• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የ2005 ዋና ዋና ፖለቲካዊ ክንዉኖች

September 10, 2013 07:10 am by Editor Leave a Comment

የመለስ ዜናዊ አስተሳሰብና ምግባር ሕዝብን በተለይም ፖለቲከኞችን በተራራቀ ተቃራኒ ጫፍ እንዳቆሙ መሞታቸዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበጎ ወይም በመጥፎ፥ ወይም በሁለቱም መሐል-ክፉኛ መንካቱ እንደማይቀር ያኔ ተብሎ ነበር። አሁንም አልቀረም።

የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር ተሸኙ።

ሁለት ሺሕ አራትም ተሰናበተ። እና አዲስ ዓመት። ሁለት ሺሕ አምስት። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃና ጳጳሳት እና፥ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ማግስት የባተዉ ሁለት ሺሕ አምስት ካዲስ መሪ፥ ካዲስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሹመት ጋር አዲስ ተስፋ አጭሮም ነበር። ዓመቱ ዛሬ-አርጅቶ ሊሰናበት ሁለት ቀን ቀረዉ። የዓመቱን የኢትዮጵያ አበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች እየጠቃቀስን፥ ተስፋዉ መጠዉለግ-መፅደቁን፥ ላፍታ እንቃኛለን። አብራችሁኝ ቆዩ።

መለስ በተቀበሩ በሳምቱ ሁለት ሺሕ አምስት እንደ አዲስ ዓመት ሲብት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሺሕ የሚቆጠሩ እስረኞች በምሕረት መፈታታቸዉን የኢትዮጵያ መንግሥት ማወጁ፥ የአዲሱ ዓመት አዳዲስ መሪዎች አሮጌዉን ከፋፋይ መርሕ ከአሮጌዉ ዓመት ጋር ለማሰናበት ፍንጭ ማሳየታቸዉ መስሎ ነበር።

ከእስረኞቹ የመፈታት ዜና በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ጋር ለመደራደር መወሰኑን አስታዉቆም ነበር።ኦብነግ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ለረጅም ጊዜ ባሽባሪነት የወነጀለዉ፥ ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ ደግሞ ከአልቃኢዳ፥ ከአልሸባብ፥ እና ከሁለት ሐገር በቀል ድርጅቶች ጋር በሕግ-በአሸባሪነት የፈረጀዉ ቡድን ነዉ።semayawi rally

በዚሕም ሰበብ በመለስ ሞት ማግሥት አዳዲሶቹ መሪዎች ከኦብነግ ጋር ለመደራደር መስማማታቸዉን ሲያስታዉቁ፥ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ተስፋ ማጫሩ አልቀረም። በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ በኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር ሲራጅ ፈርጌሳና በኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ በአብዱረሕማን መሕዲ መካካል የተደረገዉ ድርድር እንዲደረግ የወሰኑት አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸዉ በፊት መሆኑ ሲነገር ግን ተስፋዉ የአዲሱ ዓመት ፀጋ፥ የአዲሶቹ መሪዎችም ብልሕነት እንዳልሆነ ግልፅ ሆነ። እስረኞቹ የተለቀቁትም በመለስ ዉሳኔ እንደነበር ተነግሯል።

የሁለቱ ወገኖች ተደራዳሪዎች በድርድሩ ሥነ-ሥርዓታዊ ጉዳዮች ተስማምተዉ፥ ለመስክረም ማብቂያ ለሁለተኛ ዙር ድርድር ለመገናኘት ተቀጣጥረዉ ነበር። መንግሥት አማፂዉ ቡድን ሕገ-መንግሥቱን ካልተቀበለ አልደራደርም በማለቱ፥ አማፂዉ ቡድን ቅድመ ሁኔታዉን ባለመቀበሉ ቀጠሮዉ-በቀጠሮ ቀረ። ተስፋዉም ቢያንስ ለዚሕ ዓመት ተጨናጎለ።

ተስፋ የማይቆርጠዉ ወይም ተስፋ ላለመቁረጥ፥ ተስፋ የሚያደርገዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ ተስፋ የሚያደርግበት ሰበብ ምክንያት አላጣም። የአዲሱ መሪዉ ቃል ዋናዉ ነበር። የአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን በጊዚያዊነት የያዙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነትቱን ሥልጣን በይፋ ተረከቡ።

መስከረም አስር። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኋላ እንዳሉት የዚያን ቀን ያደረጉትን ንግግር ፍሬ ሐሰብ ከማርቀቅ በስተቀር ንግግሩን የፃፉት ሌሎች ናቸዉ። ንግግሩን እንደ ኦጋዴኑ ድርድር ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የወሰኑት ወይም ፅፈዉ የተዉት ነዉ ማለት ግን አይቻልም።የንግግሩ ይዘት፥ ቃሉም ብዙ አዲስ አይደለም። ግን የአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ነዉ። የሐይለ ማርያም ደሳለኝ።

ሁሉም ተባለ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጥሪ፥ የነፃ ጋዜጠኞች አቤቱታ፥ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስሞታ፥ የሙስሊሞች ጩኸትም ቀጠለ። ታሕሳስ መባቻ። የአል-ጀዚራዋ ጋዜጠኛ አዲሱን የጠቅላይ ሚንስትር ጠየቀች።

muslims1«ሙስሊሞችን በተመለከተ በቀጠለዉ የተቃዉሞ ሠልፍ ምክንያት (እና በሌላም ምክንያት) በሐገሪቱ ዉስጥ ብዙ ችግሮች አሉባችሁ። በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል። ብዙዎቹ እንደሚሉት መንግሥት አህባሽ የተሰኘዉን የእስልምና (ሐራጥቃ) በሕዝቡ ላይ በሐይል ጭናችኋል፥ መንግሥት ሐይማኖቱን በሐይል ባዲስ መልክ ለመቅረፅ ጠንካራ እርምጃ ወስዷል ይላሉ። ጠንካራ እርምጃ ነዉ።»

ጠቅላይ ሚንስትሩ መለሱ።

«እንደሚመስለኝ ይሕ የአናሳዎች ድምፅ ነዉ። የአብዛኞቹ ድምፅ አይደለም። የአብዛኞቹ ሙስሊሞች ጥያቄ የራሳቸዉ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲኖራቸዉ ነዉ። መንግሥት በነሱ የአስተዳደር ሥርዓት ዉስጥ የሚያገባዉ የለም። ለሐይማኖት ያልወገነ መንግሥት ነዉ ያለዉ።ሕገ-መንግሥቱም መንግሥት በሐይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ይደነግጋል።»

ጥር ማብቂያ። ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ «በሐይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ያሉት መንግሥት የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት የሚታይ የሙስሊም መሪዎችን በአሸባሪነት የሚወነጅለዉን ፊልም አሰራጨ። ርዕስ፥ ጅሐዳዊ ሐረካት።

ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ለአል-ጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ በፖለቲካ ምክንያት የታሠረ አንድም ሰዉ እንደሌለ ተናግረዉ ነበር። ጥር ማብቂያ። ዓለም አቀፉ የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሑዩማን ራይትስ ዋች ባወጣዉ ዘገባዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከጥር ሁለት ሺሕ አራት እስከ ታሕሳስ ሁለት ሺሕ አምስት በነበረዉ አንድ ዓመት ብቻ ሰላሳ የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች በአወዛጋቢዉ የፀረ-ሽብር ሕግ ተወንጅለዉ እስራት ተበይኖባቸዋል።

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ከሞቱበት እስከ ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የዉጪ እና የሐገር ዉስጥ በሚል ለሁለት የተከፈሉት የሐይማኖት አባቶች ይታረቃሉ የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር። ድርድር፥ ዉይይትም ነበር። የካቲት-ሁሉም ቀረ። የሐገር ዉስጡ ሲኖዶስ የዉጪዉን ጥያቄ ዉድቅ አድርጎ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ሾመ።

ሚያዚያ፥ ምርጫና ጉብኝት ነዉ። መስከረም ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል ገብተዉ ነበር።

ሚያዚያ ላይ ሠላሳ ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከመንግሥትና ከገዢዉ ፓርቲ ይደርስብናል ያሉት ጫና እንዲቃለልላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሆነብን በሚል ከአካባቢያዊና ከከተሞች አስተዳድር ምርጫ እራሳቸዉን አገለሉ። ገዢዉ ፓርቲ እና ተባባሪዎቹ ብቻቸዉን ተወዳድረዉ አሸነፉ።

ጠ/ሚ/ር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፈረንሳይ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ብራስልስን፥ ሽትራስቡርግንና ፓሪስን የጎበኙትም ሚያዚያ አጋማሽ ነበር።

ግንቦት፥ የአፍሪቃ መሪዎች የአፍሪቃ ሕብረት የተመሠረተበትን ሐምሳኛ ዓመት አዲስ አበባ ዉስጥ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አከበሩ። መሪዎቹ በተሰናበቱ በሳምንቱ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ የተቃዉሞ ሠልፍ አዲስ አበባ ዉስጥ ተደረገ። ከ1997 ወዲህ ሕዝብ፥ መንግሥትን በመቃወም አደባባይ ሲወጣ የመጀመሪያዉ ነበር። ግንቦት ሃያ-አምስት።

በወሩ አንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ የጠራዉ ሠላማዊ የተቃዉሞ ሠልፍ ጎንደርና ደሴ ዉስጥ ተደረገ። የአደባባይ ተቃዉሞ ሠልፍ የማድረጉ ጥረት፥ ሙከራ፥ ዝግጅትም ቀጥሏል። የዚያኑ ያክል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደሚሉት በአባሎቻቸዉና በደጋፊዎቻቸዉ ላይ መንግሥት የሚፈፅመዉ እስራት እንግልትም አላባራም።udj rally

ግንቦትና ሰኔ፥-የኢትዮጵያንና የግብፅን የቃላት እንኪያ ሰላንታ እንዳሰሙን-ሐምሌ ተካቸዉ።

የአዉሮጳ ምክር ቤት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ባርባራ ሎኽቢኸር የመሩት የመልዕክተኞች ቡድን ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ነበር።

ሐምሌ – ቡድኑ ከመንግሥትና ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ እስረኞችን ለመጎብኘት ጠይቆ ተፈቅዶለት ነበር። ቃሊቲ ሲደርስ «ማን ፈቀደልህ» ተባለ።

የዘንድሮዉ ሐምሌ ለሙስሊሞች የቅዱስ ረመዳን ወር ነበር። የድምጻችን ይሰማ የመስጊዱ ተቃዉሞ ጩኸታቸዉ ግን አላባራም። በተቃዉሞዉ ሰበብ ከፀጥታ አስከባሪዎች የሚደርስባቸዉ ወከባ እስራት ዘረፋና ግፍም ብሶ ቀጥሏል። ለኮፈሌ፥ ለኢዶ፥ ለዋቤ፥ ለቆሬ ከተሞች ደግሞ የዘንድሮዉ ረመዳን የአሳዝኝ ግድያ ወርም ነበር።

ሐምሌ ማብቂያ ፀጥታ አስከባሪዎች በተሰበሰቡ ሙስሊሞች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሲያንስ አስር ሲበዛ ሃያ-ስድስት ሰላማዊ ሰዎች ገድለዋል። ኢድ-አልፊጥር የፌስታ፥ ደስታ፥ ታላቅ ዕለት ነዉ።የአዲስ አበባ ሙስሊሞች የዘንድሮዉን ረመዳን የፈጠሩት፥ ኢድን ያከበሩት የከብት፥ የበግ፥ የዶሮ ደም አፍስሰዉ ሳይሆን በፖሊስ ቆመጥ የራሳቸዉን ደም አዝርተዉ ነበር። ሁለት ጋዜጠኞችም ታስረዉ ነበር። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የጋዜጠኞቹን መታሰር አዉግዟል።

በዓለም ላይ በሸሪዓ ሕግ የሚገዙ ሁለት ሐገራት አሉ። ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ። ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ በኢድ አልፊጥር ማግሥት እንዳሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን በሸሪዓ ሕግ የምትገዛ ሦስተኛ ሐገር ለማድረግ ይጥራሉ።

ዘንድሮ- ሦስት ሚንስትሮች የተሻሩ፥ ከሦስቱ አንዱ ከተከታዮቻቸዉ በሙስና የታሰሩበት፥ አዳዲስ ሚንስትሮች የተሾሙበት፥ ኢትዮጵያ ባለ-ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ካቢኔ የሰየመችበትም ዓመት ነዉ። ዓመቱ በርካታ የህወሃት ቁልፍ ሰዎች እና የደኅንነት አመራሮች እንዲሁም አይነኬ ባለሃብቶች ከሥልጣናቸው እየተነቀሉ ሌሎችን ሲያጉሩበት በነበረው እስርቤት የተወረወሩበት ነው፡፡ የሙስናው መዘዝ ተመዝዞ መጨረሻው የት እንደሚደርስና ወደየት አቅጣጫ እንደሚነጉድ መጪው ዓመት ብዙ ያሳየናል፡፡ ዋናዎቹን የሙስና ሻርኮችንም ይደርስባቸው ይሆን ወይም አልፏቸው ይሄድ ይሁን አዲሱ ዓመት ያሳየናል፡፡(ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ፤ ዘገባው ለጋዜጣችን እንዲመች ሆኖ ለመታረሙ ኃላፊነቱን እንወስዳለን)

ለአገራችን ፍትሕ፣ ነጻነት፣ ሰላምና ዕርቅ እየተመኘን መልካም 2006 ለመላው ሕዝባችን!!

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule