የአማርኛው ብሂል ‹ካለበት የተጋባበት› ይለዋል፡፡ ፈረንጅኛውም ለዚህ ዓይነቱ አባባል ከአማርኛው አይሰንፍም፤ More catholic than the Pope በማለት ያሳምረዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት አባባሎች ከአፎታቸው ተመዝዘው ወደ ደንበኛቸው እንደጃርት ወለባ እየተወረወሩ እሚሰኩት ኃይለማርያም ደሳለኝን የመሰለ ራሱን መሆን የማይችል በጥቅም ወይም በዓላማ ወይም በአእምሮ ዘገምተኝነት ወይም ምናልባትም በነዚህ በሦስቱምና በሌሎችም ተዛማጅ ምክንያቶች የተነሣ ሰውነቱን ለባዕድ ስብዕና ያስገዛ አስገራሚ ፍጡር ሲያጋጥም ነው፡፡ ለነገሩ ዘመኑ የአስገራሚ ፍጡራን መናኸሪያ ስሇሆነ አሁን አሁን የሚያስገርመን ይልቁናም ደህና ሰው ያገኘን እንደሆነ ነው፡፡ (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ይገኛል) … [Read more...] about ካለበት የተጋባበት
Archives for October 2012
ዓዲስ ሰው
ተወዳጁ ገጣሚና ባለቅኔ ጋሽ አሰፋ ገ/ማርያም ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓም (October 17,2012) የታላቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ የክቡር አቶ ሃዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) 103ኛ ቀነ-ልደት (BIRTHDAY) በማስመልከት የጻፉትን ግጥም ልከውልናል፡፡ ግጥሙ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ በዚህ ወቅት በድጋሚ አውጥተነዋል (በፎቶ የተከሸነውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) በተጨማሪ በአንድ ወቅት የተቀኙላቸውን በቃላቸው የሚስታውሱትን የአማርኛ መወድስ ቅኔ መርቀውልናል፡፡ ጋሽ አሰፋን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ መወድሱ እንዲህ ይነበባል፡- መውደድ ካልቀረ ማፍቀር፤ ወገንና ሃገር፤ እንደ ደራሲው አዲስ ነገር፤ ፍቅር !...እስከ መቃብር! በመጨረሻም “ለወጣቱ ትውልድ መልካም አርአያ የሚሆን ኢትዮጵያዊ እምብዛም በሌለበት በዚህ ጉደኛ ዘመን እንደነ ሃዲስ አለማየሁ የመሳሰሉትንና በየወቅቱ … [Read more...] about ዓዲስ ሰው
ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
አርቲስት ዳምጠው አየለ አጋጥሞት የነበረው ችግር በኖርዌይ መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች በኩል እየታየና ወደ መፍትሔ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ። በደረሰበት ያልታሰበ እንግልትና በቤተሰብ ናፍቆት የተነሳ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ በርካታ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መጨነቃቸውን ያስታወቀው ዳምጠው አየለ፣ "ያጋጠመኝ ችግር መስመር እየያዘ ነው፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። ስሜታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ ምስጋናዬ ታላቅ ነው" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። በወቅቱ ከቤተሰብ የቆየ ፍቅር ጋር ተዳምሮ፣ አጋጣሚው ስላበሳጨው ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በሰጠው ቃለምልልስ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ አዝነው በስልክና በተለያዩ መንገዶች ስለላኩለት ማበረታቻ ምስጋና ያቀረበው ዳምጠው፣ በቅርቡ ለወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ ሰፊ መልዕክት እንደሚኖረው አመልክቷል። ከቃለ ምልልሱ ዋና … [Read more...] about ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ
በማናቸውም የአገሪቱ ባለስልጣናትና ተቋማት ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ይፋ የማያደርጉት የአገር ውስጥ የጫት ፍጆታና ገቢ በውስጡ ከፍተኛ ዝርፊያ ይከናወንበታል። ከዝርፊያው ጋር በተያያዘ አቶ መለስን ጨምሮ ከፍተኛ ሹማምንትና ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቅድሚያ ስማቸው ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የጎልጉል የኦህዴድ ምንጮች የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትርና የንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ሚኒስትሩ በጫት ንግድ ዙሪያ የሚጫወቱትን ሚና አጋልጠዋል። ያገኘነውን መረጃ ለንባብ ያመች ዘንድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። የጫት ንግድ ዝምድና - ወ/ሮ ሱራ በደርግ የአገዛዝ ዘመን ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት መደረግ የጀመረው ጫት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወያኔ አባላትን ቀልብ አልሳበም ነበር። ባለስልጣናቱና የቀድሞው ታጋዮች ጫት ተጠቃሚ ስላልነበሩ ስለ ጫት ንግድና ከፍተኛ ፍጆታ እንዳለው መረጃው … [Read more...] about ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ
እኔ ምን አገባኝ?
እኔ ምን አገባኝ እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ የሚል ግጥም ልጽፍ ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና ምን አገባኝ ብየ ቁጭ አልኩ እንደገና:: ግጥሙ የተወሰደው ከኑረዲን ዒሳ ፌስቡክ ነው:: ባለፈው ሌባዬ በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ የተሳተፋችሁትን ሁሉ በተለይ ደግሞ Tsinat ፣ Gedion Adenew እና አበበ አዲስ ከልብ እናመሰግናለን:: እስቲ ለዚህኛውም አንድ ሁለት ሁላችንም እንበል!! እንደበፊቱ ሁሉ ምላሹ በግጥም ቢሆን ጨዋታዋን ሞቅ ያደርገዋል:: … [Read more...] about እኔ ምን አገባኝ?
ALERT!!
Ambassador Tiruneh Zena's fake Human Rights Council is seeking legitimacy from the United Nations for his excellent job of turning blind eye on the atrocities committed right under his nose. The need to be accredited by the United Nations gives the Commissioner and his bosses two advantages. From one angle, he may seek funding to keep his inactive office alive and may even share the money with his bosses. On the other hand he would try to claim recognition for silence on human rights abuse in … [Read more...] about ALERT!!
የሚያድግ ኢኮኖሚ ነገር ግን የማይታይ የማይዳሰስ!
... የአገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት በዚህ ዐመት በዚህ መጠን ጨምሯል፡ አልጨመረም እያሉ ሙግት ውስጥ እምብዛም መግባት የሚያስፈልግ አይደለም። ምክንያቱም ስለአንድ አገር ዕድገት በቁጥር ከተደገፈ ማሰረጃ ይልቅ ሁኔታው የበለጠ በቂ ማስረጃ ስለሚሆን ነው። በሌላ ወገን ደግሞ በኢኮኖሚ ዓለም ውስጥ የሚያወናብዱ ብዙ ሁኔታዎች አሉ። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የብዙ አፍሪቃ አገር ኢኮኖሚዎችንም በሚመለከት እነ ዓለም ባንክ ሁሉ ሳይቀሩ የዓለም የፊናንስና ኢኮኖሚ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት በዕድገት እንደመነጠቁ ሊያሳምኑን ሞክረው ነበር። ይህ በጥሬ ሀብት ጥያቄና ሽያጭ ላይ የተሰመሰረተ ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚ ሲዳከም በዚያው መጠንም ዕድገቱ ወደታች እያለ እንደመጣና፣ ይህ ዐይነቱ ዕድገት ደግሞ ለምን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊባል እንደማይችል በብዙ ማስረጃ በተደገፈ መልስ ተሰጥቶበታል።ሙሉው ጽሁፍ … [Read more...] about የሚያድግ ኢኮኖሚ ነገር ግን የማይታይ የማይዳሰስ!
የዳምጠው አየለ ጥሪ!!
“ሰው ናፈቀኝ፣ ልጆቼና አገሬ ታወሱኝ፣ ባህሌና ልማዴ የት ገባ….?” የሚሉት የአንድ ስደተኛ ጥያቄዎች ለመቶ አለቃ ዳምጠው አየለ ተረት ሆነውበታል። አርቲስት ዳምጠው አየለ ከሁርሶ የመኮንኖች ማሰልጠና ማዕከል የመኮንንነት ትምህርት ተከታትሏል። ለሰላሳ ሁለት ዓመታት በምድር ጦር የሙዚቀኛ ሻለቃ አገልግሏል። በተለይም በባህላዊና አገር በሚያሞካሹ ዜማዎቹ የሚወደደው ዳምጠው አገሩን፣ ሁለት ልጆቹንና ባለቤቱን ጥሎ በስደት ኖርዌይ ከገባ ሰባት ዓመታት አሳልፏል። የስልሳ ሶስት ዓመቱ ዳምጠው ያጋጠመውን ጊዚያዊ ችግር አስመልክቶ ከጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ዳምጠው ችግር እንዳጋጠመው ሲሰማ አስቸኳይ ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች፣ ድርጅቶች፣ ማህበሮች፣ ላደረጋችሁት በአርአያነት የሚጠቀስ ተግባር የዝግጅት ክፍላችን በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን ይወዳል። “… አዎ፤ እኔም ራሴን … [Read more...] about የዳምጠው አየለ ጥሪ!!
The Ethiopians and moral conduct.
I dreamt about my uncle. He has been dead for over ten years so I was wondering what brought him to my conscious now. It was a vivid dream and I woke both sad and happy. So all day long I kept wondering what is it that made me dream about him. I really think I was able to come up with a reasonable explanation why this memory was triggered in my brain. I believe it is due to what I have been reading lately that woke up this memory about service, integrity and today’s Ethiopia. The night before … [Read more...] about The Ethiopians and moral conduct.
ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!
ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም። ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት … [Read more...] about ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!