በእንግሊዝኛው አጠራር የዲፕሎማ/የዲግሪ ወፍጮ ቤት (diploma/degree mills) ይባላሉ፡፡ በርካታዎቹ ሠለጠነ በሚባለው ዓለም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ “ወፍጮ ቤቶች” የ“ትምህርት መረጃ” ለማግኘት በጣም ቀላል ነው፡፡ ዋናው መስፈርት አስፈላጊውን “የትምህርት ክፍያ” መፈጸም ብቻ ነው ፡፡ ከዚያ በወርቅ ቅብ የተንቆጠቆጠ “የባችለር” ወይም “የማስተርስ” ወይም “የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ.)” ዲግሪዎችን ማፈስ ነው፡፡ በቀጣይ የሚሆነው የ…ሚ/ር ወይም የ…ሚኒስትር ደኤታ ወዘተ መሆንና “በሹመት መዳበር” ነው፡፡ ከዚያ ህዝብ አናት ላይ "በስያሜ" ተቀምጦ መጋለብ ነው። ከዓመታት በፊት የአሜሪካው የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ምርመራ አካሂዶ ነበር፡፡ ያገኘውንም ውጤት ለእንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርብ “የወፍጮ ቤቶቹን” አሠራር በግልጽ ዘርዝሯል፡፡ ለምርመራው ያነሳሳው … [Read more...] about “የዲግሪና የዲፕሎማ ወፍጮ ቤቶች”
News
ዜና
ሰማያዊ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ
ምርጫ ቦርድ በጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ “ጥያቄዎቻችን የሚመልስ አይደለም” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ በተጨማሪም የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በትናንትናው ዕለት ከምርጫ 2007 ዓ.ም በፊት ውይይት ሊደረግባቸውና ሊፈቱ ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎች ለምርጫ ቦርድ ያስገቡ ቢሆንም በዛሬው ስብሰባ በደብዳቤ ካሳወቋቸው ችግሮች ይልቅ የጊዜ ሰሌዳ ቅድሚያ የተሰጠው በመሆኑ የምርጫ ምህዳሩን ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ስብሰባውን ረግጠው ከወጡት መካከል የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ዋና … [Read more...] about ሰማያዊ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ
“ለእገሌ ሚ/ር እናገራለሁ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለሁ እያሉ አያስፈራሩን”
“አማካሪዎቼ ዓላማዬን የሚጋሩና የሚያስፈፅሙልኝ ሰዎች ናቸው፤” አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተጠርቶ የተካሔደው ስብሰባ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ወቅታዊ ሁኔታ የማይገልጽ፣ መዋቅሩን ያልጠበቀ እና ጽ/ቤታቸው የማያውቀው መሆኑን በመግለጽ ተቃወሙ፡፡ “የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ” በሚል ርእስ ከትላንት በስቲያ (መስከረም 29፤2007) በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሽ የግማሽ ቀን ስብሰባ በተደረገበት ወቅት፣ የፓትርያርክ አቡነ ማትያስን የመግቢያ ንግግር ተከትለው የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ “አሁን ወደ ስብሰባው ስገባ ነው መልእክቱን የሰማሁት፤ አጀንዳውም ከመቅረቡ በፊት ከቋሚ ሲኖዶሱ ወይም ከእኔ ጋራ ምክክር … [Read more...] about “ለእገሌ ሚ/ር እናገራለሁ፤ ለእገሌ ደኅንነት እደውላለሁ እያሉ አያስፈራሩን”
“መፈንቅለ ዓለም ባንክ!”
ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል የዓለም ባንክ በተለይ ከሲቪል ማኅበረሰቦች ጋር ሲያካሂድ የነበረው ስብሰባ “በመፈንቅለ ዓለም ባንክ” ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ መድረኮች በመወከል ድምጻቸውን የሚያሰሙት ኦባንግ “በመፈንቅሉ” ከተሳተፉት የዓለም ሲቪል ማኅበረሰቦች መካከል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነበሩ፡፡ የዓለም ባንክ ስለሚሰጠው ብድርና ዕርዳታ በተመለከተ ሊያካሂድ ያሰበው የፖሊሲ ለውጥ ሰነድ አፈትልኮ ከወጣ ጀምሮ በርካታ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሟገቱ ዓለምአቀፍ የሲቪል ማኅበረሰቦችን ያስቆጣ ሆኗል፡፡ የፖሊሲ ለውጡ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለው መልኩ ለታዳጊ አገራት ብድር ከመስጠት ባለፈ በተለይ አምባገነናዊ አገዛዝ በሰፈነባቸውና አገዛዞቹንም ለሚደግፉ ድርጅቶች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ገንዘብ መስጠትን የሚፈቅድ ነው፡፡ በዚህ አሠራር መሠረት ማንኛውም … [Read more...] about “መፈንቅለ ዓለም ባንክ!”
48 + 1 ደቂቃ ቢያልፍ ምን እንደሚከተል ግንዛቤ ነበር
ከስያሜው ጀምሮ እያነጋገረ ያለው የኢህአዴግ የአሜሪካ ጽ/ቤት የጥበቃ ሰራተኛ፣ በኢህአዴግ አባባል “ዲፕሎማት” አገር ለቆ እንዲወጣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አንድ ደቂቃ ቢዘገይ ምን ሊከተል እንደሚችል አስቀድሞ ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ተጠቆመ። በስምምነቱ መሰረት ወዲ ወይኒ መባረሩ ከህወሃት ደጋፊዎችና አመራሮች ቅሬታ ማስነሳቱን አስመልክቶ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት “ወያኔዎቹ የተሰራላቸው ውለታ አልገባቸውም ማለት ነው” ሲሉ መደመጣቸውን የጎልጉል ታማኝ ምንጭ ተናገሩ። ለተቃውሞ ወደ ኢህአዴግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባመሩ ኢትዮጵያኖች ላይ ጥይት የተኮሰው የቀድሞው “ዲፕሎማት” ተመልሶ አሜሪካን መርገጥ እንዳይችል ተደርጎ የተባረረው በሁለቱም ወገኖች በተደረገ የውስጥ ስምምነት ነው። ለጉዳዩ እጅግ ቅርብ የሆኑ እንደገለጹት በአሜሪካው የምስጢር አገልግሎት (Secret … [Read more...] about 48 + 1 ደቂቃ ቢያልፍ ምን እንደሚከተል ግንዛቤ ነበር
ኦባንግ ስለ ሁለተኛው የአፍሪካ መሬት ነጠቃ
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በሥራ ጉዳይ እንግሊዝ አገር ተገኝተው የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሎንዶን የሚገኘው Minority Rights Group International ጽ/ቤት ባደረገላቸው ግብዣ ቃለምልልስ አድርገው ነበር፡፡ በቃለምልልሱ ወቅት ሁለተኛው የአፍሪካ የመሬት ነጠቃ እየተካሄደ እንደሆነ እና እንዲህ ዓይነቱ አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በእንግሊዝና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ዕርዳታና ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች መብት አይከበርም የሚባልበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ያለው እነዚህ ወገኖች መብት የሚባል ነገር እንደሌላቸው አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ እንደ ማስረጃም በጋምቤላ አካባቢ መሬታቸውን በግፍ እየተነጠቁ ለስደት፣ ለግዳጅ ሰፈራ፣ ይህንንም … [Read more...] about ኦባንግ ስለ ሁለተኛው የአፍሪካ መሬት ነጠቃ
ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?
ሰሞኑን ኢህአዴግ በፈለፈላቸው ድርጅቶች ታጅቦ የ"ባንዲራ ቀን" በሚል የመለስን ፈረጀ ብዙ ዝክር ሊደግስ ከወዲያ ወዲህ እያለ ነው። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ሲያነሱና ሲጥሉት የነበረውን ያገር መለያ ለፈጠራና ከጀርባው ተንኮል ያዘለ ዓላማቸው ሲሉ ቀኑ እንዲዘከር አድርገዋል፤ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደመሆናቸውም የታዘዙትን በሠንደቅ ዓላማው ላይ ጨምረዋል። በዚሁ የ"ባንዲራ ክብር" ሳይሆን በሌላ አህጉራዊ ክስተት ራሳቸው ያሰፉትን ጨርቅ ገልብጠው ባደባባይ ሰቅለውት ነበር። በወቅቱ ራሳቸው ያሰሩትን ባንዲራ አናትና ግርጌ መለየት ባለመቻላቸው ተወግዘውበታል፤ የትግራይን ቢሆን እንዲህ ያደርጉት ነበር ተብሎም ተጠይቋል። ባድመ ስትወረር "ደርግ ኢሰፓ" ተብለው ጎዳና ላይ የተጣሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ለዳግም ዘመቻ "እናት አገር ጥሪ" ሲተም በገጸ በረከትነት የተሰጠው ያደራ ቃል … [Read more...] about ውርደት! – መለስ ፣ ስብሃት፣ የኢህአዴግ ኤምባሲ ከዚያስ?
በህወሃት “የትግራይ ኩራት ተነክቷል” ባዮች አይለዋል
የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን "ከኋላ" አስከትለው ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያካሄዱት የፊት ለፊት ንግግር ያስደሰታቸውና ያስኮረፋቸው ክፍሎች አሉ። “በህወሃት መንደር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የመወከል ባለጊዜው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ምልክትና ተምሳሌት ነው” የሚሉት ወገኖች ቀደም ሲል ሲሰማ የነበረውን “የትግሬ ኩራት ተነክቷል” ስሜት በገሃድ ሲያንጸባርቁ ታይቷል። አስገድደው ከሚመሩት ህዝብ ይልቅ ለውጪው ዓለም በመስገድና በማጎብደድ ወደር እንደሌላቸው የሚነገርረላቸው አቶ መለስ ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ያገኙትን ዕድል አላገኙም። ከታላቋ አሜሪካ መሪ ጋር በግል የፊት ለፊት ወግ አላደረጉም። በተለያዩ መድረኮች ላይ በጅምላ ተገኝተው ከመጨባበጥና ውስን ቃላቶችን ሲለዋወጡ ከመታየቱ ውጪ ያላገኙትን ይህንን ዕድል አቶ ሃይለማርያም ማግኘታቸው … [Read more...] about በህወሃት “የትግራይ ኩራት ተነክቷል” ባዮች አይለዋል
በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል
በጋምቤላ ዞን በጎደሬ ወረዳ ነጋዴዎችና ሰፋሪዎች ከአካባቢው ተወላጅ የመዠንገር ጎሳ አባላት ጋር ተጋጩ። በግጭቱ ከ17 ሰባት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በግጭቱ የመዠንገር ዞን አስተዳዳሪና የጎደሬ ወረዳ ዳኛ ከነቤተሰቦቻቸው የግጭቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ግጭቱን ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ በጉዞ ላይ እንዳለ በተሰጠ መመሪያ እንዲመለስ ተደርጓል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለጎልጉል እንደገለጹት በወረዳው በመሬት ባለቤትነትና በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከመሀል አገር በመጡ ሰፋሪዎችና ነጋዴዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ዓመታትን አስቆጥሯል። የፌዴራል አገዛዙም ሆነ የክልሉ አመራሮች ችግሩ ሳይሰፋ ሰላማዊ መፍትሄ ባለማፈላለጋቸው ችግሩ ሊካረር ችሏል። ኢህአዴግ የሚከተለው በዘር ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ ለችግሩ … [Read more...] about በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል
ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!
በኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን እየከረረ የሚሄደው የጥላቻ ደረጃ ያሳሰባቸው “የህወሃት ወዳጆች” ህወሃት ለእርቅ እንዲነሳሳ የማግባባት ስራ እየሰሩ መሆናቸው ተሰማ። የአቶ መለስና “የህወሃት ወዳጅ” ወይም ቅርብ ናቸው የሚባሉት ራስ መንገሻ ስዩም ጉልህ ሚና ይዘዋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪዎች እንደዘገቡት ከሆነ በህወሃት መንደር እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑ ወገኖች በህወሃትና በተቀረው ህዝብ መካከል እየሰፋ የሄደው ጥላቻ መልኩን እንዳይቀይር ከፍተኛ ስጋት አላቸው። በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚሰማው ቅሬታና የተቋጠረው ቂም ማየሉ ያሳሰባቸው እኚህ ወገኖች ህወሃት ደጁን ለእርቅ መክፈት እንዳለበት በማሳሰብ መጎትጎታቸው እንጂ የእርቁ መሰረትና እርቁ የሚያካትታቸውን ወገኖች በዝርዝር አልገለጹም። “ኢህአዴግ ናቸው” በሚል የሚታሙት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ፓስተር ዳንኤል … [Read more...] about ህወሃት “በህወሃት ወዳጆች” ለእርቅ እንዲነሳሳ እየተሸመገለ ነው!










