• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሳውዲ ወላጆችና የኤምባሲ ኃላፊዎች ተካርረዋል

September 23, 2013 09:11 pm by Editor 4 Comments

ወላጆች ንብረቶቻቸውን ከዘራፊዎች ለማስጣል በሪያድ ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጋር እያደረጉ ያለው ትንቅንቅ ዛሬ ወደ ግጭት አመራ።

በወላጆች እና በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ በዲፕሎማቶች መሃከል ሴፕቴምበር 22፣ 2013 ምሽት ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ለጊዜው ጋብ ቢልም መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የተማሪዎቹ ወላጆች በተደጋጋሚ ላቀረቡት ጥያቄ አስቸኳይ መላምት ካላፈላለገ ጉዳዩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል የወላጆች ኮሚቴ አባላት ይገልጻሉ!

በተለይ ዛሬ ሴፕቴምበር 22/2013 ምሽት በሪያድ ዓለምአቀፍ የኮሚኒቲ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች ኮሚቴ የሳውዲ መንግስት በውጭ ሃገር ዜጎች ላይ ያወጣውን ህግ ተከትሎ በኤምባሲው የተመረጠው የት/ቤቱ ህገወጥ፣ የቦርድ አስተዳደር «የመኖሪያ ፈቃድ አልተሞላም፣ ፓስፖርት አልታደሰም፣ ቦንድ አልገዛችሁም፣ ወላጆቻችሁ የድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች ናቸው፣ … ወዘተ» በጣም አሳዛኝ እና ግብረገብነት በጎደለው ሰንካላ ምክንያት ከ1ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማፈናቀሉ ይታወሳል።

saudi3በመሆኑም የአያሌ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በሰው ሃገር ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀል የአብዛኛውን ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸው ተስፋ እንዲጨልም አድርጓ። ይህንንም የተረዳው 11 አባላት ያሉት የት/ቤቱ የወላጆች ኮሚቴ ከ1ሺህ የሚበልጥ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ኤምባሲው በራሱ ስልጣን መርጦ ህገወጥ በሆነ መንገድ ያስቀመጠው የት/ቤቱ ቦርድ አዲስ የትምህርት ዘመን መጀመርን አስመክቶ ያወጣውን የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች መመዝገቢያ መመዘኛዎች ትክክለኝነት በመጠራጠር ኮሚቴው የሳውዲ ት/ሚኒስቴር መ/ቤት ድረስ በመሄድ ለማጣራት ባደረገው ሙከራ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች በእጅ አዙር እንዳይመዘገቡ ታግደው ከነበሩ 1ሺህ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ውስጥ 8 መቶው የሳውዲ ት/ሚ ያወጣውን ህግ የሚያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ፡ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ኮሚቴው ማስቻሉን ተከትሎ ወላጆች በተጠቀሰው ቦርድ እና ከቦርዱ ጀርባ ሆነው በሪያድ ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤትን የመማር ማስተማር ሂደት እያመሰቃቀሉ ባሉ ወገኖች ዙሪያ ለመነጋገር ሴፕቴምበር 22 ፣2013 የወላጅ ኮሚቴው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደ ነበር የወላጆች ኮሚቴ ተወካይ ይገልጻሉ።

ተወካዩም በማያያዝ ቀደም ብለው ስብሰባ ያደርጉባቸው የነበሩ ቦታዎች ወላጆች በግል በሚከራይዋቸው አካባቢያቸው በሚገኙ የመዝናኛ ቦታዎች መሆኑንን ጠቀሰው በሪያድ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሃላፊ የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ይህ አዳራሽ እያለ ለምን ለድህነታችሁ አስተማማኝ ያልሆነ ቦታ ትሰበሰባላችሁ ከኤምባሲው እና ከኮሚኒቲው ርቃችሁ በድብቅ ስብሰባ ለምን ታደርጋላችሁ በሚል ቅን አስተሳሰብ ለወላጆ ኮሚቴው በሰጡት ሞራል እና ምክር ኮሚቴው ለእሁድ ቀን ሴፕቴምበር 22 2013 ከምሽቱ 7 ስዓት ጀምሮ ወላጆች በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ እንዲገኙ የስብሰባ ጥሪ በደብዳቤ እንደበተኑ ያወጋሉ።

እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ምንም አይነት ተቃውሞ ከኤምባሲው እንዳልነበረ የሚናገሩት የወላጅ ኮሚቴው ተወካይ በስበሰባው እለት ወላጆችን ለማስተናገድ ኮሚኒቲው አካባቢ ወንበሮችን ስናስተካክል ውለን ለተለዩ ጉዳዩች ከግቢ ወጥተን ስንመለስ የግቢው በር ያለወትሮው በቁልፍ ተቆልፎ ጠበቀን። ጉዳዩን ለማጣራት ዘበኛውን በመስኮት ስንጠይቅ በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን በተደገፈ ፊርማ በተጻፈ የደብዳቤ ትዕዛዝ መዘጋቱን ቢገልጽም በወቅቱ ጥሪ የተደረገላቸው ወላጆች ቁጥር እየጨመረ መምጣት አካቢው ተሽከርካሪ መተላለፊያ በመሆኑ ወላጆች ለአደጋ እንዳይዳረጉ ጠቅሰን በገዛ ቤታችን በር እንዲከፈትልን ብንማፀንም ዘበኛው ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ስለነበር ፈቃደኛ አልነበረም ብለዋል።

የኮሚኒቲው ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን መጥተው በቁጣ የሚጉርመረመውን ወላጅ ለማረጋጋት ሙከራ በማድረግ የኮሚኒቲውን በር እንደሚከፍቱ እና ህዝቡ እንደሚገባ ቃል ገብተው ዲፕሎማቱን አነጋግሬ መጣሁ ብለው ህዝቡን በር ላይ አቁመው በዛው መቀረታቸው አስነዋሪ እና አንድ የኮሚኒቲ ተወካይ ከሆነ አካል የሚጠበቅ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ከሰአታት ቆይታ በኋላ አልፎ አልፎ አምባሳደር መሃመድ ሃሰንን ወክለው እንደሚሰሩ የሚነገርላቸው ዲፕሎማት አቶ ዘላለም እና ቀደም ሲል በአዳራሹ እንደ ዜጋ መገልገል «መሰብሰብ» መብታችን መሆኑንን ምክራቸውን ሲለግሱ የነበሩ የዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር በወቅቱ ህዝቡን ለማነጋገር መጥተው እንደ ነበር ቢታወቅም የህዝቡ ስሜት ጥሩ አለመሆኑ መንገድ ላይ እያሉ መረጃ ስለደረሳቸው እና በአንዳንድ ትእግስታቸው በተሟጠጠ ወላጆች በገዛ ቤታችን እንዴት እንከለከላለን በሚል ቁጣ እና ንዴት ሊፈጸምባቸው የሚችለውን እርምጃ በመስጋት በት/ቤቱ የጓሮ በር ድምጻቸውን አጥፈተው በመግባት ህዝቡ ከአካባቢው እስኪበትን እዛው ባሉበት ድምጻቸውን አጥፈተው ለመቆየት መገደዳቸውን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።

በመጨረሻ የወላጆች ኮሚቴው ወደፊት ተመሳሳይ የሆነ ስብሰባ እንደሚጠራ ጠቅሷል፤ ህዝቡ እልህ ውስጥ ሳይገባ በሰከነ መንፈስ እና ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ አይን ባልገለጹ ሃገር ተረካቢ ታዳጊ ህጻናት ልጆቹ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት እና ንብረቱ የሆነውን በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት ከዘራፊዎች ለማዳን እያደረገ ያለውን ትግል አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመገስጽ የኢትዮጵያ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ስጥቶ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እስካላበጀለት ድረስ በዲፕሎማቱ እና በተማሪ ወላጆች መሃከል የተፈጠረው ግጭት ወደ ከፋ ደረጃ እንደሚሸጋገር አበክረው አሳስበዋል።

Ethiopian Hagere ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Negash says

    September 24, 2013 05:18 am at 5:18 am

    Dear editor,

    I was trying to read this story but it is written in such a confusing way that it is difficult to make sense. The basic rules of journalism — who, what where — are not followed. The story fails to make its point. I encourage you to edit future stories to make sense.

    Reply
    • Editor says

      September 24, 2013 06:58 am at 6:58 am

      Thanks for the comment, Negash. Just to give a feedback:
      who – በሪያድ ዓለምአቀፍ የኮሚኒቲ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች, በኤምባሲው የተመረጠው የት/ቤቱ ህገወጥ፣ የቦርድ አስተዳደር
      what – «የመኖሪያ ፈቃድ አልተሞላም፣ ፓስፖርት አልታደሰም፣ ቦንድ አልገዛችሁም፣ ወላጆቻችሁ የድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች ናቸው፣ … ወዘተ» በጣም አሳዛኝ እና ግብረገብነት በጎደለው ሰንካላ ምክንያት ከ1ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማፈናቀሉ,
      where – በሪያድ በሳውዲ አረቢያ
      .
      .
      .
      We think this may help answer your questions.

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      http://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  2. ሶጃት says

    September 25, 2013 09:33 pm at 9:33 pm

    ማስተካከያ ለውድ ዘጋቢ የመኖሪያ ፍቃድ ችግር የነበረባቸው 1000 ተማሪዎች ሳየሆኑ 300 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። የኮሚኒቲው ሊቀመነብር አቶ ሙስጠፋ መጥተው አረጋጉ ለሚለው አቶ ሙስጠፋ በሊላ ሊቀመንበር ከተተኩ ወደ አንድ ወር ይሆናል ስለተቀረው መረጃ ትክክለኛነት ፍርዱን ለአንባቢ ልተው…

    Reply
  3. mohamed abass says

    September 25, 2013 10:57 pm at 10:57 pm

    ምነው አቶ ሶጃት ! የስልጤው ተወላጅ ህጻናት ብቻ ናቸው እንዴ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት ተማሪ ። የኦሮሞ የአማር የትግሬ …….ወዘተ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ሲካተቱ እንደውም 1000 ይበልጣል። ሰሞኑን ት/ቤቱ ህገወጥ ቦርድ ያወጣውን የምዝገባ ማመዘኛ አታሞሉም ተበልው በልጆቻቸው ት/ቤት መመዝገብ ተስፋ ቋርጠው ሃገር ልጆቻቸውን የላኩትም ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያኖች መዘንጋት የለባቸውም ። ስለዚህ አቶ ሶጃት «አድበስብሰው ቢያርሱ በአረም የመለሱ ነው» እና ዲፕሎማቶቻችን በወገኖቻችን ላይ በእጅ አዙር እየፈጸሙ የሚገኙትን ሃጥያት ለማድበሥበስ አይሞክሩ። ኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ መብቶት ነው ግን አይን ባልገለጡ ህጻናት ልጆቻችን ሽፋን የዲፕሎማቶችን ፍቅር ለማግኘት እያሰሙን ያለው የማስተካከያ ጩሃት አፍንጫ ሲመታ ነው የሚሆነው » ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን አሃዝ ቀደም ብለው ረእስ መምህሩ በት/ቤታችን አሁን መንግስት ያወጣውን ማመዘኛ የማያሞሉ ተማሪዎች ቁጥራቸው ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን አሃዝ ሊደርስ እንደሚችል ስብሰባ ላይ በይፋ ተናግረዋል ። ሰሞኑንን በእርግጥ የወላጅ ኮሚቴው ባድረገው ጥረት 7 መቶ የሚያህሉት ተመዝግበው 3 መቶው ምንም የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በመሆኑ መላምት እይተፈለገላቸው መሆኑንን ከወላጅ ኮሚቲው መረዳት ይቻላል ። ምናልባት እርሷ ይህንን አሃዝ ማስቀመጥ ፈልገው ከሆነ አልተሳስቱም አለበልዚያ ግን አሁንም በየመንደሩ እጠቅሳለሁ « ነሲም አካባቢ መንፉሃ አካባቢ ነስሪያ አካባኢ ሙፉሃ አካባቢ …….ወዘተ ሰፈር ውስጥ በየቤታቸው የቀሩትን ህጻናት ያጠቃለለ አሃዝ በመሆኑ ከዚህ በላይ የቀረበው ሰዕላዊ መግለጫ እና የጽሁፍ መረጃ ትክክለኛ በመሆኑ ዜና አቅራቢዎችን ሊመሰገኑ ይገባል። ከተማሪ ወላጅ አንዱ « አቶ መሃመድ አባስ ሪያድ « ከመንፉሃ »

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule