• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር!

September 29, 2013 09:50 pm by Editor 2 Comments

አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡

ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ አመራር ህዝቡ ለሰጠው አመርቂ ምላሽ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረቡ፣በቀጣይ ለሚደረገው ወሳኝ ትግል ታላቅ የማበረታቻ እርሾ መሆኑን ያምናል፡፡ ከዚህም ሕዝቡ አመራር ካገኘ ለመብቱና ነፃነቱ ወደ ኋላ የማይል መሆኑንና በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት መኖሩን ያረጋገጥንበት፣ ትዕይንት ሲሆን በተጨማሪ ሠላማዊ ትግል በጋራ አመራር ከተያዘ ውጤታማ መሆኑን አምነናል፡፡

udj 2 19ሆኖም ከዚህ ሕዝባዊ ንቅናቄ የተማርነው ሌላ ነገር ቢኖር በአገራችን ያለውን የአስተዳደርና የህግ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ መውደቁንና ገዢው ፓርቲ በየትኛውም ደረጃ በሕዝብ በሚነሱ ጥያቄዎች በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ የወደቀ መሆኑን ነው፡፡

የአዲስ አበባ መስተዳድርና የፌዴራሉ መንግሥት ለሰልፉ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ቢልም የተለያዩ አስተዳደራዊ ደንቃራዎችን በመፍጠርና የማናውቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በመፍጠር የቅስቀሳ ሥራችንን በማደናቀፍና ሕዝቡ ወደ ሰልፉ እንዳይወጣ በማድረግ በተግባር ሠልፍ የማይደረግባት አገር ለመፍጠር ሣይታክት ተግቶ ሰርቷል፡፡ ቀስቃሾችና አመራሮችን አስሯል መኪናዎችን አግቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ማለፍ የተሣካ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠራችን ከዚህ በመነሳት አንድነት ፓርቲና 33ቱ በጋራ በተጠናከረ መንገድ በመላው አገሪቱ ቀጣይና ተከታታይ ሕዝባዊ ንቅናቄ የማድረግ አስፈላጊነትን ተምረንበታል፡፡

ስለሆነም በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር የምትገኙ የሠላማዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ ደጋፊዎቻችን በሙሉ ለእስከዛሬው በድጋሚ እያመሰገንን ለቀጣዩ የጋራ ሥራችን እንደተለመደው ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

አንድነት ፓርቲና 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. mohamed abass says

    September 29, 2013 10:07 pm at 10:07 pm

    አዎ ይህ ሚሊዮኖች ብሷት ድምጽ !! ፍትህ ነጻነት እኩልነት ፈልጊ ህዝብ ድምጽ ! በኑሮ ውድነት የነፍረ ህዝብ ድምጽ ! ሁለት አስርት አመታት የአንድ ስረአት አገዛዝ በቃኝ ያለ ህዝብ ድምጽ ! ይህ ድምጽ በየቀበሌው እና የገጠር ግብሬ ማህበራት በገዢው ስረአት ካድሬ ተገዶ አደባባይ የሚወጣውን ህዝብ ነጻነት የሚያውጅ ታሪካዊ ድምጽ ነው ! አዎ የህሊና ባሪያ ሆነው የሚያገለግሉትን ደካማ ቱባ ባለስልጣኖች እና ለሆዳቸው ያደሩ ምስለኔዎች ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ የነጻነት ድምጽ ! አዎ ይህ ድምጽ ወህኒ የሚማቅቁ ንጹሃን የነጻው ፕሬስ አረበኛ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን ስቃይ እና መከራ የሚያሰማ ድምጽ ነው ! ከሳውዲ አረቢያ «ጅዳ በዋዲ »

    Reply
    • mohamed abass says

      September 29, 2013 10:20 pm at 10:20 pm

      correction ከዚህ በላይ ያስቀመጥኩትን የሚሊዮኖች ድምጽ ትርጉም ያገኘሁት ከጅዳው የፌስቡክ አጋሬ « Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ » መሁኑን መጥቀስ ወዳለሁ !

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule