• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ

September 17, 2013 04:10 pm by Editor 9 Comments

የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ እንደቀልድ እና እንደ እልህ የጀመሩት ”ኤርትራ ኢትዮጵያዊ አይደለችም” ብሎም ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አጀንዳን የሻብያ አጀንዳ እንዲሆን ካስደረጉ በኃላ ከእሳቸው በፊት የነበረው ትውልድ ባይቀበላቸውም የእሳቸውን ትውልድ ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚለውን ገለፃ ለመንገር አላንገራገሩም። አቶ ኢሳያስ በአንድ ጎናቸው ተንቤን ትግራይ ቢወለዱም ያነሷት ጉዳይ ግን ኢትዮጵያን ለማዳከም ለዘመናት ከሚያልሙ አንዳንድ የአረብ ሀገራትም ሆነ ጎረቤት ሱዳንን የሚያማልል ብሎም ዳጎስ ያለ ድጎማ የሚያስገኝ የወቅቱ አዋጪ ”የገበያ ማስታወቅያ” መሆኑን የተረዱት ይመስላሉ።

ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በነፃ ትምህርት ዕድል ይማሩ የነበሩት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ”የኤርትራ ነፃነት ግንባር” (ELF) ከመቀላቀላቸው በፊት በቻይና የፖለቲካ እና የወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ተጉዘው እንደነበር ተወስቷል። አቶ ኢሳያስ እና ድርጅታቸው ከሰላሳ አመት ውግያ በኃላ ”ሁሉ ነገር ተፈፀመ!” ብለው ተናግረው ሳይጨርሱ ሌላ ጦርነት ”በባድሜ መሬት ሰበብ” እውነታው ግን የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለመያዝ ከሕወሓትጋር በነበረ ግፍያ አዲስ ጦርነት ውስጥ ገብተው አስር ሺዎች ሲረግፉ አብረው ከአቶ መለስ ጋር ተዋናይ ሆነው ታዩ። ያ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” ያሉት ጉዳይ አስመራን ከያዙ በኃላም ጥያቄው ተወሳሰበባቸው።

አቶ ኢሳያስ እና ድርጅታቸው ሻብያ ስልጣን ከያዘ ሃያ ሁለት ዓመታትን አስቆጠረ። በእነኝህ ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ የኤርትራ ተወላጆችሲነገራቸው የነበረው ”የአፍሪካ ታይዋን ትሆናለች” ትንታኔ ሐሰት መሆኑን ተረዱት። ይልቁን ከአስመራ ዩንቨርስቲ ጀምሮ እስከ ቀድሞ በውሱን አቅም ይሰሩ የነበሩ ድርጅቶችን የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም ተዳከመ። በአስር ሺዎች በሱዳን፣በኢትዮጵያ፣በየመን አድርገው ተሰደዱ።ኤርትራ ከዲፕሎማሲ እስከ አካባቢ ሃገራት ድረስ እንድትገለል አደረጉ። የአቶ ኢሳያስ ”የዓለም እይታ ፍልስፍና” የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሆነ። እሳቸው አሜሪካንን የሚያዩበት እይታ የግል አስተያየት መሆኑ ቀረና የመንግስት ቃል አቀባይ የሚናገረው ”መዝሙረ-ኤርትራ” ሆኖት አረፈው። አምባገነንነት አስደናቂው እና አዝናኝ ገፅታው ይሄው ነው።መሪው ሲያስነጥሰው ሁሉም ለመሳል ጉሮሮውን ይጠራርጋል።

”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚለው የአቶ ኢሳያስ ትውልድ ጥያቄ ዛሬም ፈተና ላይ ነው።

አቶ ኢሳያስ እና ትውልዳቸው የወቅቱ ገበያን ስሌት ያደረገው ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አሁን በተነሳው ትውልድ የሚሞገትበት ጊዜ እሩቅ የሚመሰለው ካለ በሃሳቡ የመቀጠል መብቱን አከብራለሁ። ለእኔ ግን ይህ ጥያቄ በእራሱ የሚሞገትበት ጊዜ እንደሚመጣ አስባለሁ። የማኅበራዊ ትምህርት ሳይንስ ለምሳሌ የፖለቲካ ሳይንስ እንደ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ በቤተ-ሙከራ (ላብራቶሪ) ጥናት ውጤቱን ከወዲሁ ለመወሰን አይቻልም። የሚቻለው ነገር ካለፉት፣አሁን ካለው እና መጪውን ከመተለም አንፃር በምክንያታዊ አቀራረብ ከወዲሁ ሁኔታዎችን መመልከት ነው። ከእዚህ አንፃር የኤርትራ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሶስተኛው ትውልድ ላይ የወደቀ የእዚህ የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄም በእርሱ ታሪካዊ ሂደት የሚፈነዳበት ሁኔታ ይኖራል። የሶስቱ በኤርትራ ጉዳይ የተሳተፉ ትውልዶች ጥያቄዎች እንደዘመናቱ ”የፖለቲካ ገበያ አዋጭነት” እንደ አቶ ኢሳያስ ያሉ ተዋናዮች ተጫውተውበታል። ጥያቄው የሶስተኛውንም ትውልድ ጥያቄ አሁንም ”የፖለቲካ ገበያውን” ተመልክተው ጥያቄውን በመሞረድ የአቶ ኢሳያስ ቡድን ሊመራው ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ፈታኝ ነው። መልሱ አይመስልም ነው።

ሶስቱ በኤርትራ ጉዳይ ላይ የነበሩ ትውልዶች

የመጀመርያው ትውልድ

የመጀመርያው ከአቶ ኢሳያስ በፊት የነበሩት የጣልያን እና የእንግሊዝን ቅኝ ግዛት ግፍ የሚያውቁቱ ሲሆኑ ይህ ትውልድ ከ 1900 ጀምሮ እስከ 1960ዎቹ የነበረ ትውልድ ነው። በእዚህ ዘመን ውስጥ ኤርትራ መከራ ፍዳ በቅኝ ገዢዎች ማየቷን በአይን የተመለከቱ፣ የምስራቅ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን እንደህልም የሚያልሟት እና የሚወዷት ኢትዮጵያ ክፉ እንዳይነካት እንደ አይን ብሌን  የሚሳሱላት ትውልድ ነበሩ። ይህ ትውልድ በግድም ይሁን በውድ በጣልያን የባንዳ ሰራዊት ውስጥ ገብቶ እስከ ሊብያ እና ኢትዮጵያ የዘመተ ቢሆንም ”ኢትዮጵያ ሀገሬን ቅኝ ገዢ አይዛትም” ብሎ እንደ አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶምን አፍርቶ ግራዝያንን ያቆሰለ ትውልድ ነው። የኢጣልያ ስብከት  አላማው እና ግቡን ስለተረዳ ኢትዮጵያ እናት ሀገሬ አይደለችም የሚል አስተሳሰብ ማሰብ በራሱ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እራስን መካድ መሆኑን ጠንቅቆ የተረዳ ትውልድ ነው።

መላከ ሰላም ዲመጥሮስ ገ/ማርያም (ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ እጅጉን ከገፉት የመጀመርያው ትውልድ የኤርትራ ተወላጅ)
መላከ ሰላም ዲመጥሮስ ገ/ማርያም (ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ እጅጉን ከገፉት የመጀመርያው ትውልድ የኤርትራ ተወላጅ)

ጣልያን ኤርትራን በያዘችበት ጊዜ በአስመራ ከተማ ውስጥ

  • ለነጮች የተከለሉ ምግብ ቤቶች እንደ አሸን መብዛታቸውን ፣
  • ከምሽቱ 11 ጀምሮ አንድም ኤርትራዊ በአስመራ ጎዳና እንዳይዘዋወር (ጣልያን እና ነጮች ብቻ የተፈቀደ ስለነበር) መታገዱን፣
  • በአውቶቡስ ውስጥ ሲሄድ ኤርትራውያን ከነጮች ጋር እንዳይቀላቀሉ በመጋረጃ እንዲከለል ተደርጎ እንደ ዕቃ ይሄድ የነበረ መሆኑን፣
  • እስላሙ እና ክርስቲያኑ እንዲጋደል የእስላም ቤት ከውጭ የቀይ ምልክት የክርስቲያን ቤት በነጭ ቀለም እንዲቀለም  መድረጉን ወዘተ ያውቃል።

ይህ ትውልድ የቀንም ሆነ የማታ ሕልሙ እናት ሃገሩ ኢትዮጵያን ማየት ነበር። ለእዚህም ነበር ብዙ ሺዎች በሁመራ -ጎንደር እያደረጉ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እና በንግድም ሆነ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ሳይቀር ቦታ እያገኙ የመጡት። ይህ ትውልድ ነበር ”ኢትዮጵያ ወይንም ሞት!” ብሎ” የሀገር ፍቅር ማኅበር” መስርቶ የንጉሡ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ ሆኑ ንጉሡ ሲያመነቱበት የነበረውን የተባበሩት መንግስታትን የፌድሬሽን ጥምረት ውሳኔ ከክህደት ቆጥሮ ንጉሱን መቆምያ መቀመጫ አሳጥቶ ወደ ውህደት የመራው። አምባሳደር ዘውዴ ረታ ስለነበረው ትውልድ ሲናገሩ ”ኢትዮጵያ ኤርትራ እንድትዋሃድ ለማድረግ ሞከረች ከሚለው ይልቅ ኤርትራውያን ውህደቱን አለመፈፀም በእራሱ ትልቅ ክህደት እንደተፈፀመ ከመቁጠራቸውም በላይ ኤርትራውያን በእራሳቸው ጥያቄ ውህደቱን ከመነሻው እስከመጨረሻው ድረስ በሁለት እግሩ አስኬዱት ማለት ይቀላል። እኔ በወቅቱ ምስክር ስለነበርኩ” ያሉት።

ሁለተኛው ትውልድ

ይህ ትውልድ ከ 1960ዎቹ እስከ 1990 ያለው ትውልድ ነው። ይህ ወቅት የሶሻልስቱ አብዮት፣ ወታደራዊ ደርግ፣ የኢትዮጵያ የለውጥ ማዕበል በተለያዩ ኃይሎች እጅ በመከፋፈሉ እና እንደ ድርጅትም ”ሻብያ” ጎልቶ ከመውጣቱ አንፃር የኤርትራ ጉዳይ በተወሰኑ መሳርያ በያዙ ኃይሎች እጅ ወደቀ። ሌላው ቀርቶ የቆላው የኤርትራ ሕዝብ ጥያቄ የሚሰማው ከማጣቱም በላይ ተወካዮቹ ወደ ደርግ መጥተው አቤት ለማለት ተገደዱ። የእዚህ ትውልድ ጥያቄ ከቀይሽብር መከራ ጋር ተዳምሮ ”ነፃነት!ነፃነት!መብት!” የሚሉትን ጥያቄዎች ሁሉ ከመለየት እና የእራስን መንግስት ከማቆም ጋር ተዛመደ። አምባገነንነትን መዋጋት የእራስ ሀገር ከመመስረት ጋር ያለው ተዛምዶ እና ቅራኔን የሚፈታ ጠፋ። የወቅቱ የብሔር ብሄረሰቦች ጥያቄ ማሰርያ ውሉ ጠፍቶ መገንጠልን መድረሻው ሲያደርገው የሚጠይቅ ጠፋ። ጉዳዩ ያሳሰባቸው የመጀመርያው ትውልድ አባላት የሚሰማቸው ጠፋ። ይልቁንም በዘመነ ደርግ  የተከበሩ የደጋው ሃማሴን እና  የኤርትራ ቆላ ተወላጅ  አባቶች በተለይ  ”የሀገር ፍቅር ማኅበር” አባላት እና መስራቾችም ጭምር ‘የኤርትራ እና የኢትዮጵያን አንድ ሕዝብ መሆን አትናገሩ’ ተብለው ድብደባ፣ዛቻ አንዳንዶቹም እስካሁን በሻብያ ወኪሎች እንደሆነ በሚታሰብ መልኩ ቤታቸው መግብያ ላይ የጥይት አረር ሆኑ። ይህንን እውነታ ወደፊት ታሪክ በሚገባ ይዘክረዋል። የሁለተኛው ትውልድ መነጋገርያ ውይይት፣ መግባባት እና ሃሳብን መግለፅ ሳይሆን ”ቀና ብሎ ያየህን በጥይት አረር ድፋው” መሰል የወረደ አስተሳሰብ ነውና ብዙዎች ደርግ እራሱ ሊታደጋቸው አለመቻሉን ሲመለከቱ ወደተለያዩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ሃገራት ተሰደዱ። ዘመንን ዘመን ተካውና የአቶ ኢሳያስ ትውልድ በ 1983 ዓም ከሰላሳ ዓመት ጦርነት በኃላ አስመራ ሲገባ ሁኔታው አዲስ ምዕራፍ ያዘ።

አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ
አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ

ትንሽ ቆይቶ ግን ነገሮች ተቀየሩ። በመጀመርያ በኤርትራ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን ያገቡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የያዙትን ንብረት ትተው ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ተደረጉ። በመጀመርያ ጊዜ የነበረው አወጣጥ በተለይ ህወሃትም በወዳጅነት ላይ ስለነበር የተፈናቃዮቹን መከራ የሚያደምጥ ጠፍቶ በአዲስ አበባ የሚታተሙ የግል ጋዜጦች ብቻ የምስኪን ስደተኞች ችግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስተጋቡ ብቸኛ ጠበቃዎች ሆኑ። ውሎ አድሮ ግን ሻብያ እራሱ ከህወሓት ጋር አዲስ ፍጥጫ ውስጥ ገባ። በለስ ቀንቷቸው አዲስ አበባ የገቡቱ ተፈናቃዮች በሳሪስ ቃሊቲ አካባቢ በድንክዋን ሆነው ቀይ መስቀል ይጎበኛቸው ገባ። ይህ በሆነ በሰባተኛው ዓመት ብዙም ስለ ጀት ማብረር ችሎታ የሌላቸው የአቶ ኢሳያስ አይሮፕላን አብራሪዎች ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን በቦንብ ደበደቡ። ሕፃናት በትምህርት ገብታ ላይ ሳሉ ተቀጠፉ።

ከጥቂት ወራት በኃላ የበቀል እርምጃው ቀጠለ። ከሰባ ሺህ በላይ የሚሆኑ ቀኝ እና ግራ እጃቸውን ያልለዩ ሕፃናትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ ትውልደ ኤርትራውያንን ህወሓት በማባረሩ ኢትዮጵያውያንን አሳዘነ። ብዙዎቹ ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት በአንዲት ጀንበር ሲነጠቁ አነቡ። ከቤት ወጥተው የማያውቁ ልጆች በአውቶቡስ እየተጫኑ በትግራይ በኩል ደቡብ ኤርትራ ላይ ተወረወሩ። ምናልባት የሁለተኛው ትውልድ (የአቶ ኢሳያስ ትውልድ) የመጀመርያው ትውልድ ሲናገረገው የነበረውን ሁሉ ማሰብ የጀመረው በእዚህ ወቅት ይሆናል።የሆነው ሆኖ ይህ ወቅት ”መንግሥታት” ተብለው የሚጠሩ ሁለት አካላት አስመራ እና አዲስ አበባ ላይ ሆነው በከረመ የመለያየት ፖለቲካቸው ሕዝብን ስያሰድዱት ተስተዋሉ። የሁለተኛው ትውልድ አባዜ በእዚህ አላበቃም በሻብያ እና በህወሓት መካከል የነበረውን የቆየ ቁርሾ ”ወደ ሀገር አጀንዳነት” ተቀየረ እና ሁለቱም የህዝብን ስሜት እየኮረኮሩ በባድማ መሬት ስም ውግያ ገጠሙ።በውግያው የኢትዮጵያ ሰራዊት ገፍቶ  አስመራ ሊገባ ሰዓታት ቀሩት። በውቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የነበሩት ወይዘሮ ሶሎሜ በአሜሪካዊ እንግሊዝኛ በተቃኘ ንግግራቸው ለቢቢሲ ”ፎከስ ኦን አፍሪካ” ፕሮግራም ”we gave them our lesson” ”ዋጋቸውን ሰጠናቸው” አሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሁለቱም ወገን የአፈር ሲሳይ ሆነው ነበር።

ሶስተኛው ትውልድ

በኤርትራ ጉዳይ የሶስተኛው ትውልድ ታሪክ የሚጀምረው ከ 1992ቱ የባድሜ ውግያ በኃላ ነው። ኢትዮጵያ እናቴ! ያለው የመጀመርያው ትውልድ አለፈ። ”የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” ያለውም ሁለተኛው ትውልድ ብሎት ብሎት ደከመው። በመጀመርያ ኤርትራን በሀገርነት በማወጅ (በኤርትራ በኩል) እንዲያውጅ በማገዝ (በአቶ መለስ በኩል) ተፈፅሟል። ሺዎች ኢትዮጵያ ነክ ናችሁ ተብለው ከኤርትራ ተባረዋል። ሌሎች ሺዎች ኤርትራ ነክ ናችሁ ተብለው ከኢትዮጵያ ተግዘዋል። በድንበር ሰበብ ብዙ አስር ሺዎች አልቀዋል። ሁለተኛው ትውልድ ደከመው። ከእዚህ ሁሉ በኃላ የመጀመርያው ትውልድ የመከረውን የፍቅር ጥሪ እያሰበ ሳለ ሶስተኛው ትውልድ ተነሳ።
ሶስተኛው ትውልድ በተለይ ሁለተኛው ትውልድን የሚያደንቀው በጠበንጃ አያያዙ ካልሆነ በቀር ልማት እና እድገትን ሲያመጣ ማየት አልቻለም። ይልቁን ይህ ትውልድ በመረጃ ዘመን እንደመኖሩ ታሪክ ሲነገረው በደቂቃዎች ውስጥ የተባለው ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ስለሚችል በአራዳ አነጋገር ”የማይሸወድ” ሆነ። ከሁሉም በላይ አቶ ኢሳያስ ቀደም ብለው ያነሱት ”የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አባባል ውላ አድራ በእዚህ በሶስተኛው ትውልድ ከባድ ፈተና ገጠማት።

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከባለቤቱ ጋር
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከባለቤቱ ጋር
  • ”ኤርትራ ቅኝ ግዛት ተይዛ የነበረው በኢጣልያ እና በሞግዝቷ እንግሊዝ ነው እንጂ በኢትዮጵያ መች ሆኖ ያውቃል?” የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ ቀጠለ…
  • ”በደል እና ጭቆና ቢኖርም ይህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የመጣ መከራ አይደለም ወይ?”
  • ”የኃይለስላሴ አስተዳደርም ሆነ የደርግ ቀይሽብር በአስመራ ላይ በተለየ ተደረገ ወይስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የቀመሰው ገፈት ነበር?”
  • ”ይህ የሚያሳየው የአቶ ኢሳያስ ትግል መሆን የነበረበት ከደርግ አምባገነንነት እና ከንጉሡ ፍፁም ዘውዳዊ ስርዓት ለመላቀቅ ብሎም ስልጣንን ከማዕከላዊ መንግስት ለመንጠቅ መሆን የለበትም ነበር ወይ?” ወዘተ ጥያቄዎች አቶ ኢሳያስ እንዲመልሱለት ሶስተኛው ትውልድ የሚጠይቃቸው ናቸው።

ሶስተኛው ትውልድ ድንበር ከድንበር ቢዘጋበት በመከራ ላይ ሆኖ በስደት ሲገናኝ የሁለተኛውን ትውልድ ሥራ ማብሰልሰሉ አልቀረም። ጊዜ፣ ቦታ እና አጋጣሚ ሲገጥመው ግን የአቶ ኢሳያስ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” ብለው የሰሩት ዶሴን ይዘት እራሳቸውን አቶ ኢሳያስን ይጠይቅበታል።

የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ አልቆመም…

  • “ከኢጣልያን የዘር መድሎ የተላበሰ አገዛዝ ከእንግሊዝ ከሞግዝትነት ባለፈ ሌላ ቅኝ ገዢ ለመሆን ታደርገው ከነበረው ዝግጅት ኤርትራ የዳነቸው ከኢትዮጵያ ጋር በፌድሬሽን ከተቀላቀለች በኃላ አይደለም ወይ?”
  • “አስመራ በነፃነት ከ 11 ሰዓት በኃላ መሄድ የተቻለው፣የፈለጉበት ምግቤት (የነጮች የጥቁሮች) ሳይባል መመገብ የተቻለው ከፌድሬሽን በኃላ አይደለም ወይ?”
  • “በአስመራ መንገድ ላይ በእግር ለመሄድ ‘ነጮች በሚሄዱበት መንገድ ላይ መሄድ አይቻልም’ ተብሎ ለጥቁር በተከለለ መንገድ ላይ ብቻ ይሄድ የነበረው ኤርትራዊ በነፃነት በሁሉም የእግር መንገድ ላይ በዜግነቱ ኮርቶ መሄድ የቻለው ከፌድሬሽን በኃላ አደለም ወይ?”
  • ኢጣልያ ለኤርትራ ተወላጆች ትምህርት እስከ አራተኛ ክፍል ብቻ እንዲሆን መወሰኗ ያቆመው እና ኤርትራውያን የትምህርት ዕድል እስከፈለጉት ክፍል ድረስ መግፋት የቻሉት ከፌድሬሽን በኃላ አይደለም ወይ?
  • “ለመሆኑ  በኤርትራ የተወለደው ኢትዮጵያ ከተወለደው በምን ተለያየ?  በንግግር? ወይንስ በመልክ? በአመጋገብ? ወይንስ በሃይማኖት በምን ተለያይቶ ነው የዲሞክራሲ፣ የመብት እና የስልጣን ጥያቄ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” የተባለው? የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ ይቀጥላል።

አበቃሁ

ጌታችው በቀለ (የጉዳያችን ብሎግ)
ኦስሎ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Eyoel says

    September 17, 2013 05:45 pm at 5:45 pm

    This is so informative. I did not know very well about the first generation of Eritrea. Surprisingly, I read that Isayas said ” Ethiopia did not colonized Eritrea ” . Ze Yigerm !!!

    Reply
  2. TEWBEL says

    September 18, 2013 01:13 am at 1:13 am

    THE STRANGE IS THAT ISSAYAS HIMSELF IS NOT ERITREAN HE WAS BORN IN MEKELLE FROM A GOOD TIGREAN FAMILY. BY THE WAY OF ERITREAN HEROES WOLDAB WOLDEMARIAM WAS ALSO ANOTHER TIGREAN.
    THE ERITREAN LEADER SEEMS TO BE SUFFERING OF A HIGH STATE OF DELUSIONAL PARANOIA CAUSED BY IDENTITY CONFUSION.
    CONTRARY TO GINBOT 7 DECLARATION IT ALSO HARD TO BELIEVE THAT ETHIOPIA WILL BE LIBERATED BY ERITREAN MONEY (CUM ARAB) MONEY AND ASSISTANCE, UNLESS IT IS ANOTHER ILLUSION, KNOWING THE PAST HISTORY OF BOTH REGIMES.
    GOD HELP US !!!

    Reply
  3. Mekonnen Abraham Tewolde says

    September 19, 2013 02:41 am at 2:41 am

    I agree Eritrea was not colonized by Ethiopia
    but when the HSI and Dergue regimes try and
    do their utmost through their propagandas and
    lies to mobilize people on their side the Eritrean
    struggle has the right also to do its utmost work
    on propaganda and mobilize the oppressed people
    on their side and just causes. Hence the most familiar
    term” colonizing or colonization” to mobilize the masses
    on easy understandable terms or explanations.

    Reply
  4. LIBERTY says

    September 19, 2013 09:45 pm at 9:45 pm

    ይየትኛው ዙር ትውልድ ይሁን ከብዙ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ የምሰማውና የሚያናድደኝ ነግር ቢኖር የኤርትራን በጣልያን እጅ መውደቅ ሲመጻደቁብት መስማት ነው… የኤርትራ ህዝብ እድሉ ሆኖ ጂኦግራፋዊ አቀማምጡ ለውጭ ወራሪዎች የመጀመርያ ገፈጥ ቀማሽ ኣርጎት ለዘመናት ኖሯል..ሆኖም ግን ለማንም የውጭ ወራሪ አሜን ብሎ ተገዝቶ አያውቅም ይብዛም ይነስም ለነጻነቱ የታገል የነበረና ያለ ህዝብ ነው…ታድያ ይህ ኩሩ ህዝብ ቢደክመውና ለተወሰነ ግዜ በጣልያን እጅ ቢወድቅ የቱ ላይ ነው ጥፋቱ ? ይህ ሁኔታስ ለኢትዮጵያዊያን የመመጻድቅያ ነጥብ መሆን ነበረበት ? የኢትዮጵያ ህዝብ በውጭ ወራሪ ባይገዛና ባይንገላታ እንኳ በራሱ መሪዎች ከውጭዎቹ በባሰ እስካሁኗ ደቂቃ አየተሰቃየ አይደልምን ያለው ? ወይስ የባርነት መልክና ቀለም አለው ? የአጼውና የአሁኖቹ የመዕራባውያን ደርጉ ደግሞ የምስራቃውያን አሻንጉሊቶች አልነበሩም ብሎ የሚከራከር ያለ አይምሰለኝም ..ታድያ የህ የቅኝ አገዛዝ ከቀጥታው አግዛዝ ቢከፋ እንጂ አያንስም…ውጤቱም በኢትዮጵያ ህዝብ የወረደውና እየወርደ ያለው ግፍ ነው መልሱ :: ድፍን አፍሪካ በወራሪዎች እንዳልተገዛና እንዳለተንገላታ የኤርትራን ብቻ እንደ ልዩ ነገር ተቆጥሮ ከኢትዮጵያ መነጻጸርያ መጠቀሙ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ነው የሚብሰው…የኢትዮጵያ ልሂቆች ደረታቸውን ነፍተው ”ኢትዮጵያ በውጭ ሃይሎች ተገዝታ አታውቅም ” ሲሉ …እሺ ጥሩ … ከተገዙት ህዝቦችና አገሮች የተሻለ ወይ ደሞ የበለጠ ኑሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ነው ? ምነው ይህን ደሮን ስያታልዋት ጨዋታ ቢቀር ?

    “ለመሆኑ በኤርትራ የተወለደው ኢትዮጵያ ከተወለደው በምን ተለያየ? በንግግር? ወይንስ በመልክ? በአመጋገብ? ወይንስ በሃይማኖት በምን ተለያይቶ ነው የዲሞክራሲ፣ የመብት እና የስልጣን ጥያቄ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” የተባለው? የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ ይቀጥላል።

    አሁን የህ ጥያቄ ህዝብን አስተምራለሁኝ ከሚለው ጽሃፊ የሚጠየቅ ጥያቄ ነው ? አቶ ጌታቸው በቀለ በርስዎ ቀመር ጣልያንኛ የሚናገሩት ስዊሶች ከጣልያን… ጀርመን የሚናገሩት ስዊሶች ከጀርመን..ፈረንሳይኛ የሚናገሩት ስዊሶች ደግሞ ከፈረንሳይ ተዋህደው ሲውዘርላንድ የምትባለው አገር ከአለም ካርታ ድሊት ትሁን እያሉን ነው ያሉት ? በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙት የተለያዩ የ አረብ አገሮች ደግሞ አንድ ቋንቋ ..ተመሳሳይ አመገአገብና ከሞላ ጎደል አንድ ሃይማኖት ስለሚጋሩ ሁሉም ፈርሰው አንድ አገር ዩሁኑ ነው አያሉን ያለው ?

    በመጨረሻ እኔ እንደ ኤርትራዊ መጠን ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን በስጋ… በታሪክ…ባመጋገብ..በባህል… ይህን ያህል ልዩነት አለን ብየ አላማንም ሆኖም ግን ይህ ብቻ ደግሞ አንድ አገር የደርግናል ብየም አላምንም…ህዝቦች ራሳቸው በሚፈጥሩት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሂደት ብቻ ነው አንድ አገር ልያድርጋቸው የሚችል አስተያየት ነው ያለኝ … የ እውን የሚሂኖው ደግሞ ኢትዮጵያውያን የራሳችን የሚሉት መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲፈጥሩ ብቻ ነው :: ምክንያቱም ከራሷ ጋር የታረቀች ኢትዮጵያ ከኛ ተርፋ ለአፍሪቃም በረከት እንደሆነች ነው የሚገባኝ ::

    Reply
  5. Haddish Alem says

    September 20, 2013 02:17 am at 2:17 am

    Sometimes I feel sorry for Ethiopia when it has dumb asses like Getachew Bekele in
    this enlightened age of 21st century. Certainly he is one of those left mentally crippled
    by the severe propaganda of bankrupted ruling families and junts who also crippled the
    country for generations.
    what made me say so is :
    1- If Eritreans were colonized and the rest of Ethiopia is not; how come one ( like Abraham
    Deboch and Moges Asgedom) come from that society and country to lead the people to
    freedom instead of from the rest parts of Ethiopia. Isn’t this so shamefull to so called
    Ethiopians (to say) !
    2- The other point is – Isn’t this legacy and grieving that caused the 1960 coup or revolution
    and supported by many true Ethiopians abroad and at home later and caused the second 1974
    revolution to the delights of the Ethiopian people.
    3- And my third point is like LIBERTY pointed it above whether colonial or neo-colonia it is
    rule by foreign and people…………( if not neo-colonial is actually worst !). And it is so foolish
    to think Ethiopia had free self ruling government untill 1991 unless one is so dump like the
    writter of this article Mr. Getachew Bekelle.

    Reply
  6. Bariso says

    September 20, 2013 05:24 pm at 5:24 pm

    Amhara elites all the time crying for the land Eritrea, Oromia, Ogaden, Sidama,…..which is not belongs to them, the liberation struggle continue until the Amhara/Tigray Ethiopian empire will dismantled

    Reply
  7. wlude twld says

    September 22, 2013 11:31 pm at 11:31 pm

    The whole Article that Getachew wrote is not contrary to fact. It is stating about the three consecutive generations. The first generation has insisted to librate from Italy colony and be united with Ethiopia king dom.The witness is mentioned on Ambassador Zewde Reta’s book titled ”ERITREA ISSUE”. The third generation which is active now do not have problem with Ethiopianism Idea. The problem is with out-dated generation which is called in this article as second generation. Almost all commentators here above who are trying to fan Isayas Afewerq succession act. Isayas him self is now in a big problem of identity. He is half from Ethiopia moreover the people of Ethiopia and Eritrea are well conscious on the bad act of Isayas. You second generation advertisers please come to the reality. Ethiopians and Eritreans are well aware of your ego manner. enough is enough!!!!!

    Reply
  8. second Generation says

    September 25, 2013 01:28 am at 1:28 am

    I am the second generation Eritrean-Ethiopian
    But I disagree with your assessement of our generation
    Actually our second generation is one of the best and heroic Eritrean-Ethiopians
    who are proud and ready to sacrifice their life for justice and freedom of the the
    whole Ethiopian peoples.
    Our generation is the one who called a spade a spade and wrong is always wrong.
    You some writers here seem to be one of those who like to misrepresent and
    mischaracterise people’s history for fear of the wrath of rulers or are ones who
    chose to live for their bellies and stomachs.
    What is wrong if one said HSI and his people commited grave mistake and should be
    held accountable ?
    What is wrong if one refused to bow down and silenced by mercenary acts of the Dergue
    regime and accept wrong and injustice created by previous confused oligarchy ?
    Wouldn’t that amount to seeling your freedom and betrayal of the justice and freedom
    seeking Ethiopian peoples and submitt to unjust rulers and injustice ?

    Reply
    • washeraw says

      September 30, 2013 01:31 pm at 1:31 pm

      I agree with you, about 90%.

      I think the writer highlighted one element of Eritrean society, especially when he described the 1st generation. It is well documented that there were a variety of opinions about the future of Ethiopia. We can assume that the Unionists (Mahber Fqri Hager) won the day because of their numbers (?) and support from Addis Ababa.

      The writer failed to mention the two grave errors committed by those who were in power in Addis Ababa: 1) appointment of Haileselassie’s son in law as Eritrean Governor after the “legal” dissolution of the federation, 2) Mengstu’s crazy action in stopping the peace process started by General Aman Michael Andom.

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule