• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

48 + 1 ደቂቃ ቢያልፍ ምን እንደሚከተል ግንዛቤ ነበር

October 11, 2014 03:28 am by Editor Leave a Comment

ከስያሜው ጀምሮ እያነጋገረ ያለው የኢህአዴግ የአሜሪካ ጽ/ቤት የጥበቃ ሰራተኛ፣ በኢህአዴግ አባባል “ዲፕሎማት” አገር ለቆ እንዲወጣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አንድ ደቂቃ ቢዘገይ ምን ሊከተል እንደሚችል አስቀድሞ ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ተጠቆመ። በስምምነቱ መሰረት ወዲ ወይኒ መባረሩ ከህወሃት ደጋፊዎችና አመራሮች ቅሬታ ማስነሳቱን አስመልክቶ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት “ወያኔዎቹ የተሰራላቸው ውለታ አልገባቸውም ማለት ነው” ሲሉ መደመጣቸውን የጎልጉል ታማኝ ምንጭ ተናገሩ።

ለተቃውሞ ወደ ኢህአዴግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባመሩ ኢትዮጵያኖች ላይ ጥይት የተኮሰው የቀድሞው “ዲፕሎማት” ተመልሶ አሜሪካን መርገጥ እንዳይችል ተደርጎ የተባረረው በሁለቱም ወገኖች በተደረገ የውስጥ ስምምነት ነው። ለጉዳዩ እጅግ ቅርብ የሆኑ እንደገለጹት በአሜሪካው የምስጢር አገልግሎት (Secret Service) እና የዋሽንግተን ከተማ ፖሊስ ወዲ ወይኒን ለማሰር ወስነው ነበር። ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት እነ አቶ ግርማ ብሩ “ጓዳቸውን” ፈቅደው ለማሰናበት ቅድሚያውን በመውሰዳቸው ተጠርጣሪው ወንጀለኛ ሳይያዝ ቀርቷል። ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት (State Department) የተሰጠው መግለጫም ቃል በቃልም ባይሆን ይህንኑ ያረጋገጠ ሆኗል።

የምስጢር አገልግሎቱም ሆነ የከተማው ፖሊስ ከ“ፖለቲካው ግንኙነት” ጋር በተያያዘ ስለሚፈጠረው የፖለቲካ ውዝግብ ቁብ እንደሌለው ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አቶ ግርማ ብሩ “በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ተነጋግረናል” ሲሉ ለአገዛዙ ተላላኪ ድረገጽ ባለቤት እንዳረጋገጡት የስቴት ዲፓርትመንት ሰዎች የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ያልተፈረደበትን ወንጀለኛ፣ ወዲ ወይኒን፣ ካገር የሚወጣበትን መንገድ እንዳመቻቹ ዲፕሎማቱ አልሸሸጉም።

“አሜሪካ በቂ ጥበቃ አላደረገችልንም” በማለት ተቃውሞ የሚሰነዝሩት አፍቃሪ ህወሃቶች የሚሰነዝሩትን ተቃውሞ አስመልክቶ “የተደረገላቸውን ውለታ ካለመረዳት ነውነው፤ አፋቸውን ቢዘጉ (ዝም ቢሉ) የተሻለ ነው” ሲሉ የተደመጡት ከፍተኛ ሃላፊ፣ ይህንን ሲናገሩ ክፉኛ ተበሳጭተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የአሜሪካ መንግስት ተወንጃዩ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሚዲያ ቁርስና ምሳ ሲሆን፣ ከዚሁ በጋር ከኢህአዴግ ጋር የሚነሳው ውዝግብና በምስራቅ አፍሪቃ በኩል ስለሚከወነው የፖለቲካ ጨዋታ ሲባል ጉዳዩ አሁን በተከናወነበት መልኩ እንዲጠናቀቅ መወሰኗን ከጉዳዩ ብዙ ርቀት የሌላቸው ክፍሎች አመልክተዋል። አቶ ግርማም ቢሆኑ “በዲፕሎማሲያዊ” ሲሉ ቋንቋውን ቢያስውቡትም ስምምነቱ ስለመኖሩ ከማሳበቅ ወደኋላ አላሉም።

በገደብ፣ በስምምነት የተቆረጠው 48 ሰዓት ቢተላለፍ ምን ሊከተል እንደሚችል ግንዛቤ በመኖሩ እነ አቶ ግርማ ወዲ ወይኒን አፋፍሰው ኢህአዴግ አለገደብ ወደሚገዛት አገር ልከውታል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንድ ደቂቃ ቢዘገይ “ወዲ ወይኒ ወህኒ ወርደው ወዲ ወህኒ የሚል ስም ይሰጣቸው ነበር” ሲሉ ከዲሲ አካባቢ አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡

ከኢህአዴግ ወገን አሁንም ዋሽንግተን ዲሲ ለተከራዩት ለጽህፈት ቤታቸው አሜሪካ ልዩ እንክብካቤ እንዲደረግ እየወተወቱ ነው። አሜሪካ ለዚህ ምንም ዓይነት የተለየ ጥበቃ የማታደርግ መሆኑ በተለያዩ መግለጫዎች የተነገረ ቢሆንም በህወሃት/የኢህአዴግ በኩል ጥያቄው እንዲነሳ ያደረገው መነሻ በድጋሚ ተመሳሳይ ውርደት እንዳይከሰትና ወደ ሌሎች አገራትም እንዳይዛመት ስጋት በመኖሩ ነው።

በተመሳሳይ ዜና ከአሜሪካ በሰዓታት ገደብ እንዲሰናበት የተደረገውና ተበደልን ባሉ ወገኖች ላይ ጥይት ሲተኩስ የነበረው ይኸው የትግራይ ተወላጅ ለሞራሉ በሚል ወደ ሌላ አገር ኤምባሲ ተዛውሮ እንዲሰራ አዲስ ምደባ እንደሚሰጠው የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ምንጮች አመልክተዋል። ከህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን ወጣ የተባለው ይኸው የአዲሱ ምደባ ጉዳይ ለወዲ ወይኒ “ተጋዳላይነት”፤ ለሌሎች ደግሞ “አለኝታነትን ለማሳየት” በሚል ታስቦ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule