• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ታላቅ ዕድል ነው!”

September 21, 2012 02:02 pm by Editor 4 Comments

ዛሬ አርብ ልክ ከጠዋቱ 3፡38 ላይ 374 የኢህአዴግ ወኪሎችና ኢህአዴግን እንደሚደግፉ በግልጽ የሚናገሩት አንድ በግል ያሸነፉ የፓርላማ አባል የሚገኙበት የተወካዮች ምክር ቤት አጨበጨበ። ጭብጨባውን ተከትሎ ኢቲቪ የቦሎ ሶሬውን ሰው አመላከተ። ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ በሟቹ አቶ መለስ የፓርላማ መቀመጫ ላይ የተሰየሙት አቶ ኃይለማርያም ፈገግታ አሳዩ። አስቀድሞ የተነገረው በትረ ሹመት ስርዓቱን አሟላ። አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ታወጀ።

ቀልጠፍ ቀልጠፍ እያደረጉ ስርዓቱን የመሩት አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ተገኔ ጌታነህን ጋበዙ። በሳቸው ትዕዛዝ ኃይለማርያም ቃለ መሃላ ለመፈጸም ቀኝ እጃቸውን አነሱ። ስማቸውን ጠርተው ማሉ።“…ከአገርና ከህዝብ የተጣለብኝን ሃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት፣ እንዲሁም ህግንና ስርዓትን ለመፈጸም ቃል እገባለሁ” ሲሉ ሲናገሩት ቀላል የሚመስለውን መሃላ በመልካም አስተዳደር፣ በሙስና፣ በድህነት፣ በዴሞክራሲ እጦት፣ በፍትህ ጥማት፣ ቀና መሪ በራበው፣ እስርና ስቃይ ባንገፈገፈው፣ የመሰብሰብና የመናገር መብት በተገፈፈ፣…… ህዝብ አቀረቡ።

3፡38 ላይ ሙሉ ጠ/ሚኒስትር የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ከአንድ ደቂቃ በኋላ “ ክቡር ጠ/ሚኒስትር” ተብለው ንግግር እንዲያቀርቡ ተጋበዙ። “የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች” በማለት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሙሉ ማዕረግ ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አስራ ስድስት ደቂቃ በፈጀው ዲስኩራቸው ቅድሚያ የወሰዱት ሹመታቸውን “ታላቅ ዕድል” በማለት ነበር።

አቶ መለስን በማሞካሸት የታጀበው የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር “… የኔ ድርሻ የአቶ መለስን ሌጋሲ/ውርስ/ ሳይበረዝ ማስቀጠል ነው” በማለት ወ/ሮ አዜብ ባለቤታቸውን በመስቀል አደባባይ ሲሸኙ የተናገሩትን ቃል በቃል አጣቅሷል። እያንዳንዱን ዘርፍ በመዳሰስ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት አቶ ኃይለማርያም በእርሻና በመስኖ ልማት የአገር ውስጥ ባለሃብቶችን ለመደገፍ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጡ ባሰመሩበት ንግግራቸው በጥንቀቄ ተዛልፈዋል።

ሹመታቸውን “ታላቅ ዕድል ነው” ያሉት አቶ ኃይለማርያም፤ ሙስናን አስመልክቶ ሲናገሩ በከፍተኛ ደረጃ ኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ወንጀል የሚፈጸምባቸውን ዘርፎች ዘርዝረዋል። የመሬት አስተዳደር፣ የታክስና ቀረጥ አሰባሰብ፣ የመንግስት ግዢ አሰባሰብናና የፍትህ አሰጣጥ ዘርፍን በዋናነት ነቅሰው በመጥራት “በሙስናና በስነ ምግባር ጉድለት የተለከፉ ሰዎችን በአግባቡ መስመር ማስያዝ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል። ህዝብ ያለማቅማማት ተባባሪ እንዲሆንም ጠይቀዋል።

ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ህዝቡን በማርካት ማገልገል እንደሚኖርባቸው ያሳሰቡት አቶ ኃይለማርይም፤ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማትና ህግን አክብረው ከሚሰሩ ካሉዋቸው የተቃዋሚ ፓርቲዋች ጋር አብረው እንደሚሰሩ ቃል ከመግባት ውጪ መንግስታቸው ተቋማዊ ለውጥ ለማድረግ ስለማሰቡ የተነፈሱት ነገር የለም።

በነጻነት እጦት ስለታፈነው የነጻው ፕሬስ በደምሳሳው አብረን እንሰራለን ከማለት ውጪ በበጎም ሆነ በመልካም ጎኑ ምንም ሳይናገሩ አልፈውታል። የመልካም አስተዳደር ችግር ሮሮ እንዳለ በማውሳት ህዝብን በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን እንደሚያከብርና ጣልቃ እንደማይገባ አውስተው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

አቶ መለስን መስለው ባስተላለፉት ማሳሰቢያ በሃይማኖት ስም የሚደረግን ማናቸውም ዓይነት የሽብር ተግባር እንደማይታገሱ በግልጽ አስቀምጠዋል። ተግባሩንም “በቀጥታ ከህገ መንግስት ጋር የሚያላትም ነው” ብለውታል። በማንኛውም ሽብር ነክ ጉዳዮች ላይ መንግስታቸው ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ ያሳሰቡት አቶ ኃይለማርያም ሽብር ነክ ስላሉዋቸው እንቅስቃሴዎች አላብራሩም። ይልቁኑም ኢትዮጵያን ከማንኛውም አይነት ጥቃት የሚከላከል የመከላከያ ሃይል መገንባቱን በማውሳት “ከህዝባችን ጋር በመሆን ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላማዊና የተረጋጋች አገር መሆኗን አስመስክረን እንቀጥላለን” በማለት የመከላከያ ተቋማት ይበልጥ ሳይንሳዊ የሚሆኑበት አቅጣጫ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስገነዘቡት።

አዲስ ካቢኔ ስለማቋቋማቸው ዝምታን የመረጡት ጠ/ሚ/ሩ “የባንዲራ ፕሮጀክት” በሚል ስያሜ የሚጠራውን የአባይ ግድብ ከተያዘለት እቅድ አስቀድሞ ለመጨረስ ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ እንዲቆም ጫና ስለመኖሩና ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም ስላጋጠመው የገንዘብ እጥረት ግን ያወሱት ነገር የለም።

የዋጋ ግሽበትን ለማርገብ ከዘንድሮው የምርት ዓመት የተሻለ ምርት እንደሚገኝ በማመልከት መልካም ምኞት ከማስተላለፍ ውጪ ግሽበቱን ለማቃለል በተለይ ስለሚተገበር ጉዳይ ያላብራሩት አቶ ኃይለማርያም በሌላ መልኩ በአገሪቱ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ለማድረግና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በእርሻ ስራ እንዲሳተፉ እገዛ እንደሚደረግ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸው በዛሬው ንግግራቸው ውስጥ ታላቁ ቁም ነገር ተብሎላቸል።

የመስኖ እርሻን ስለማስፋፋትና ሰፋፊ እርሳዎች በአገር ተወላጆች እንዲጎለብት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የተናገሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም እየተቸረቸረ ስላለው አገሪቱ ለም መሬት ጉዳይ አቋማቸውን አላሳወቁም። በርካቶችን እያፈናቀለ ያለው የመሬት ወረራ የደም ዋጋ እያስከፈለ ያለ ከመሆኑም በላይ ምርቱ አገር ውስጥ እንዲውል የሚደረግ አለመሆኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰነዘርበት የቆየና አሁን ድረስ መልስ ያላገኘ ጉዳይ ነው።

ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ የብአዴን ሊቀመንበርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ደመቀ መኮንን ለምክትል ጠ/ሚኒስትርነት አቅርበው አሹመዋል። አቶ ደመቀ ልክ እንደ አቶ ኃይለማርያም ቃለ መህላ ፈጽመው ሹመታቸውን አጽንተዋል። በቀጣይ ከሁለት ወር በኋላ ትግራይ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ ተለዋጭ መሪዎችን ካልመረጠ በስተቀር አቶ ኃይለማርያም በአሁኑ ሰዓት የደህኢዴን ሊቀመንበር፣ የኢህአዴግ ሊቀመንበር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የጦርሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ የሚኒስትሮች ምክርቤት ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ባለትልቁ ማዕረግ ናቸው። ህወሓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ለኦህዴድ በመስጠት የፖለቲካውን ክፍተት ቢሞላው የተሻለ እንደሚሆን አስተያየት እየተሰነዘረ ነው፡፡

(በጎልጉል ሪፖርተር )

የጎልጉል ኤዲቶሪያል ቦርድ ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ? በሚል ርዕስ ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያስተላለፈውን መልዕክት በርዕሰ አንቀጽ ገጻችን ላይ  ይመልከቱ። በመልዕክታችን “የእኛ ምክር መጀመሪያ እንደራሳቸው እንዲሆኑ፤ ቀጥሎም እንደ ፖለቲከኛ እንደ አክሊሉ እንደ ሃይማኖተኛ ደግሞ እንደ ዳንኤል እንዲሆኑ ነው፡፡ እርሳቸው ግን እንዴት እንደሚሆኑት ዛሬ ጀምረውታል፡፡ ሕዝብ ማስተዋል፤ ታሪክም መመዝገብ ጀምሯል” ብለናል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በግለሰብ ስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. micheal says

    September 21, 2012 05:15 pm at 5:15 pm

    sewuchu agendachewu lay wutate teteki tewulede ena addis hasabe yemibale neger ayfelgum megdel maser masadede morale ena tesfa maskorite yeker feker en aybtekrestiya yebandira fekre masetelate hobiyachewu adergewu hzebun tekam metekemiya bemaderg wodefite meketel chebechebawu
    yeketelale wutatenehe 21 setetagel +21 berbahulet kelhun endensu teyte kelchohe mesari kaletetkose lewute mamtate ayechalem yalewu manewu gezen lemitekem sewu and dekiga enkon tekem alate yehen mederge yemtechelewu tekmun selawuke becha sehone kawkute gga seterameden abre setesera becha newu GOD BLS

    Reply
  2. Zienamarqos says

    September 21, 2012 06:50 pm at 6:50 pm

    <<>>:- “ፍየል:ከመድረሷ:ቅጠል:መቀንጠሷ”::”የኔ ድርሻ የአቶ መለስን ሌጋሲ/ውርስ/ ሳይበረዝ ማስቀጠል ነው”::ብለው:የከሃዲዋን:ዓዜን:መስፍንን:ንግግር:ደገሙት:አይደል?::ለኢትዮጵያና:ሕዝቧ:እግዚአብሔር:ይሁናቸው::

    Reply
  3. fikir says

    September 21, 2012 10:30 pm at 10:30 pm

    ፍየል:ከመድረሷ:ቅጠል:መቀንጠሷ

    Reply
  4. Wore says

    September 21, 2012 11:06 pm at 11:06 pm

    ፍየል ከመድረሷ ጫት ቃመች
    ፍየል ከመድረሷ ጫት ቃመች
    ፍየል ከመድረሷ ጫት ቃመች

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule