ማስታወሻ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ የህወሃት አባል ወይም ተላላኪ እንደሆነ የታሰበ ግለሰብ 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት (በፎቶው እንደሚታየው) ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን እንግሊዝ ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ለመጀመሪያ የፍርድ ምርመራ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኛው “ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ግለሰቡ “ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጾዋል። ይሁን እንጂ ዳኛው “ይህን ያህል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ ለጊዜው በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሚ እንደሚቀርብ ተነግሯል። የወለላዬ ግጥም በዚህ ዘረፋ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ (ቅርብ የሆናችሁ ግጥሙን ጸረ ሙስና ኮሚሽን ለሚባለው አድርሱልን)
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ይቺ አመለ ክፉ – መስረቅ የለመደች
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
አንድ ሻንጣ ሙሉ – ገንዘብ ይዛ ሄደች
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ሰው ሀገር ቢገቡ – ከሀገር ቢሰርቁ
ብሩም አይበላ – አያደምቅም ወርቁ
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
እንኳንስ ከሀገር – ሰርቶም በውጪ ሀገር
ማንም አላገኘ – የያዙብሽን ብር
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ህዝቡን አስርበሽው – ሰብስበሽ ሰብስበሽ
ዛሬ ሻንጣ ሙሉ – ለፖሊስ አስረከብሽ
ገንዘብ ብታገኚ ሀብት ሲሞላሽ
ሁሉም ያንቺ ፖሊስ – መስሎ ተሰማሽ
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
የፖሊስ ያለህ አትሉም ወይ?
የዳኛ ያለህ አትሉም ወይ?
ለሻንጣ ሌባ ህግ የለም ወይ?
ለፍትህ ሌባ ህግ የለም ወይ?
ልትሄጂ እንዳይሆን – ፈጽሞ ጠቅለሽ
ይሄን ሁሉ – ገንዘብ የያዝሽው ጠቅጥቀሽ
የፎቁ ኪራይ ነው – ወይስ የሆቴሉ
ከምን አገኘሽው – ሌቦ ይሄን ሁሉ
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
በበረከት ሞት – በይ ልጠይቅሽ
በአባዱላ ሞት – በይ ልጠይቅሽ
በሳሞራ ሞት – በይ ልጠይቅሽ
ገንዘብ አሲዞ ማነው የላከሽ
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ሰብስበሽ ሰብስበሽ – ላትበይው ነገር
ተሸክመሽ ወስደሽ – በተንሽው ስው ሀገር
ለድሮውም ቢሆን – ታውቂበታለሽ ንግድ
ሀገሩ አገባሽው የሀገሩን ፓውንድ
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
የፖሊስ ያለህ አትሉም ወይ?
የዳኛ ያለህ አትሉም ወይ?
ለሻንጣ ሌባ ህግ የለም ወይ?
ለፍትህ ሌባ ህግ የለም ወይ?
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ይሄን ሁሉ ገንዘብ – ማውጣትሽ ሰብስቦ
እስቲ ምን ይባላል – ወገንሽ ተርቦ
ዳኝነትን ሽረሽ – ህጉን አጥፍተሽው
ህዝቡን እያጋደልሽ – እርሙን አበላሽው
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
ገድለሽ ገድለሽ ጥለሽ – በየቦታው ስዉን
ሌቦ ከሬሳው ላይ- ዘረፍሽው ገንዘቡን
ባታይው ነው ሌቦ – አይንና ጥርስሽን
የኋላ የኋላ – አታጭም የጅሽን
ኦሆሆ ሌቦ ነይ …
Gilentufagonji says
Looting and stealing is not strange for tplf members because they have heirted from their grand parents who were been serving the italian invaders in Ethiopia
Gilentufagonji says
Woyane has looted billion dollars from Ethiopia what they don’t understand is finally the money will return home and they will come to the peoples court