… የአገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት በዚህ ዐመት በዚህ መጠን ጨምሯል፡ አልጨመረም እያሉ ሙግት ውስጥ እምብዛም መግባት የሚያስፈልግ አይደለም። ምክንያቱም ስለአንድ አገር ዕድገት በቁጥር ከተደገፈ ማሰረጃ ይልቅ ሁኔታው የበለጠ በቂ ማስረጃ ስለሚሆን ነው። በሌላ ወገን ደግሞ በኢኮኖሚ ዓለም ውስጥ የሚያወናብዱ ብዙ ሁኔታዎች አሉ። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የብዙ አፍሪቃ አገር ኢኮኖሚዎችንም በሚመለከት እነ ዓለም ባንክ ሁሉ ሳይቀሩ የዓለም የፊናንስና ኢኮኖሚ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት በዕድገት እንደመነጠቁ ሊያሳምኑን ሞክረው ነበር። ይህ በጥሬ ሀብት ጥያቄና ሽያጭ ላይ የተሰመሰረተ ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚ ሲዳከም በዚያው መጠንም ዕድገቱ ወደታች እያለ እንደመጣና፣ ይህ ዐይነቱ ዕድገት ደግሞ ለምን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊባል እንደማይችል በብዙ ማስረጃ በተደገፈ መልስ ተሰጥቶበታል።ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል
Leave a Reply