አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው "ሬት" ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ "ክፉ ጠረን" አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ። "… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም … [Read more...] about የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ?
Politics
አቶ ኦባንግ ሜቶ እስራኤል ገቡ
የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት አቶ ኦባንግ ሜቶ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር በ21/06/2013 እስራኤል በሰላም ደርሰዋል፡፡ በወቅቱም የማህበሩ አባላት በቤንጎሪዮን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በ22/06/2013 የሚካሄደውን ጉባኤ አጠቃላይ ስነ ስርአት የያዘ ዘገባ በተከታታይ የምንልክ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ የአቀባበሉ ሥነስርዓት ምስል ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ከሰላምታ ጋር ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር ሊ/መንበር … [Read more...] about አቶ ኦባንግ ሜቶ እስራኤል ገቡ
“Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights”
Testimony before the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations Date: June 20, 2013 Given by: Mr. Obang O. Metho, Executive Director Solidarity Movement for a New Ethiopia “Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights” I would like to thank the Chairman of the Committee on Foreign Affairs, Congressman Edward Royce, and all ranking members of the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and … [Read more...] about “Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights”
አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም "ዘርፈው አስቀመጡት" የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት … [Read more...] about አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?
አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!
ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !! "We are just leaving barbarism and are still entirely at the beginning. The French, however have already gone a piece of the way and have a century`s lead in every respect.” Friedrich the Great II to Wilhelm of Prussia መግቢያ የወያኔን አገዛዝ ነፍስ ለመዝራት፣ ወይንም የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የሚደረገውን በአንዳንድ ምሁሮች የሚነዛውን የማያስፈልግ አጻጻፍ ትተን፣ እስከዛሬ ድረስ በተለይም ብዙዎቻችንን ያሰጨነቀንና የሚያስጨንቀን፣ የቀድሞዎቹ አገዛዝም ሆነ ወያኔ ያተራመሰውን አገር እንዴት መገንባት አለብን ? የሚለው ሳይሆን፣ እሱን አስወግዶ እንዴት ስልጣን መያዝ … [Read more...] about አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!
“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ ቅድሚያ አቶ መለስ ድንገት አልታመሙም። በሽታቸው የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ምስጢርም አይደለም። ለዚሁ እኮ ነው ቤተ መንግስት ውስጥ በአዋጅ የተፈቀደላቸውን ቤት አሰርተው በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠሩ ለመኖር ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበረው። በዚህ ቢስተካከል ለማለት ነው። መለስ ለኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ሁሉ የጋራ ነጠብ ናቸው። በድልድይም ይመሰላሉ። በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተለይም … [Read more...] about “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
“የኢህአዴግ እብሪትና ትዕቢት አገርንና ህዝብን የሚያጠፋ ነው”
ከቤንሻንጉል አማርኛ ተናጋሪ ዜጎችን በግፍ የማፈናቀሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል በአፋር የተከሰተው ርሃብ ተባብሷል -የሟቾች ቁጥር 22 ደርሷል ኢህአዴግ አድርባይነትን ከማጥፋት ራሱን ማጥፋት ይቀለዋል ርዕዮት ዓለሙ ሁለተኛ ዲግሪዋን እንዳትማር ተደረገች የመንግስትን ዘር ማፅዳት ዘመቻ ማስቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነው ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ … [Read more...] about “የኢህአዴግ እብሪትና ትዕቢት አገርንና ህዝብን የሚያጠፋ ነው”
ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል አንድ)
የጎጆዎቻንን ገመናስ እንሸፍንበት ገዶን አያውቅም፤ ድሮ በደህናው ጊዜ፣ ኑሮ ርካሽ በነበረበት ዘመን፣ ኑሮ ከሀገራችን እድገት ጋር እንዲህ አብሮ ሳያድግ፣ የጋገርነውን የዘንጋዳ ቅይጥ፣ ባሰጣነው ማኛ፣ እርቃናችንን በሰልባጅ እንሸፍነው ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን እንደየአቅማችን ገመናችንን እንሸፍንበት አልገደደንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መሶባችን ባዶ ሆኖ የሚበላ ቢጠፋ፣ ጦም መዋላችንን እንሸፍንበት የከራረመ ስቴኪኒ ከጥርሳችን አይጠፋም፡፡ እንደርበው ጃኬት ባይኖረን፣ ቆዳ በሚያሻክር ብርድ ሙቀቱን እናማርራለን፡፡ አቦ የራስን ገመና ይሸፍኑበት መች ይገዳል! ሀገሬ የገደደው ያንቺ ገመና ይሸፈንበት መንገድ ነው፡፡ ሁሉም የጎጆውን ገመና ለመሸፈን ደፋ ቀና ሲል፣ የአንቺ ገመና እንደአዳል በግ ላት ተገልብጦ አረፈው፡፡ ለነገሩማ፤ አዎ ያስተማርሻቸው ልጆች አሉሽ፤ ህገ-መንግስትም አቁመሻል፤ ህግ … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል አንድ)
ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሁለት)
በቀደም ሳት ብሎኝ፣ ለ መጀመሪያ ልጄ ብቻ የፈረንጅ ሸራ ጫማ ገዝቼ ገባሁ። ያለወትሮዬ ማለቴ ለወትሮው ገበያ የምወጣው ሁለቱንም ልጆቼን ይዤ ስለነበረ ነው። ታዲያ ያን እለታ ማታ ትልቅዋ ልጄ ጫማውን ስትለካ፣ የታናሽ እህትዋ አይን ከሚለካው ጫማ ጋር ሲንከራተት ተመለከትኩ፤ ወይም የተመለከትኩ መሰለኝ። ከወደድሽው ላንቺም ይገዛልሻል አልኳት፤ የትንሽዋን ልጄን አይን እየሸሸሁ። በውስጤ አድሏዊነት ተላወሰ። በልጅትዋ ህሊና ውስጥ ይህ ስሜት እንደማያድር ባውቅም፣ የእኔን ሃሳብ ግን ቶሎ ላስወግደው አልቻልኩም። አየሽ ሀገሬ? እንኳን ህዝበ አዳምና ሔዋንን በእኩልነት ቤት ሆኜ አኖራለሁ የሚል ሀገር፣ አንድ ተራ ምስኪን ወላጅ እንኳን በጎጆው አድሏዊነት እንዳይሰፍን ይጥራል። አንቺ ግን ሀገሬ! … አንቺ ግን ዝሆንና ጥንቸል እያፋለምሽ ለአሸናፊው ታጨበጭቢያለሽ፤ ትሸልሚያለሽ። መቼም ማንም … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሁለት)
ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)
ሀገሬ አንዳንዴ ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ከምስራቅ ወደ ምእራብ የዘረጋሻቸውን ጎዳናዎች፣ ልታነጥፊያቸው ደፋ ቀና የምትይላቸውን ሀዲዶች ስመለከት ደስ ይለኛል። የአዲስ አበባን አስፋልትና በየአስፋልቱ ዳር ያቆምሻቸውን ህንፃዎች አዲስነት ስመለከት ደግሞ፣ ‹‹ቆይ ሀገሬ፣ መንገድም፣ ህንፃም አልነበራትም እንዴ?›› ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። እውነቴን ነው የምልሽ ሀገሬ ግንባታሽን ለተመለከተ ፈርሶ የሚሰራ ሀገር ነው እኮ የምትመስይው! ግን እኔ ልማትሽን፣ እድገትሽን፣ ትራንስፎርሜሽንሽን . . . አልነግርሽም! እንደነገርኩሽ ጉዳዬ ከገመናሽ ነው። ለልማት ለትራንስፎርሜሽንማ ራዲዮና ቲቪሽ መች አነሰሽ! ዋናው ራዲዮና ቲቪ አልበቃ ብሎ ኤፍ.ኤም፣ ኢቲቪ1፣ ኢቲቪ 2 . . . ልማትና እድገትሽ ራስምታትሽ እስኪሆን ይነግርሽ የለ! ነጋሪ ያጣው እኮ ገመናሽ ነው! እና እኔ ልጅሽ ልንገርሽ! በትልልቅ … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)