የኢትዮጵያ ህወሓት ሰራሹ “ፌደራሊዝም” ወደ ተፈራው ቀውስ እየተንደረደረ መሆኑንን የሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች የተሰሙት ገና ከጅምሩ ነበር። በርካታ ባለሙያዎችና የተቀናቃኝ ፖለቲካ መሪዎች በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ቢገልጹም ተቀባይነት ሊያገኙ ባለመቻላቸው የጎሣና የብሄርተኛነት በሽታ እያደር ኢትዮጵያን እየበላት አሁን ያለችበት ደረጃ አድርሷታል። ችግሩ አለመስማትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዓላማ ያለው፣ በቅጥረኝነት አገሪቱን የማፈራረስ ተልዕኮ የማሳካት ጉዳይ በመሆኑ የመከሩ፣ የዘከሩ፣ ያስጠነቀቁ፣ ስጋታቸውን አደባባይ ያወጡ ዜጎች ወንድ ሴት ሳይባል ተፈጅተዋል። አገሪቱ ምትክ የሌላቸውን ልጆቿን እንድትከስር ተደርጋለች። ግድያውና አፈናው ብቻ ሳይሆን መላውን የአገሪቱን ህዝብ እርስ በእርስ ጎሣና ጎጥ ለይቶ እንዲናከስ እየተወተወተና እየተገፋ አገሪቱ ቆዳዋ በልጆቿ ደም እንዲለወስ ሆኗል። ዛሬ … [Read more...] about የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
Middle Column
የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ገና ከመነሻው በበረሃ ያወጣው ፕሮግራሙ በግልጽ እንደሚያመለክተው የህወሓት ዋንኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አዳክሞና በጎሣ ከፋፍሎ ትግራይን ታላቅ በማድረግ ሪፑብሊክ መመሥረት ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ይህንን ለማሳካት በኢትዮጵያ ውስጥ ያልፈነቀለው የጎሳ ድንጋይ የለም፤ ያላጋጨው ሕዝብ፤ ያላጋደለው ወገን የለም፤ ትግራይን ሳይጨምር! ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ሳያስበው አስፈነጠረው እንጂ የመለስና ዋናዎቹ የህወሓት መሥራቾች ዕቅድ ይህንኑ ለማሳካት እንደሆነ ሰሞኑን በተከታታይ በምናትመው የአቶ ገብረመድኅን ጽሁፍ በግልጽ የተቀመጠ ሐቅ ነው። የወቅቱ የፍጅት ዓላማ ደግሞ ኦሮሞን ከሶማሊ ወገኖቹ ጋር በማጋጨት የአገዛዝ ዘመኑን ማራዘም፤ ሁለቱን ጎሣዎች በማይረሳ ቂምና ጥላቻ ውስጥ ማስገባት፤ ይህንንም እስካሁን በሌሎቹ ጎሣዎች መካከል ከፈጠረው ጥላቻና ቁርሾ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያን ኅልውና አጥፍቶ … [Read more...] about የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን … [Read more...] about ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የቅማንት ጉዳይ!
ብዙ ወዳጆቼ ስለምንድን ነው የቅማንትን ጉዳይ ዝም ያልከው እያሉ በየቀኑ መልዕክት ይልኩልኛል፡፡ ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ቆጫት ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ጽንፍ ይዞ መሔዱን አማራጭ አድርጌ አላየሁትም፡፡ መሀል ሰፋሪ ለመሆንም አይደለም፡፡ ግና ዕውነታውን ይዘን ለሁሉም የሚበጀውን መከተል አስፈላጊ ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ እነኚህ ወዳጆቼ እንደሚሉት ዝም ብዬም አላውቅም፡፡ ነገርን ከሥሩ ውኃንም ከጥሩ እንደሚሉ ከሥር መሠረቱ ጉዳዪን መዘርዘር አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ የቅማንትን ጉዳይ መከታተል የጀመርኩት በ2003/4 ዓም ጀምሮ ነበር፡፡ ይህም የተፈጠረበትን አጋጣሚ ከዚሁ ላይ መግለጹ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ አይከል ከተማ እሜቴ አይከል የምትባል ዛፍ አለች፤ የሚገባላት ብጻት ብዛት ይኽ ነው አይባልም፡፡ ምርጥ ምርጡን ገብስማ ዶሮ ከጊወን … [Read more...] about የቅማንት ጉዳይ!
ኢትዮጵያ ያለ”ኢትዮጵያዊነት” ልትኖር አትችልምን?
በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በጣም ተወዳጁ ኤፍኤም ሬዲዮ ሸገር ነው ቢባል የሚያጣላን አይመስለኝም። ሸገር መፈክሩ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” የሚል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፖለቲከኞችም ይህንኑ መፈክር የንግግራቸው ማሳረጊያ ዓረፍተ ነገር እያደረጉት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ከመግለጫዎቹ ግርጌ “ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር” የሚል ዓረፍተ ነገር ያስቀምጣል። አዲሱ በእነሰይፉ ፋንታሁን እና ሠራዊት ፍቅሬ… የተከፈተው ኢትዮ ኤፍኤም ሬዲዮ “ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ” የሚል መፈክር ይዞ መጥቷል። በቅርብ ጌዜ ከተከፈቱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንዱ – ጄቲቪ – መፈክሩ “ኢትዮጵያዊነት መልካምነት” የሚል ነው። “ኢትዮጵያ” የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ዘፈን የአገር ውስጥ ሽያጭ ሪከርድ ሰብሯል። የሐበሻ ቢራ ማስታወቂያ ‘ኢትዮጵያዊነት’ የሚለውን ቃል ማዕከል ያደረገ እና ስለኢትዮጵያ ‘ገናና ታሪክ’ የሚያወሳ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ያለ”ኢትዮጵያዊነት” ልትኖር አትችልምን?
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!
“ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተለቀቁ ፍትሕ ይበየናል” “ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ውሳኔውን በመቀበል ለአገራቸው አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል” ኦባንግ ሜቶ “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ራይላ ኦዲንጋ በኬኒያ በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በርካታ ችግሮች የገጠሙትና በአገሪቱ ሕግጋት መሠረት ያልተካሄደ ነው ሲል የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ከመጀመሩ በፊት የኬኒያን ፖለቲካ በቅርቡ የሚከታተሉት ኦባንግ ሜቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማድነቅ “ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተደረጉ በምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን አፍሪካም የሕግ የበላነይትና ፍትህ ይሰፍናል፤ ሁለቱም ተወዳዳሪዎች፤ ራይላ ኦዲንጋ ከአመጽ ይልቅ በሥርዓት ጥቄያቸውን ለፍትሕ አካል በማቅረባቸው፤ ኡሁሩ ኬኛታ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ እገዛለሁን ማለታቸው የሚደነቁ ናቸው፤ … [Read more...] about ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!
የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ
ህወሓት በትግራይ ላይ የራሱን አቋም እንዲወስድ ተመክሯል በኢትዮጵያ ያለማቋረጥ ሲካሄድ ከቆየው ሕዝባዊ ተቃውሞ አኳያ በህወሓት የደህንነት ክፍል የተሰበሰበው መረጃ፤ አሁን ካለው የተቃውሞ ንቅናቄ የተነሳ የኢህአዴግ የገጠር መዋቀር በኦሮሚያና በከፊል የአማራ ክልሎች ሊፈርስ እንደሚችል አስታወቀ። ከሁኔታው አሳሳቢነት የተነሳ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች ቢኖሩም ህወሓት ትግራይን አስመልክቶ የራሱን አቋም እንዲወስድ ሃሳብ ተሰጥቶታል። ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ተስኖት ይገኛል። በተለይ “ባለራዕዩ መሪውን” ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ካስፈነጠረው ወዲህ ግምባሩ በአንድ መጓዝ፣ በአንድ መስማማት፣ በአንድ ማሰብ አቅቶት በተቃዋሚው መዳከምና በአንጋሾቹ አለሁ ባይነት … [Read more...] about የህወሓት/ኢህአዴግ የገጠር መዋቅር ሊፈርስ ይችላል ተባለ
ሕዝብ “በጠብመንጃ መገዛት በቃን” አለ!! ትውልድ እንዳመጸ ነው!
ለፖለቲከኞች እስር እውቅና የሰጡ “ፓርቲዎች” እየተደራደሩ - ሕዝብ እያመጸ ወዴት? “እንወክለዋለን” በሚሉት ሕዝብ ዘንድ እውቅና ያላቸው ተቀናቃኝ ፓርቲዎች እጅግ አነስተኛ እንደሆኑ ይነገራል። አብዛኞቹ በምርጫ ቦርድ እውቅና ያገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጥቂት” ከተሰኙት ውጪ ስለመኖራቸው እንኳን እንደማይታወቁ በተደጋጋሚ አስተያየት ይሰጣል። እነዚህን ፓርቲዎች ሰብሰቦ ድርድር መቀመጥ የአገሪቱን ችግር ማስተንፈስ እንደማይቻል የሚከራከሩ ወገኖች ድርድሩን አያከብሩትም። በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ እዚህ ደረጃ መምጣቱ በራሱ አንድ ርምጃ ነው የሚሉና ድጋፋቸውን የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም። በውጤቱ ሲታይ ግን አመጹም፣ ቅሬታውም፣ ችግሩም መልኩን ሲቀያይር እንጂ ሲለዝብ ማስተዋል አልተቻለም። ለዚህም ይመስላል የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ “ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር … [Read more...] about ሕዝብ “በጠብመንጃ መገዛት በቃን” አለ!! ትውልድ እንዳመጸ ነው!
የህወሓት “መከላከያ ሰራዊት” በበቃኝ ጥያቄ ተወጥሯል፤ ጄኔራሎች አሉበት!
ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ህወሓት የሚመካበትን የታጠቀ ሰራዊት የሚመሩ ከፍተኛ መኮንኖችና ጄኔራሎች በጡረታ ለመሰናበት ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። የአስቸኳይ አዋጁ ሲነሳ መልስ እንደሚያገኙ ቃል የተገባላቸው እንዳሉም ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ለደህንነት ሲባል መረጃውን ያገኘበትን ሳይገለጽ እንደጠቆመው “መከላከያ ሰራዊት” የሚባለውን የህወሓት ሥልጣን አስጠባቂ የታጠቀ ኃይል ከሚመሩት ጄኔራሎች መካከል “በቃኝ” ያሉት ጄኔራሎች ከሰባት በላይ ሲሆኑ፣ በከፍተኛ መኮንን ደረጃ ያሉት ግን ቁጥራቸው በርከት ያለ ነው። ጄኔራሎቹ ሰራዊቱን ለመሰናበት ያቀረቡትን ዋና ምክንያት የመረጃ ሰዎቹ ቃል በቃል ይፋ ባያደርጉም፣ ከሰራዊቱ ጋር ላለመቀጠል ዕድሜ፣ ጤና፣ ጋብቻና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎችን እንደ ምክንያት አቅርበዋል። መልቀቂያ ያስገቡት ብቻ ሳይሆኑ በርካቶች ተመሳሳይ ፍላጎት … [Read more...] about የህወሓት “መከላከያ ሰራዊት” በበቃኝ ጥያቄ ተወጥሯል፤ ጄኔራሎች አሉበት!
የግፍ ለከት አልባው ህወሓት
የፌዴሬሽን ምክር-ቤት የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ የሚባለው ኮሚቴ እንደግዴታው "ተርጉሞ" መመለስ የነበረብትን ሠነድ ባለመመለሱ የ3 ወር (ጥቅምት 2010) ተለዋጭ ቀጠሮ ለዶ/ር መረራ ጉዲና ተሰጥቷል - የህወሓት ግፍ ለከት የለውም። ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የግፍ ለከት አልባው ህወሓት










