አረንጓዴ፡ብጫና፡ቀይ፡ሰንደቅ፡ዓላማችን፡ የአንድ፡ኢትዮጵያና፡ የነፃነት፡ ምልክታችን፡ነው።አረንጓዴው፡ የአገራችንን፡ልምላሜ፣ብጫው፡ሃይማኖታችንና፡ምግባራችን፣ቀዩ፡ሀገራችን፡ ወሰንዋ፡ ሳይደፈር፡ነፃነቷ፡ ተከብሮ፡እንዲኖር፡ጀግኖች፡ወገኖቻችን፡ለከፈሉት፡መስዋዕትነትን፡የሚገልጽ፡ነው። ሙሉውን አስነብበኝ/read more … [Read more...] about ሰንደቅ፡ዓላማችንን
Archives for September 2012
ሌባዬ. . .
ሌባዬ. . . ድምጹ ሳይሰማ ኮቴውን አጠፍቶ በጠራራ ፀሐይ የደጄን በር ከፍቶ መዝለቅ የጀመረው ክርችም በሬን ከፍቶ ምን ሊዘርፈኝ ይሆን በምኔ ጎምጅቶ? በማለት ኖላዊት ሽመልስ ስትጠይቅ የሚከተሉት መልሶች ተሰጥተዋታል፡፡ (ምልልሱን ያገኘነው ከፌስቡከ ሲሆን እርስዎም የሃሳብ በመስጫውን በመጠቀም ምላሽዎን እንዲሰጡ እንጋብዝዎታለን፡፡) ************************************************************************************* ጠንቀቅ አለሽ ንብረት አለሽ አንቺዬ ሃብት አለሽ ገንዘብ የማይገዛው ለራስሽ ያልታየሽ እጅግ የበለጠ ከወርቅ፤ አልማዝ፤ ከእንቁ አድፍጦ ሊዘርፍሽ ያመጣው ከሩቁ እመኚኝ ሃብት አለሽ ዘብ የሚያስፈልገው ብቻ ችላ ብለሽ እንዳታሰርቂው፡፡ (ብሌን … [Read more...] about ሌባዬ. . .
“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”
“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው። ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር … [Read more...] about “ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”
“ግራውንድ ሲቀነስ አንድ”
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ለአዲስ አበባ ከተማ ክብር ያላችሁ እንስማማለን። አዲስ አበባ አንጀቷ ርህሩህ ነው። ከገዢዎች ክፋት በተጨማሪ አዲስ አበባ ፊቷን ብታጠቁር ምን ይኮን ነበር? ሎሬት ጸጋ ስለ አዲስ አበባ ተቀኙት ወደው አይደለም። በውነት ላስተዋለው የአዲስ አበባ ቆዳና ያዲስ አበቤዎች ትከሻ “ላይችል አይሰጥም” የሚሉት አይነት ነው። በየቀኑ አዲስ አበባ በማለዳ በትና በምሽት የምትሰበስባቸው ልጆቿ ተቃምሰው ማደራቸው ባዲሳባ በረከት እንጂ በገዢዎች አቅርቦት አይመስልም። ከአራቱም ማዕዘን የሰው ደራሽ ወደ አዲስ አበባ ይንፎለፎላል። አዲስ አበባ ሞልታ የምትፈስ አትመስልም። እምዬ ምኒሊክ ሲቆረቁሯት ጀምሮ አዲስ አበባ ተቀባይ ነች። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና፣ የሰው ልጅ እምብርት፣ አዲስ አበባ፣ ፊንፊኔ። ምንም ትባል ምን አዲስ አበባ ሁሉም ጓዳ የተባረከች ናት። … [Read more...] about “ግራውንድ ሲቀነስ አንድ”
ዶላር አዘዋዋሪዎቹ ደላሎች!!
ህወሓት የአጋር ፓርቲዎቹን የንግድ ተቋማትና ልማታዊ ባለሀብት እያለ የሚጠራቸውን አባላቱን በዋናነት አሰባስቦ ያቋቋመው የወጋገን ባንክ ውለታ ባስገባቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር የመሰብሰብ አቅም መገንባቱ ተጠቆመ። የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባካሄደው ማጣራት ወጋገን ባንክ ከፖለቲካው አመራር ባለው ቀጥተኛ ድጋፍና ሽፋን በመታገዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን የውጪ ምንዛሪ መቆጣጠር ያስቻለውን አቅም የገነባው በአስገዳጅ ደንብ ነው። በሶማሌ ተወላጆችና በህወሓት ሰዎች አማካይነት በሽሪክነትና በተናጥል የተቋቋሙ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማት ስራውን መስራት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ሲያወጡ ከወጋገን ባንክ ጋር ብቻ ለመስራት አስቀድመው ውል እንደሚፈጽሙ ያስታወቀው ዘጋቢያችን፤ በዚሁ መሰረት ውል ከገቡት የገንዘብ … [Read more...] about ዶላር አዘዋዋሪዎቹ ደላሎች!!
“ታላቅ ዕድል ነው!”
ዛሬ አርብ ልክ ከጠዋቱ 3፡38 ላይ 374 የኢህአዴግ ወኪሎችና ኢህአዴግን እንደሚደግፉ በግልጽ የሚናገሩት አንድ በግል ያሸነፉ የፓርላማ አባል የሚገኙበት የተወካዮች ምክር ቤት አጨበጨበ። ጭብጨባውን ተከትሎ ኢቲቪ የቦሎ ሶሬውን ሰው አመላከተ። ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ በሟቹ አቶ መለስ የፓርላማ መቀመጫ ላይ የተሰየሙት አቶ ኃይለማርያም ፈገግታ አሳዩ። አስቀድሞ የተነገረው በትረ ሹመት ስርዓቱን አሟላ። አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ታወጀ። ቀልጠፍ ቀልጠፍ እያደረጉ ስርዓቱን የመሩት አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ተገኔ ጌታነህን ጋበዙ። በሳቸው ትዕዛዝ ኃይለማርያም ቃለ መሃላ ለመፈጸም ቀኝ እጃቸውን አነሱ። ስማቸውን ጠርተው ማሉ።“…ከአገርና ከህዝብ የተጣለብኝን ሃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት፣ እንዲሁም ህግንና … [Read more...] about “ታላቅ ዕድል ነው!”
ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ?
አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አስር የሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አስተዳድረዋታል፡፡ ከእነዚህ መካከል በተለየ ሁኔታ ከሚወሱት አንዱ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ በአውሮጳ ያደረጉት ተጋድሎ እጅግ ከፍተኛ ለመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች ሲጠቀስ የሚሰማ ነው፡፡ አርበኞቻችን በአገር ውስጥ የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍሉ አክሊሉ ሃብተወልድ በአውሮጳ የከፈሉት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያን ለማዳን የሠሩት ሥራ ተጽፎ የማያልቅ ታሪካቸው ነው፡፡ ያላንዳች ማጋነን የዲፕሎማሲውን ሥራ ያለመታከት ከግብ ያደረሱት አክሊሉ ነበሩ፡፡ በተለይ “የአክሊሉ ማስታወሻ” በተባለው የራሳቸው ታሪክ በከፊል የተወሳበት መጽሐፍ ላይ የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆር እና የፈረንሣዩ ጠ/ሚ/ር ላቫል ከኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት አብዛኛው የሆነው ሐረር፣ ሲዳሞና ባሌን ጨምሮ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ?
Ato Seye and his politics.
By Yilma Bekele. Mr. Charles Krauthammer is an American syndicated columnist, political commentator and is considered a highly influential conservative voice. He is critical of President Obama’s policies and supports the election of Mr. Romney to be President. As a tradition if a candidate for the presidency does not have a thick resume when it comes to foreign policy issues they normally travel to friendly European countries to shake hands with the leaders for what is called a ‘photo … [Read more...] about Ato Seye and his politics.
ድምፅ አልባው አብዮት በኢትዮጵያ
በራሚደስ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በህዝቡ ጫንቃ ላይ ተጭኖ የኖረውና በብልጣብልጡ መሪ መለስ ዜናዊ በተቀየሰው መስመር መሰረት ለመጪው አራትና አምስት አስርት ዓመታትም ይቀጥላል ተብሎ ሲፎክርበት የነበረው የትግሬ አፓርታይድ አገዛዝ ባልታሰበና ባልተጠበቀ መልኩ ፍሬን መያዙ ብቻም ሳይሆን ሿፈሪዎቹ ከመሪ ጨበጣው ገለል መደረጋቸው እውነትም ሀገሪቷ የድምፅ አልባ አብዮት እያስተናገደች መሆኗን የሚያሳይ ተጨባጭ ምልከታ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ይህ አይታሰቤና ድንገቴ ክስተት ተጠራጣሪዎቹ እንደሚገምቱት አስቀድሞ በሚስጥር የተቀነባበረ (አንዳንዶች የጠቅላይ ሚኒስተሩ ምክንያተ- ቅስፈት የማይታዩ እጆች አሉበት ብለው እንደሚጠረጥሩት) አልያም እንደብዙዎቹ እምነት ‹‹የእግዚአብሔር ስራ›› ተብሎ ለጊዜው ሊታለፍ ቢቻልም ቅሉ ይህ አብዮት ተጀመረ እንጂ ተጠናቀቀ ብሎ የየዋህ ከበሮ ድለቃ ውስጥ … [Read more...] about ድምፅ አልባው አብዮት በኢትዮጵያ
“የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!!
አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ። በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል። ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም … [Read more...] about “የመሬት ባላባቱ” ሚኒስትር!!