• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዶላር አዘዋዋሪዎቹ ደላሎች!!

September 24, 2012 07:47 am by Editor 3 Comments

ህወሓት የአጋር ፓርቲዎቹን የንግድ ተቋማትና ልማታዊ ባለሀብት እያለ የሚጠራቸውን አባላቱን በዋናነት አሰባስቦ ያቋቋመው የወጋገን ባንክ ውለታ ባስገባቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር የመሰብሰብ አቅም መገንባቱ ተጠቆመ።

የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባካሄደው ማጣራት ወጋገን ባንክ ከፖለቲካው አመራር ባለው ቀጥተኛ ድጋፍና ሽፋን በመታገዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን የውጪ ምንዛሪ መቆጣጠር ያስቻለውን አቅም የገነባው በአስገዳጅ ደንብ ነው።

በሶማሌ ተወላጆችና በህወሓት ሰዎች አማካይነት በሽሪክነትና በተናጥል የተቋቋሙ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማት ስራውን መስራት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ሲያወጡ ከወጋገን ባንክ ጋር ብቻ ለመስራት አስቀድመው ውል እንደሚፈጽሙ ያስታወቀው ዘጋቢያችን፤ በዚሁ መሰረት ውል ከገቡት የገንዘብ አሰባሳቢ ድርጅቶች መካከል ዋንኞቹን በስም ዘርዝሯል።

ደሀብሺል/Dahabshiil፣ ካህ ኤክስፕሬስ/Kaah Express፣ ተወከል/Tawakal፣ ገረን ኤክስፕሬስ/Qaran Express፣ ኦሊምፒክ ኤክስ/Olimpic X፣ ሆዲን ግሎባል ኤክስፕሬስ/Hodin Global Express፣ አማነ/Amaana፣ ሰሃል/Sahal የመሳሰሉት በኢትዮጵያ ቢሮ ከፍተው በገንዘብ ዝውውር ስራ የሚሰሩትን ድርጅቶች የዘረዘረው የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ የገንዘብ ዝውውሩ እንዴት እንደሚከናወን አመልክቷል።

ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካና ከአረብ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን የውጪ ምንዛሪ በማስተላለፍ ኮሚሽን የሚወስዱት ክፍሎች ራሱ ወጋገን ባንክ፣ ምንዛሪውን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ወጋገን ባንክ የሚያስተላልፉት የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችና እነዚህ ድርጅቶች ብር እየለቀሙ በወጋገን ባንክ በኩል እንዲላክ የሚያደርጉ ደላሎች ሲሆኑ ከሚተላለፈው ገንዘብ ሁሉም በጥቅሉ የሚካፈሉት የአምስት በመቶ (5%) ኮሚሽን አላቸው።

በዚሁ ስሌት መሰረት ወጋገን ባንክ ሁለት በመቶ (2%)፣ የገንዘብ አስተላላፊው ተቋም ሁለት በመቶ (2%)፣ ደላሎቹ ደግሞ አንድ በመቶ (1%) በዶላር ሂሳብ የሚታሰብና ባሉበት አገር ገንዘብ ተመንዝሮ የሚሰጣቸው ድርሻ አለቸው። ወጋገን ባንክ ዶላሩን በራሱ ሒሳብ (account) በታዋቂ አለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት ካስገባ በኋላ ከአምስት መቶኛው ድርሻውን ከመውሰዱ በተጨማሪ በያንዳንዱ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት (cashier) የሚሰሩ ሰራተኞችን በመመደብ ገንዘብ ለተላከላቸው ሰዎች በኢትዮጵያ ብር ክፍያ የሚያከናውነው ራሱ ነው።

“የሚላከው የውጪ ምንዛሪ በራሱ አካውንት ከገባለት የራሱን ገንዘብ ከፋይ ለምን ይመድባል?” በሚል ዘጋቢያችን ላነሳው ጥያቄ “ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶቹ ከዋናው ተልዕኳቸው ውጪ በማናቸውም የገንዘብ ማቀባበል ስራ እንዲሰማሩ አይፈለግም፤ አመኔታም የላቸውም። የሚላከው ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር በርካታ ስለሆነ ወጋገን ባንክ ከእስልምና ጉዳዮችና ከተለያዩ እንቅስቃሴዎች ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል የሚል ስጋት ስላለበትም ጭምር ተቀባዮችንም ለመቆጣጠር ጭምር ሲባል ነው…” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መልስ ሰጥተዋል።

አውሮፓ ተቀምጦ ገንዘብ በማሰባሰብ አንድ ከመቶ ኮሚሽን የሚወስድ አንድ የድለላ ሰራተኛ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሪፖርተር እንደተናገረው ስራ የለም ከተባለ እስከ ሃምሳ ሺህ ዶላር በቀን ወደ ወጋገን አካውንት የሚገባ የገንዘብ ሰነድ ለቀጠረው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት እንደሚልክ አስታውቋል።

የገንዘብ አዘዋዋሪ ድርጅቶቹ የሶማሌ ተወላጆች ቢመስሉም ከጀርባቸው ተቆጣጣሪና ሽርካ እንዳላቸው የጠቆመው ይህ ደላላ ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የሶማሌ ዜጎች ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በመላክ ወጋገን ባንክን እያደለቡት እንደሆነ አመልክቷል። ስሙ እንዳይገለጽበት የጠየቀው የሶማሌ ተወላጅ “የኢትዮጵያ መንግስት በኛ መስመር ብቻ በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጪ ምንዛሪ ከአውሮፓ ብቻ ያገኛል” ሲል ከቅርብ አለቆቹ የተነገረው እንደሆነ  በመጥቀስ ተናግሯል። በየቦታው የተበተኑት ደላሎች እንዴትና ማን እንደመለመላቸው በራሱ አነጋጋሪ መሆኑንም አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የወጪ ምንዛሪ እጥረት ችግር አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ከሌሎች ባንኮች በተለየ መልኩ ሸሪኮቹን እንደሚያሰተናግድ በመግለጽ በርካታ ባለሃብቶችና ተገልጋዮች ምሬት የሚያቀርቡበት ወጋገን ባንክ፤ ከኤፈርት ቀጥሎ “ከፍተኛ ባለድርሻ” በሚል የያዛቸው የብአዴኑ ኢንዶውመንት – ጥረትና የኦህዴድ የንግድ ድርጅት – ቱምሳ ኢንዶውመንት እንኳን ሳይቀሩ በወጉ እንደማይስተናገዱ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ምንጮች ይጠቁማሉ።

በተለይም ቱምሳ ኢንዶውመንት ማዳበሪያ ንግድ ውስጥ በመግባት የኤፈርት አንድ አካል የሆነውን አምባሰልን ከፍተኛ ገቢ ስለተጋራው ሆን ተብሎ ብድር እንዲከለከል በማስደረግ እዳ ታቅፎ እንዲቀመጥ መደረጉን የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች፣ ኦህዴድ በክልሉ እንኳ ማዳበሪያ መሸጥ እንዳይችል መደረጉ ህወሓት አጋር ፓርቲዎችን በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በገንዘብ ተቋሙ በኩልም ምን ያህል ባሪያ እንዳደረጋቸው ማሳያ እንደሆነ ይጠቁማሉ።

የህወሓት ንብረት በመሆኑ ብቻ በሚደረግለትና በሚመቻችለት የተለየ ጥቅም ከዋናው የአገሪቱ ባንክ ይልቅ “የኔ” ለሚላቸው ወዳጆቹና የስርዓቱ ደጋፊዎች ያለ ወረፋ የውጪ ምንዛሪ በማቅረቡ የባንኩ ደንበኛና የህወሓት አጋር ያልሆኑ አስመጪዎች እንቅስቃሴያቸው ሊፋዘዝ እንደቻለ የአዲስ አበባ የጎልጉል ዘጋቢ አመልክቷል። ባንኩ የሸፍጥ ንግድ ውስጥ መግባቱና የንግድ ውድድሩ እንዲዛባ ምክንያት ከመሆኑ ውጪ አገሪቱ ያጋጠማትን የውጪ ምንዛሪ እጥረት መቅረፍ የሚያስችል ሚና እንደሌለው ታዋቂ ነጋዴዎች አስተያየት መስጠታቸውን ዘጋቢያችን አክሎ ገልጿል።

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተበተኑ ኢትዮጵያውያኖች ለፍተው ለቤተሰቦቻቸው የሚልኩት የውጪ ምንዛሪ ተሰብስቦ በተለያዩ መንገዶች ህወሓት ጉያ ውስጥ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ቢገለጽም መንግስት ራሱ የሚያወጣቸው መረጃዎች ከዳያስፖራው የሚገኘው የመንግስት የውጪ ምንዛሬ ገቢ  ከዓመት ዓመት እየጨመረ መሄዱን ነው። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ድርቅ መመታቷን በቅርቡ ማስታወቁ አይዘነጋም።

(በጎልጉል ዘጋቢ)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በግለሰብ ስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. dawit says

    September 24, 2012 10:42 am at 10:42 am

    ስለ ቱምሳ ኢንዶውመንት ካነሳችሁ አንድ የማውቀውን ነገር ልጠቁም። ከንግድ ባንክ ብድር ወስዶ ማዳበሪያ ንግድ ጀምሮ ነበር። ቱምሰ በወቅቱ ቢፍቱ ትሬዲንግ በሚባለው አንዱ ቅርንጫፉ ማዳበሪያ ንግድ ውስጥ ሲገባ አምባሰል አኮረፈ። የማደፋበሪያ ንግድ በዱቤ ስለሚሰጥ እስከ ሁለተኛው የምርት ዘመን እዳው አይሰበሰብም ። ቱምሳ ከንግድ ባንክ ባገኘው ብድር ማዳበሪያ አስገብቶ ለገበሬው በብድር አደለ። ለቀጣዩ የምርት ዘመን ተጨማሪ ብድር ሲጠይቅ ተከለከለ። በዛው ከማዳበሪያ ንግድ ወጣ። ታሪኩ ብዙ ነው። ይህችን ያልኩት ታሪኩ እውነት እንደሆነ ለማሳየት ነው። በነገራችን ላይ ጎልጉሎች ለቤተሰብ የሚላክ ገንዘብ አምስት በመቶ አየር ላይ ከመበላት በቀጥታ በአዋሽ ባንክ፣ ንብ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ……. ካልሆነም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ራሳቸው የብር ማስተላለፍ ንግድ ውስጥ ቢገቡ ከገንዘብ ችግር ይላቀቃሉ የሚል ሃሳብ አለኝ። ለዜናው አመሰግናለሁ።

    Reply
  2. ELIAS says

    September 26, 2012 11:39 pm at 11:39 pm

    My comment is no comment for now!

    Reply
  3. amee says

    September 28, 2012 04:47 pm at 4:47 pm

    Its nice news!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule