• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስለ “ጽናት” የቀረበ ተጨማሪ መረጃ

September 3, 2015 08:18 am by Editor Leave a Comment

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት ኢንጂነር መሃመድ አባስ በጽናት ዙሪያ ባቀረቡት ዘገባ ከብዙ አንባቢዎቻችን ብዙ ተብለናል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ እንደመሆኑ ሕዝብ መረጃ ከማቅረብ ጀምሮ መጦመርና ዜና መሥራት ይችላል፡፡ በዘመናዊው ጋዜጠኝነት የተለመደ አሠራር ነው፡፡ በመሆኑም ባለፈው ከቀረበው መረጃ አኳያ አሁን ደግሞ ደጋፊ የሚሆን የድምጽ መረጃ ከአጭር መግቢያ ጽሁፍ ጋር ልከውልናል፤ እንዲህ ይነበባል፡-

“እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ ላቀረብኩት ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት “ዘረፋ” ግልጽ የሆነ ማስረጃ!”

ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/ኢህአዴግ እንቅልፍ አጥቶ ማደር የጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ ይታወቃል።

ህወሃት/ኢህአዴግ የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ ለይስሙላ ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ መብት በመተላለፍ የህዝቦችን መብት በጠመንጃ አፈሙዝ ጨፍልቆ ለጸሎት አደባባይ የወጣውን አዛውንት፣ ሴት፣ ወጣት ሳይል ያገኘውን ሁሉ በደም በጨቀዩ ልዩ ኮማንዶዎቹ በጥይት ረሽኗል፡፡ ከሞት የተረፈውን በቆመጥ ደብድቦ የተረፈውን በማጋዝ ወዳልታወቀ ስፍራ ወስዶ አስሮ  በማሰቃየት ላይ ይገኛል።

ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና ስቆቃ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ሰላማዊ ተቃውሞውን የበለጠ በማጠናከር ሳይገድል እየሞተ ለአምባገነኖች የአላማ ጽናቱን በተግባር አሳይቷል፤ በማሳየትም ላይ ይገኛል። ይህ የህዝበ ሙስሊሙ አንድነትና ለሃይማኖቱ ነጻነት ያለው ቁርጠኝነት እንቅልፍ የነሳው ህወሃት፤ የበግ ልምድ ለብሶ ውሎና አዳሩን ህዝበ ሙስሊሙ ጉያ ውስጥ በማድረግ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዑለማዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በኃይል አሊያም በጊዜያዊ ጥቅም በማግባባት ለዚህ እርኩስ ሰይጣናዊ ተግባሩ ማስፈፀሚያ ግበአት እንዲሆኑ ሃገር ውስጥ ያልበጠሰው ቅጠል ያልቧጠጠው ተራራ የለም።

ለአብነት ያህል የፖለቲከኛውን ጃዋር መሃመድ አሳዛኝ ታሪክ ወደ ጎን ትተን በዑስቷዝ ሃስን ታጁ ስም አዲስ አበባ ላይ ቀደም ሲል የተበተነውን ከፋፋይ የሆነ ባለ10 ገጽ ጽሁፍ ማስታወስ ከበቂም በላይ ማስረጃ ነው። በዑስቷዝ ሃስን ታጁ ጽሁፉ ላይ «ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉ ወጣቶች አላዋቂ፣ ስሜተኛ፣ ጃሂል አድርጎ ለማቅረብ ከተደረገው ጥረት ባሻገር የተቃውሞ አካሔድ ሌላ መንገድ ቢፈለግለት በሚል አሳፍሪ አቋም በተለይም የጁሙዓ ተቃውሞዎች መቋረጥ እንዳለባቸውና ኮሚቴዎቻችን ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ» ህወሃት/ኢህአዴግ ህዝበ ሙስሊሙን ተመስሎ በዑለማዎቻችን አንደበት ያሻውን መልዕክት በድፈረት ይስተላለፈበት ያ ፈታኝ የትግል ዘመን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

ዛሬ ከዚህ አፍራሽ ተዕልኮ ባልተለየ የኢህአዴግ ካድሬዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሳውዲ አረቢያ ጅዳና ሪያድ ከተማ ውስጥ ብዙሃኑ ተመስለው ሊያሰሙን በሞከሩት ጩኸት በአካባቢው ያሉትን ስመጥር የሃይማኖት አባቶችንና ሩቅ ያሉትን የህዝበ ሙስሊሙን ነጻ ሚዲያዎች ቀልብ አሳስተው ለዚህ መስሪ ተግባራቸው ግበአት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ አንድንት ላይ አደጋ ከመጋረጥ አልፈው በአቋራጭ የግል ኑሮቸውን ለማደርጀት ሲያደርጉ የነበረው ጥረት በሃገር ሽማግሌና በኃይማኖት አባቶች ውሻ በቀደድው ጅብ እንዳይገባ ሲነገራቸው የነበረውን ምከር አሻፈረን ብለው በህዝበ ሙስሊሙ ትግል ሽፋን ንጹሃን  ለማደናገር ሞክረዋል።

እነዚህ ወገኖች ጅዳ መካና መዲና ላይ እውነተኛ በሆኑ የትግሉ ባለቤቶች ሲተፉ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል እንዳለችው እንሰሳ ከፋፋዩን ዶሴያቸውን ሸንክፈው ሪያድ ከተማ ውስጥ በማድባት ጠንካራ ተብሎ በሚነገርለትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ለመፈታተን ያልሸረቡት ሴራ እንደሌለ ሰሞኑን በድምጽ ከተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በጣም የሚያሳዝነው ከጥቅማቸው ባሻገር የህዝበ ሙስሊሙ የትግል አንድነት ማየት የተሰናቸው እነዚህ ጀሌዎች ብዙሃኑን ተመስለው የሚያሰሙትን ጩኸት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በማስተጋባት ከአያሌ እህቶቻችን ቦርሳ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በትግል ሽፋን ስለሚሰበስቡት በመቶሺ የሚቆጠር ገንዘብ አግባብ አለመሆኑ በነዚህ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢመከሩም አባታዊ ምክርን ሰምቶ ከመቀበል ይልቅ መካሪዎቹን አባቶች ከመኮነን አልፈው ያልሆነ ስም በመስጠት እየፈጸሙ ያለውን ነውረኛ ተግባር በማድበስበስና ለህዝብ የቀረበውን መረጃ ከሃቅ የራቀ አስመስለው በማናፈስ «ውሻ በበላበት አፉ» እንዲሉ የህዝብ ሚዲያዎችን እስከ መዝለፍ ርቀው የሄዱበት ተግባራቸው ሰሞኑን ሪያድ በሚኖሩ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች እርቃኑን መቅረት መቻሉ የጀሌዎቹን ማንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ አድርጎታል። ዛሬ እነዚህ ጀሌዎች በፈጸሙት ነገር ሁሉ ተፀጽተው የበደሉትን ሁሉ በአደባባይ ይቅርታ በመጠየቅ ከጥፋታቸው መመለሳቸውን በደረሰን የድምጽ መረጃ አረጋግጠናል!

የድምጽ መረጃውን ለመስማት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ – ፎቶው ቀደም ብሎ ሳውዲ አረቢያ ድምጻችን ይሰማ ካደረገው ስብሰባ የተወሰደ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule