በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከቅርብና ከሩቅ ተጠራርተው ቅዳሜለት (ኅዳር 6/Nov. 15) በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ስብሰባ አድርገው ነበር። ውይይታቸው በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው ትብብር ለመገንባት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና የጋር እሴቶችን በመመርመር ላይ ያተኮረ ነበር። በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ያሰናዳው ጉባዔ ከተለያዩ ብሄሮች፤ ጾታና የሃይማኖት አባላት፤ እራሳቸውን እንደግለሰብ ወክለው የተሳተፉበት ነበር። ቅዳሜለት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በምትገኘው አርሊንግተን ቨርጂኒያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዊያን፤ በሀገራቸው ተቋማዊ አስተዳድር ባልተጠናከረበት መልኩ፤ ማህበረሰቦች ሊጫወቱት የሚገባቸው ሚና፣ እንዲሁም እርስ በርስ የመተባበር ሃሳቦች ላይ ያተኮረ ነው። የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በዋሽንግተን … [Read more...] about የማህበረሰብ ውይይት በኢትዮጵያ ዘለቄታዊ ሰላምና ትብብር
News
ዜና
“ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ የወረርሽኝ ኢንቨስትመንት!?
በተለያዩ ወቅቶች የሰውን ልጅ ከእንስሳ በማሳነስ የተፈጸሙ ወንጀሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች ይወጣሉ። በቤተ ሙከራ ውስጥ የሚፈበረኩትና ሆን ተብለው እንዲሰራጩ የሚደረጉት የበሽታ መነሻዎች የክቡር ሰው ልጆችን ህይወት በሚዘገንን ሁኔታ አራግፈውታል። አባት፣ እናት፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ አልፎ ተርፎ ትውልድ … የሰው ልጅ በሽታ ኢንቨስት ተደርጎበት፣ የሕዝብ ብዛት መቀነሻና የባዮሎጂካል ጦር መሣሪያ መመራመሪያ ተደርጓል፣ አሁንም እየተደረገ ነው፤ የበሽታ ማምከኛ መሞከሪያና ማፈላለጊያ ሆኖ ኖሯል። ዛሬም እየኖረ ነው። የሌላውን አገር ሕዝብ ከህይወት በታች፤ የራሳቸውን ግን ድርብ ህይወት እንዳላቸው አድርገው የሚቆጥሩት ምዕራባውያን እንደመልካቸው ለማሳመር የሚሞክሩት ታሪካቸው ለማመን የሚያስቸግር እና ለመቀበል የሚከብድ ፍትሕ ያልተሰጠባቸው “ወንጀሎች” አካሂደዋል፤ አሁንም በረቀቀ መንገድ እያካሄዱ … [Read more...] about “ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ የወረርሽኝ ኢንቨስትመንት!?
የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ
ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ነጭ … [Read more...] about የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ
“ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር "ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ" በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡ "ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ" እንዳዘጋጀ ያሳወቀው ትብብሩ የትግሉ ዓላማ ፍትሃዊ ምርጫ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጾአል፡፡ "ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል" ያለው መግለጫው በመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ፕሮግራሙ 6 ዋና ዋና ተግባራትን ለመፈጸም ዝርዝር እቅዶችን አውጥቶ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን … [Read more...] about “ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ
መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል
የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጥኚ እጥረቱ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ ከ20 ቀናት በፊት እያንዳንዱ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የውጭ ምንዛሬ ይሸጥ እንደነበር የተናገሩት ምንጮች፣ ከ20 ቀን ወዲህ ግን በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማንኛውም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥ በደብዳቤ (circular ዞሯል) ተከልክሏል፡፡ በመሆኑም አሁን ላይ ዜጎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቸገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ "በተለየ ሁኔታ የሚሸጥላቸው ሰዎች ከጉዞ ወኪላቸውና ከበላይ አካል ይዘውት በሚመጡት ደብዳቤ መሰረት ብቻ ነው ምንዛሬ ሊያገኙ የሚችሉት፡፡ ከዚህ ውጭ ግን እንደበፊቱ ማንም የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይችልም" ሲል አንድ የንግድ ባንክ ሰራተኛ … [Read more...] about መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል
“ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”
ቡርኪናፋሶን ያለገደብ ሲመሩ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ ለተጨማሪ ዓመታት ሥልጣናቸውን ለማራዘም ያደረጉት ሙከራ በመክሸፉ ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ገለጹ፤ ለአንድ ዓመት የመሸጋገሪያ መንግሥት ተመስርቶ ምርጫ እስከሚደረግ በሥልጣን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ሕዝቡና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን ይህንን የሚቀበሉበት ትከሻ እንደሌላቸውና የኮምፓዎሬ አገዛዝ አሁኑኑ መውረድ እንዳለበት በተቃውሟቸው እየገለጹ ነው፡፡ ከ27ዓመት አምባገነናዊ ሥርዓት በኋላ ቡርኪናፋሶ ወደ ሌላ አምባገነናዊ ሥርዓት ልትሄድ እንደምትች ተጠቆመ፡፡ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ቶማስ ሳንካራ ዘመን የመንግሥት ባለሥልጣንና የሳንካራ ወዳጅ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ፤ ቶማስ ሳንካራ ባልታወቀ ሁኔታ በመፈንቅለ መንግሥት ከተገደሉ ከዛሬ 27ዓመት ጀምሮ ቡርኪናፋሶን መግዛት ጀመሩ፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱን በመምራት የተሳተፉት ኮምፓዎሬ … [Read more...] about “ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”
አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል
የበር መብራት ማጥፋት ክልክል ነው፤ በሕግ ያስቀጣል “መውጫና መግቢያ ሰዓታችሁ መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” ነዋሪዎቹ ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ምሶሶ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ “አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ ይሆናል ብለው በገመቱት ላይ ቁጣቸውን ገልጸው ነበር፡፡ በተለምዶ ካታንጋ ወደሚባል ስፍራ ሄደው ገዳዩን አውጡ ብለዋል፡፡ መኪኖችን ሰባብረዋል፡፡ ካታንጋ ምንም ፍንጭ ሲያጡ ወደ ፊላሚንጎ አምርተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ፖሊስ የተወሰኑትን ይዟል፤ ያመለጡም አሉ፡፡ … [Read more...] about አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል
ተመስገን ደሳለኝ 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ቀን በዋለው ችሎት 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ ፍትህን ሲያሳትም የነበረውና ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው ማስተዋል ህትመትና ማስታወቂያ በ10 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥቅም 3/2007 ዓ.ም የመንግስትን ስም ማጥፋት፣ ህዝብን ማነሳሳትና የህዝብን አመለካከት ማናወጽ በሚሉ ሶስት ክሶች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን አሁን የተፈረደበት በትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በአንደኛው ክስ ነው ተብሏል፡፡ የጥፋነኝነት ክሱ በተነበበት ወቅት ግን ‹‹መንግስት ይገድላል፣ ያፍናል፣ ይጨቁናል ብሎ ጽፏል፡፡›› በሚል ጥፋተኝ ነው ተብሏል፡፡ አቃቢ ህግ የቅጣት ማክበጃ ያላቀረበ ሲሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ሆነ ጠበቃው የቅጣት ማቅለያ አላቀረቡም፡፡ በሌላ በኩል የጋዜጠኛው ጠበቃ አምሃ መኮንን ይግባኝ … [Read more...] about ተመስገን ደሳለኝ 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት
የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ
የአዲስ አበባ መስተዳደር ማዘጋጃ ቤት (ከንቲባ ጽ/ቤት) ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች ዛሬ በግምት ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ እርስ በእርሳቸው መታኮሳቸውን አስተዳደሩ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት በከንቲባው ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች በነበራቸው ግምገማ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት ከስብሰባው እንደወጡ እንደሆነም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ በከንቲባ ጽ/ቤት ፖሊሶች በተታኮሱበት ወቅት የአትክልት ተራን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኘው ማህበረሰብ በድንጋጤ ውስጥ እንደነበርና አብዛኛው ከተኩሱ በኋላ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ በማቅናቱ በከንቲባው ጽ/ቤት አካባቢ በርከት ያለ ህዝብ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡ ፖሊሶቹ በተታኮሱበት ወቅት ገላጋዮች መሃላቸው በመግባታቸው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና ይህም በግምገማው ወቅት … [Read more...] about የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ
የቴሌ “አገልግሎት” መስተጓጎል ከሳምንት በላይ አስቆጠረ
ኢትዮ ቴሌኮም ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የሞባይል ማስፋፊያ መጠናቀቁ ቢገለጽም፣ አገልግሎቱ አሁንም በሞባይል አገልግሎት ላይ የሚታየውን ችግር ሊቀርፍ ባለመቻሉ፣ በተለይ ሰሞኑን ከአገልግሎት ጥራት ጋር በተያያዘ ደንበኞች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ ችግሩ የተከሰተው በተወሰኑ ቦታዎች እንደነበረና በአሁኑ ወቅት ግን ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ይላል፡፡ በተለይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የከተማዋ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች፣ የሞባይል መቆራረጥና የጥሪ መስተጓጎል ከሳምንት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ባለፉት አምስት ቀናት ግን ችግሩ ይበልጥ መባባሱን አመልክተዋል፡፡ ካለፈው ዓርብ ማምሻውን ጀምሮ በሞባይል ስልኮች ለመጠቀም ከፍተኛ ችግር እንዳጋጠማቸው ጠቅሰዋል፡፡ የሞባይል ጥሪ … [Read more...] about የቴሌ “አገልግሎት” መስተጓጎል ከሳምንት በላይ አስቆጠረ










