ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው “ጥቁር ሳምንት” (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት “አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር” በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ “ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ … [Read more...] about ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ
News
ዜና
በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ
በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ በስደት አገራቸውን ጥለው የወጡ የኤርትራ ስደተኞችን እንደሚሰልል ተረጋገጠ። የስዊድን መንግሥት በደረሰው ጥቆማና ማስረጃ መሰረት ባደረገው ማጣራት ኤምባሲው በስለላ ስራ ተሰማርቶ ስዊድን ከለላ የሰጠቻቸውን የኤርትራ ተወላጆች አንደሚከታተልና እንደሚሰልል ማስረጃ ተይዞበታል። ተቀማጭነታቸው ስዊድን የሆነ የጎልጉል ተባባሪዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር እንዳመለከቱት፣ የስዊድን ዜግነት ያላቸውንና ሻዕቢያን ለማስወገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን የሚደግፉ፣ አክቲቪስት የሆኑትን የኤርትራ አገዛዝ በኤምባሲው አማካይነት እንደሚስልላቸው የታወቀው በጥቆማ ነው። ውስን ቁጥር ያላቸው በስዊድን የሚኖሩ የኤርትራ ተወላጆች ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት የስዊድን መንግሥት ባካሄደው ማጣራት የኤርትራ ኤምባሲ የተከሰሰበትን ተግባር እንደሚፈጽም ተረጋግጧል። የመረጃው … [Read more...] about በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ
የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ
አንጀሊና ጆሊ ኤግዚኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር የሆነችበትና ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር ሊመረቅ የነበረው ድፍረት ፊልም፣ በፍርድ ቤት እግድ ከተቋረጠ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማስነሳቱ ታወቀ፡፡ በአሜሪካ በሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫል ተሸላሚ ከሆነ በኋላ የፊልሙ በአዲስ አበባ መመረቅ በብዙዎች በጉጉት እየተጠበቀ ነበር፡፡ እንዲህ የተጠበቀው ፊልም ሊመረቅ በታሰበበት ዕለት ከአሥራ አምስት ደቂቃዎች በላይ ሊታይ አልቻለም፡፡ በብሔራዊ ቴአትር እየታየ ፌደራል ፖሊስ ደርሶ ሊያቋርጠው የግድ ሆኗል፡፡ ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የሚያጠነጥነው አስገድዶ የደፈራትን የ29 ዓመት ወጣት በገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ አበራሽ በቀለ (በፊልሙ ሒሩት) ሕይወት ዙሪያ ነው፡፡ ደፋሪዋ … [Read more...] about የታገደው ድፍረት ፊልም የይገባኛል ጥያቄ አስነሳ
ቱሪዝም ቢሮ የቀድሞ ውሳኔውን በመሻር ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃ ቅርስ አይደለም አለ
የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጥንታዊው የሼክ አህመድ ሳለህ አልዛህሪ (ሎምባርዲያ ሬስቶራንት የሚገኝበት) ሕንፃ ቅርስ መሆኑን በባለሙያዎች አረጋግጦ ክብካቤና ጥበቃ እንዲደረግለት ሲያሳስብ ቢቆይም፣ ሰሞኑን ባወጣው ሰርኩላር ሕንፃው ቅርስ አይደለም በማለት የቀድሞውን ውሳኔ ሽሯል፡፡ ቢሮው ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ለአዲስ አበባና ዙርያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ጽፎ በነበረው ደብዳቤ፣ ሕንፃው ቅርስ መሆኑን ገልጾ በማስተር ፕላኑ በቅርስነት እንዲያዝ አስታውቆ ነበር፡፡ ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ከፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ከቅርስ ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ደረጃ ማውጣት ዳይሬክቶሬትና ከቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት፣ እንዲሁም ከራሱ ቢሮ በተውጣጡ ባለሙያዎች በዝርዝር ተጠንቶ የቅርስ መሥፈርት እንደሚያሟላ … [Read more...] about ቱሪዝም ቢሮ የቀድሞ ውሳኔውን በመሻር ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃ ቅርስ አይደለም አለ
ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች "እንሰጋለን" ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል። ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና … [Read more...] about ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
በአዲስ አበባ ያለው የመጸዳጃ ቤት ችግር ከልክ ያለፈና መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። ሐሙስ በወጣው የጋዜጣው ድረገጽ ላይ እንዳስነበበው ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ መገልገያነት የዋሉት መጸዳጃ ቤቶች 63 ብቻ መሆናቸውን ዘግቧል። አማራጭ ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማዋ ወደ መጸዳጃ ቤትነት እየተለወጠች መሆኗን በምሬት ገልጸዋል። ጋርዲያን “Wash Ethiopia Movement” የተባለ አገር በቀል ድርጅት ጠቅሶ እንደዘገበው በከተማዋ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤት እንደሚጠቀሙና መቀመጫ ባለው መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙት ከ25 ቤተሰቦች አንዱ ብቻ መሆኑን ተናግሯል። በዘገባው መሠረት የከተማዋ ባለሥልጣናት የዛሬ ዓመት ይገነባሉ በሚል የ100ሚሊዮን ብር ዕቅድ የተያዘላቸው መጸዳጃ ቤቶች እንዳሉ መናገራቸውን … [Read more...] about ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ። ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል። ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ … [Read more...] about አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና
የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል
የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም አዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ የአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ስልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ተቃውሞ … [Read more...] about የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል
የውሸት አባት 2ኛ ሙት ዓመት
ግንቦት 20፣ 1983ዓም መለስ ወይም ለገሠ ወይም አስረስ ወይም ዜናዊ ወይም … ትክክለኛ ስሙን በውል የማናውቀው ከነጭፍሮቹ ቤተመንግሥት ገብቶ ራሱን አጼያዊ ፕሬዚዳንት፣ ቀጥሎም አጼያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ … በማድረግ ከሾመበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኦፊሴል እንደ ሻማ ወይም እንደ ኩራዝ ተለኩሷል። አቀጣጣዮቹ ምስለኔዎች ከሻማና ከኩራዝ ከፍ ብለው ብርጭቆ የለበሱ ፋኖሶች ሆነዋል። ለመለስና ለጭፍሮቹ የሚያበሩ ፋኖሶቹም (ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ …)፣ ኩራዞቹም፣ ሻማዎቹም የበራላቸው ማሾዎች (ህወሃቶች) ሁሉም በአንድነት ዛሬ ላይ ደርሰዋል። ለኳሹም ተለኳሹም እያበሩ የአስለኳሹን ሁለተኛ ሙት ዓመት “እያከበሩ” ነው። በሌላ አነጋገር ለሙት መንፈስ እሣት አንድደው እየሰገዱ ነው። ተገድዶ እየነደደ ያለውን ሕዝብ፣ አዳዲሶቹ አስለኳሾች (የኃይለማርያም ደቦ አስተዳደር) ሕዝብን ሻማ … [Read more...] about የውሸት አባት 2ኛ ሙት ዓመት
በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል
ማለዳ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ አፈሳ ማድረጋቸውን የሪያድ ምንጮች ገለጹ። የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ የውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን … [Read more...] about በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል










