• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጥቂት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ

September 16, 2015 12:41 am by Editor Leave a Comment

 ተግባቢና በሳል ነው፤ ረጋ ባለ አንደበቱ የሚሰማውን በጥሞና መናገር ልዩ ያደርገዋል ፡፡ እምነቱን አጥበቆ ይወዳል፤ የእስልምና ሃይማኖት የሚያዛቸውን ተግባራት (ሶላት መስገድ፣ መጾም…) ፈጽሞ ሌሎች መሰሎቹ እንዲፈጽሙ ማድረግን ያውቅበታል፡፡ ከሌሎች የእምነት ተከታዮች ጋር የመግባባቱና ከሁሉም ጋር በአብሮነት መኖሩ ባጠቃላይ ማህበራዊ ኑሮ የሚጠይቀውን ግዴታ የመወጣት ልዩ ችሎታ አለው፡፡ ከማንም ሰው ጋር የመግባባት፣ ተጫውቶ የማጫወት ክህሎት አለው፡፡ ከቀለሙ በተጓዳኝ ሀይማኖታዊ እውቀቱም የተመሰከረለት ነው፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችን በመሰብሰብ በስነ ምግባር እንዲታነጹና ለሀገራቸው ተቆርቋሪ እንዲሆኑ ያስተምራል፡፡ በግቢው ውሰጥ ተሰሚነት ካላቸው የሀይማኖት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡

ካሚል ሽምሱን መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሳለ አውቀው ነበር፤ አንድ ባችም ነበርን፤ በህግ ፋከልቲ ተደልድለን ለአምስት አመታት በቆየንባቸው ወራት ደጉንም ከፉንም አብረን አሳልፈናል፡፡ ካሚል ሸምሱ ጽንፈኛ የሆነ አመለካከት ሲያራምድ ለአንዲት ቀናት እንኳን አላየነውም፣ አልሰማነውም፤ በግቢው ውሰጥ ከነበረው ተወዳጅነት ተነስቶም እንዲህ አይነት ሀሳብ የነበራቸውን ተማሪዎች ሊገስጽ ይችል ይሆናል እንጂ አንዲትም ቀን ክፉ ሲወጣው አልሰማንም፡፡ ከዚህ ይልቅ በሳል አስተሳሰቦችንና አንድ የሚያደርጉ ስራዎችን ማከናውን ይቀናዋል – ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፡፡ እንደውም እኛም ክርስትያንነታችን እርሱም ሙስሊምነቱ ሳይገድበን እንደ አንድ የአዳም ልጆች እንጨዋወታለን ቀልዶችን እያነሳን እንሳሳቃለን እንጂ ላንዲትም ቀን እርሱ የኛን እኛም የርሱን እምነት የተንተራሰ እሰጥ አገባ ወይንም መከፋፈል መሰረት ያደረግ ጉዳይ አንስተን አናውቅም፡፡ እንደውም አንተ የዚህ እኔ የዛ ነኝ የሚለው አስተሳሰብ ትዝም ብሎን አያውቅም፡፡ በዚህ መልኩ የህግን ሀ ሁ፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ የህግ ሙያን ተምረን ወጣን፡፡ አገቱኒ፡፡

ሰብአዊ መብት ማለት የማይሸራረፍ አንድ ሰው ሰው ስለሆነ ብቻ የሚያገኘው መብት ማለት ነው፡፡ ሰብአዊ መብት አንዱ ባንዱ ካልተደገፈ፣ አንዱን አክብሮ ሌላዉን ቸል ያሉት እንደሆነ፣ አንዱን በአደባባይ አውሎ ሌላውን ጓዳ ውስጥ ከቆለፉበት ምንም ትርጉም አይኖረውም፣ ግንጥል ጌጥ የሚሉት አይነት ይሆናል፡፡ በአገራችን ዛሬ ዛሬ እየደመቀ የመጣው ሰብአዊ መብቶችን መቆራረጥና መሸራረፍ ችግር አንዱ አንዱን እየወለደ አገሪቷን ልትወጣው የማትችለው አዘቅት ውስጥ እየከታት እየመጣ እንደሆነ በሂደት ክስተቶች እያሳዩን መጥተዋል፡፡

መንግስት የእምነት ነጻነት ተረጋጧል እንደፈለግክ እምነትህን ማራመድ ትችላለህ ይልና በሌላ በኩል ደግሞ የእምነት መሮዎችህን የምመርጥልህ ግን እኔ ነኝ ይላል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞው ከዚህ ይጀምራል፤ በታህሳስ 21 ቀን 2004 አ.ም. ጀማል መሀመድ የተባለው የመጅሊስ አመራር አወሊያ ትምህርት ቤት አንድ ደብዳቤ ይጽፋል፤ ደብዳቤው በርካታ የመስጂድ ኢማሞች፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን እና የአረብኛ ተማሪዎች ከተቋሙ እንደተባረሩ ይገልጻል፤ ይህ ደብዳቤ መጅሊሱ ሙሉ በሙሉ ፓለቲካዊ ማስፈጸሚያ ወደ መሆን እንደተሸጋገረ ግልጽ ማሳያ ሆነ፡፡ ሀይማኖታቸው እንዲህ የካድሬ ማላገጫ መሆኗ ያበገናቸው ሰዎችም ተሰበሰቡ፣ አስራ ሰባት አባላትን ያቀፈ ኮሚቴ ሰየሙ፡፡ “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” በተሰኘው በዚህ ኮሚቴ አባል ለመሆን ከተመረጡት አንዱ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ነበር፡፡ ስራ ድልድል ላይም የኮሚቴው የህግ ተጠሪ ሆኖ ተመረጠ፡፡

ከዚህ በኋላ ኮሚቴው ስብሰባዎችን በሚያካሄድበት ቦታ ሁሉ የኮሚቴው አካሄድ ፍጹም ሰላማዊ እንደሆነ ህገ መንግስቱ ላይ የተካተቱ መብቶቻችን ይከበሩ ሲል ካሚል ሸምሱ ይናገር ነበር፡፡ ጥያቄያቸውም ሀይማኖታዊ ብቻ እንደሆነ ሳያሰልስ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ ባንዳንድ መስጊዶች ስብሰባ ላይም (ለምሳሌ በሻሸመኔ እንዲህ ማድረጉን ከአሌክስ አብርሀም የፌስቡክ ገጽ ላይ የተያያዘውን ፎቶ ማየት ይቻላል፡፡) የህገ መንግስቱን አንቀጾች እየጠቀሰ ጥያቄያቸው ህግንና ህግን የተከተለ መንገድ እንደሆነ አንደበተ ርትኡ የሆነው ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ተናግሯል፡፡

በግንቦት 8 ቀን 2004 አ.ም ኮሚቴው ስለተቋቋመበት አላማና የህዝበ ሙስሊሙ ወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ቃለ ምልልሱም ህዝበ ሙሲሊሙ ያነሳው ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች መሆናቸውንና ባእድ የሆነው የአህባሽ አስተምሮም በግድ ላያቸው ላይ ሊጫን በመሞከሩ መቃወማቸውን ተናግሯል፡፡ አያይዞም አህባሽ ለሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን፣ ለክርስትያኑ ባጠቃላይ ለሀገር ጸር የሆነ ሙስናን የሚያበረታታ አስተምህሮ ነው ሲልም ተናግሯል፡፡ በሌላ አነጋገር አህባሽ ጸረ ኢትዮጵያ አስተምህሮ ከሆነ የነካሚል ሸምሱ ትግልም ይህንን ባጭሩ ለመቅጨት ከሆነ ትግላቸው አገርን ማዳንም ጭምር ነበር ማለት ነው፤ በመሆኑም ለመስዋእትነታችሁ ታላቅ ዋጋ መስጠት ብቻ ሳይሆን እዳም እንዳለብን ተገንዝበናል፡፡ ነገሩ አስቀድሞ የገባቸው የሚመስሉ እንዳንድ ክርስትያኖች ኮሚቴው በሚጠራው ስብሰባ ላይ ይገኙ ነበር፡፡Kamil(1)

መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ድረስ ደብዳቤ በመጻፍ ጥያቄያቸው ገለልተኛ መጅሊስ እንዲቋቋም፣ የአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር እንዲከለስ፣ የሀይማኖት ነጻነታቸው እንዲጠበቅ የሚያሳስብ ብቻ እንደሆነ ገልጧል፡፡ ይህ ቢሆንም ቅሉ በጥር የተቋቋመው ኮሚቴ አባላት በሀምሌ ወር 2004 አ.ም ለእስር ተዳረጉ፡፡ ለአገሩም ለእምነቱም ብዙ መስራት የሚችለው ካሚል ሸምሱ ከልጆቹና ከባለቤቱ ተነጥሎ ወደ እስር ቤት ተጋዘ፡፡ ለአራት ወራትም ያለ ፍርድ በማእከላዊ ታሰሮም ስቃየ ስቃያትን ተቀበለ፡፡ ጂሀዳዊ ሀረካት ተብሎ በወያኔ የተቀነባበረው ዶክመንተሪ ፊልም ላይም ካሚል ሸምሱን ሲያቀርብ መከራ እየደረሰበት መሆኑን ከገጽታው ማንበብ ይቻል ነበር፡፡ ማእከላዊ እንዲታሰሩ የተደረጉበት ቦታም ሳይቤሪያ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በበጋም በክረምትም እጅግ ቀዛቃዛ በመሆኑ እችክእችክ ያስብላል፡፡በማእከላዊ ቆይታቸውም አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጥቃቶችን ለማስተናገድ ተገደዋል፡፡ ከመርማሪዎቹ አንዱም‹‹ዓለም ላይ ያለን ጠበቃ ብታመጣ አታሸንፈንም ፖሊሱም የእኛ! አቃቤ ህጉም የእኛ! ዳኛውም የእኛ!›› ሲል እንደደነፋ ካሚል ሸምሱ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ከዚህ ባለፈም በፍርድ ሂደቱ ጊዜ ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን ለአቃቤ በማቅረብ ሀሰት ራቁቱን እንዲቀር አድርጓል፡፡

ደፋር የሆነውና በመንግስት የሚደገፈው መጅሊስ ግን የህዝበ ሙስሊሙን መሪዎች አሳስሮ ሲያበቃ ምርጫ አካሂዳለሁና ተሳተፉ ሲል ቱሪናፋነቱን ሊያስመሰክር በቅቷል፡፡ መስከረም 27፤ 2005 በማደርገው ምርጫም ተሳተፉ ሲልም መለፈፍ ጀመረ፡፡ ካሚል ሸምሱም በጠበቃው አማካይነት መጅሊሱን በመክሰስ ምርጫውን እንዳያካሂዱ እግድ ይተላለፍ ዘንድ ጠይቆ ነበር፡፡ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተዛወረ ወዲህ በእስረኞቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን በማትረፉ በከፍተኛ ድምጽ የታሳሪዎች ተወካይ ተደርጎ ተመርጧል፡፡ የሙስሊሞች ድምጽ፤ የቂሊንጦ ድምጽ፤ የድምጽ አልባዎች ድምጽ – ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፡፡ በቂሊንጦ አስሩ በዞን 1 ታሰሮ የነበረ ሲሆን ወደ ዞን ሶስት እንዲዛወር ተደርጓል፤ የእስር ቤቱ ምክንያትም ሰዎችን እየሰበሰብክ ቁራን እንዲቀሩ ታደርጋለህ የሚል ነበር፡፡

እንደ ማራቶን በረዘመው የሶስት አመታት የፍርድ ቤት ምልልስና እንግልት በኋላ ካንጋሮው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸሁ ሲል በየነ፡፡ የሙስሊሙ ህጋዊ ተወካይ የሆኑትን ኮሚቴዎችም ከ 7 እስከ 22 አመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ ከኮሚቴው አባላት መሀል 22 አመት የተፈረደባቸው አራት ሲሆኑ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ አንዱ ነው፡፡ እውነትና ፍትህ አገራቸው የት ይሆን ፍርዱን ተከትሎም ባንድ ክፍል አብረው ይማሩ ከነበሩ ጓደኞቹ ሁለቱ እንዲህ ብለዋል፣

  • Law school friend, Kamil Shemsu, fall prey to the constitution he studied! 22 yrs of sentencing for simply demanding constitutional rights?
  • Kamil was the most mature, intelligent, down to earth classmates I’ve ever had. As far as I am considered one cannot get as far from being a religious terrorist as Kamil. He was a good man.

ዛሬ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገርም በውጭም ያለው ካሚል ሸምሱን አንተ ብሎ አይጠራውም፤ ሰውን የሚያስከብረውም ሆነ የሚያወርደው ስራው ነውና ላመነበት ጉዳይ እስከ መጨረሻው በጽናት በመጓዙ አንቱ ተብሏል፡፡ እንዲህ አንቱታን ካተረፈ፣ ቃሉን ጠባቂ፣ ስለ እውነት እስከመጨረሻው ድረስ መስዋእት ከሆነ ሰው ጋር ባንድ ወንበር ቁጭ ብዬ መማሬ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ 22 አመታትን ያለ ሀጥያቱ እንዲታሰር በዝንጀሮው ፍርድ ቤት የተበየነበትን ወንድም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን ሳስበው እንባ ይተናነቀኛል፡፡

ህግን አሳምሮ ለሚያውቅ ግለሰብ ህጋዊ መብቶቹ ሲጣሱ መመልከት እጅግ የሚያደማ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ ቢሆንም የዛሬ መስዋእትህ ለሀገርህ፣ ለልጆችህ፣ ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን ያደረግው መሆኑ ያጽናናኛል፤ እውነት ግን መቼም ተሸፍና አትቀርም፣ ዋጋ የከፈላችሁለት አላማችሁም ጠብ አይልም፤ እውነት ነጻ ታወጣችኋለች፤ ወንድም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ አንተም ሆንክ ፍትህ የተጠማው መላው ህዛባችን ከእውነተኛ ዳኛ ፍትህ የሚያገኙበት ቀን እጅግ ቅርብ ናት፡፡

አዲሱ አመት በጎ በጎውን የምንሰማበት ያድርግልን!

በሱፍቃድ ደረጄ

(besufekadereje@gmail.com)

ተጻፈ፤ መስከረም 02 2008 አ.ም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule