ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነጭ ሰንደቅ አላማ ሲያውረበልብ፣ የማህበሩን አላማና በህዝብ ላይ አሉ ያላቸውን ችግሮች ለህዝብ ሲያስተዋወቅ የተያዘው አቶ ፋንታሁን ህዝብን ለማነሳሳትና አመጽ ለመቀስቀስ ሙከራ በማድረግ በሚል እንደተከሰሰም ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ ፋንታሁን እሁድ ጥቅምት 23 ሽሮ ሜዳ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲበትን ተይዞ ላዛሪስት በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ታስ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ (ምንጭ እና ፎቶ: ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia)
በለው ! says
አቶ ፋንታሁን ህዝብን ለማነሳሳትና አመጽ ለመቀስቀስ ሙከራ በማድረግ በሚል ተከሰሰ:
“ነጭ ሰንደቅ አላማ ሲያውረበልብ፣ ለሕዝብ በሰጠው በራሪ ወረቀቱ ላይ፡_
* የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣!
*መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣!
* በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆም!
*መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ!
የሚመክሩ ሀሳቦችንና የማህበሩን አላማና ለህዝብ ሲያስተዋወቅ ነው።አራት ነጥብ።
*******************!
***መንግስት ያሠረው በበራሪ ወረቀቱ ላይ ያለውን ፈፅሜአለሁ ምንአገባህ ብሎ ነው?
***በሕገመንግስቱ ይህ ለገዢው ፓርቲ ብቻ ይፈቀዳል ብሎ ነው?
***ይህንን ድርጊቴን ህዝብ የመቀበል ግዴታ አለበት ብሎ ነውን?
***ሕዝቡ እየተሰደበ እየተረገጠ በትናንሽ ጥቅማጥቅም ተይዞ ይኖራልና ችግሩን አትንገረው ብሎ ይሆን?
***ይህ ሌላ አማራጭ የሌለው ሕዝብ በሙሉ ፍቃደኛነት ሊረገጥ ተስማምቷል ብሎ ነው?
*** ለእኛ በእኛ ሰው የሆነ ያለእኛ ምንም የማይሆን ግን ተበታትኖ የሚጠፋ ነው ብሎ ተማምኖ ይሆን?
*** በፈጣንና አሳላጭ መንገድ በቅፅበት የሚያድገው ከሕዝብ በላይ ከመንግስት በታች የሆነው ቡድን ይሆን?
***የነጭ ባነዲራ ትርጓሜ ያልገባቸው ብጥብጥ ወዳድ(እነጭር ሲል አንወድም ይሆኑ?)
*** ይህ ጭፍን ደጋፊ(ተደጋፊ)…ጭፍን ተቃዋሚ(አቋቋሚ) ዕርቅ ሰላም አንድንት ኀብረት ያቃዣቸው ይሆኑ?
***በእርግጥም አውራው ገዢ ፓርቲ ተራራ ውጡና፣ ገደል አቋርጡና ጉልበቴን ፈትሹ ብሎ እየገፋ ይሆን?
*** መንቀሳቀስ፣ መዘዋወር፣ መሰለፍ፣ መሰብሰብ፣ በከልልና በክልከላ ከተለወጠ ዜግነት ቀርቶ በሊዝ መኖር ተጀመረ?
***በውስጥ የብሔርና ቋንቋ ብጥብጥ የቡድን መናቆር ትርፋማ የሆኑ ተደራጅተው አቆብቁበው እየጠበቁ ይሆን?
“ማንም ሰው በፖለቲካ አመለካከቱ አልታሰረም! ሊታሰርም አይገባም!ኢህአዴግ ከስሕተቱ ይማራል! ከተባለ..የሰላም ማኅበር ማቋቋምና የህዝብ ብሶትን ለመንግስት ማሳወቅ በየትኛው ሕግና ሰንደቅ ወንጀለኛ ያደርግ ይሆን?
_____ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ መከላከያ ለሕዝብ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት ከቆመ ይህንን የተበላሸ(የበሰበሰ) ሥርዓት መምከር ወይንም የከፋ ውጥንቅጥ ውስጥ ከመግባታችን በፊት ማንአለብኝነት፣ የህዝብ ንቀት፣አምባገነን፣ የወሮ-በላ ቡድን እንዲወገድ አስተዳደሩን በሠላም ተረክቦ ለፍትሀዊ አስተዳዳር ማስረከብ ሀገራዊ ቃለ-መሐላ ግዴታ የገባበት፣ ኀላፊነትም የወሰደበት ለግለሰብና ለፖለቲካ ፓርቲ ዕድገት፣ ብልፅግና ሳይሆን ለሕዝብ ሠላምና ደህንነት መሆኑን አይዘንጋ!። ሠላም ለሁሉም።