በራሚደስ
ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በህዝቡ ጫንቃ ላይ ተጭኖ የኖረውና በብልጣብልጡ መሪ መለስ ዜናዊ በተቀየሰው መስመር መሰረት ለመጪው አራትና አምስት አስርት ዓመታትም ይቀጥላል ተብሎ ሲፎክርበት የነበረው የትግሬ አፓርታይድ አገዛዝ ባልታሰበና ባልተጠበቀ መልኩ ፍሬን መያዙ ብቻም ሳይሆን ሿፈሪዎቹ ከመሪ ጨበጣው ገለል መደረጋቸው እውነትም ሀገሪቷ የድምፅ አልባ አብዮት እያስተናገደች መሆኗን የሚያሳይ ተጨባጭ ምልከታ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ይህ አይታሰቤና ድንገቴ ክስተት ተጠራጣሪዎቹ እንደሚገምቱት አስቀድሞ በሚስጥር የተቀነባበረ (አንዳንዶች የጠቅላይ ሚኒስተሩ ምክንያተ- ቅስፈት የማይታዩ እጆች አሉበት ብለው እንደሚጠረጥሩት) አልያም እንደብዙዎቹ እምነት ‹‹የእግዚአብሔር ስራ›› ተብሎ ለጊዜው ሊታለፍ ቢቻልም ቅሉ ይህ አብዮት ተጀመረ እንጂ ተጠናቀቀ ብሎ የየዋህ ከበሮ ድለቃ ውስጥ እንደማያስገባ ማወቅ ከምንም በላይ አስፈላጊ ይመስላል፡፡ እስከ መጪው ሀገራዊ ምርጫ የሚያደርሱን ቀጣዮቹ ሶስት አመታት የድምፅ አልባው አብዮት ዘላቂነት አልያም አብዮቱ ድምፅ አውጥቶ የሚጮህበት ጊዜ መሆኑን መገመቱ አይከፈልም፡፡ (ሙሉውን አስነብበኝ)
Leave a Reply