አርቲስት ዳምጠው አየለ አጋጥሞት የነበረው ችግር በኖርዌይ መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች በኩል እየታየና ወደ መፍትሔ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ። በደረሰበት ያልታሰበ እንግልትና በቤተሰብ ናፍቆት የተነሳ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ በርካታ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መጨነቃቸውን ያስታወቀው ዳምጠው አየለ፣ “ያጋጠመኝ ችግር መስመር እየያዘ ነው፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። ስሜታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ ምስጋናዬ ታላቅ ነው” ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
በወቅቱ ከቤተሰብ የቆየ ፍቅር ጋር ተዳምሮ፣ አጋጣሚው ስላበሳጨው ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በሰጠው ቃለምልልስ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ አዝነው በስልክና በተለያዩ መንገዶች ስለላኩለት ማበረታቻ ምስጋና ያቀረበው ዳምጠው፣ በቅርቡ ለወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ ሰፊ መልዕክት እንደሚኖረው አመልክቷል። ከቃለ ምልልሱ ዋና ጭብጥ ውጪ ወሬ ለማስተጋባት ሃሳቡን አዛብቶ በማቅረብ በተለያዩ ድረገጾች ላይ እንዲለጠፍ ምክንያት የሆኑትን ክፍሎች አስመልክቶ በጎልጉል ፌስቡክና ኢሜይል አድራሻ አማካይነት በርካታ አስተያየት እንደደረሰን ለመግለጽ እንወዳለን።
Beeminet says
Egzeabher kante gar yehun ayezoh bekerbu ende Egzeabher fekad ke betesebeh gar tekelakelaleh.
legaw says
demetew ayezoh wetader mehonehen ateresa lechiger eji mesetet yelem weyanen sanatefa reft yelem wendeme sedet qentot ayedelem