በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 18 ኪግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን ››የተባለ ማእድን ተያዘ። በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬድዋ ከተማ ባደረገው ክትትል በተለምዶ ሶስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 1 ኪ.ግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን›› የተባለ ማዕድን በቁጥጥር ስር አውሏል። ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማእድኑን ወደ ውጭ ሀገር ለማስወጣትና ለመሸጥ በዝግጂት ላይ እንዳሉ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞችና በብሄራዊ መረጃ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ኢፕድ ዘግቧል። በዚህ ህግ የማስከበር ስራ ይህንን የሃገር ሐብት ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣዎች የተያዙ ሲሆን የተያዘው ማእድንም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ቀጣይ … [Read more...] about ይህ ሌብነት ሲፈጸም መዐድን ሚኒስቴር የት ነው?
Archives for December 2022
ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ኃላፊዎችን የጠቆመ ከሃብቱ 25% እንዲያገኝ ይደረጋል
ሀብት ያላስመዘገቡ አመራሮችንና ባለሙያዎችን የጠቆመ ሰዉ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ ይደረጋል ሲል የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ሀብት በማስመዝገብና በማሳወቅ ሂደት፤ አመራሮችንና ባለሙያዎች ሳያስመዘገቡ የቀሩትን ሀብት የጠቆመ ዜጋ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ እንደሚደረግ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል። ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስ እና መረጃ አስተዳደሥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፈርዳ ገመዳ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም በአዋጅ ቁጥር 668/2002 በግልፅ መስፈሩን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እስካሁን 763 የመንግስት አመራሮችን ቢለይም፤ እስካሁን ሀብታቸውን ያስመዘገቡት 20 በመቶው ብቻ መሆናቸው ተጠቅሷል። እስካሁንም 2 ሺሕ 272 የፌደራል … [Read more...] about ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ኃላፊዎችን የጠቆመ ከሃብቱ 25% እንዲያገኝ ይደረጋል
በፊርማው ስምምነት መሠረት የትህነግ ታጣቂዎች ከ፱ ግምባሮች ለቀቁ
በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች በስራቸው ከነበሩ የውግያ ግምባሮች ለቀው መውጣት እንደጀመሩ ተገልጿል። ታጣቂዎቹ ከደቡብ፣ ማይ ቅነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት፣ ጨርጨር፣ ኩኩፍቶ፣ ሕጉምብርዳ፣ በሪተኽላይ እና አበርገለ ለቆ ግንባሮች ነው መውጣት እንደጀመሩ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተሰማው። ከጥቂት ቀናት በፊት (የትግራይ ኃይሎች አዛዥ) ታደሰ ወረደ በሰጡት መግለጫ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን (orientation) ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን እንዳለቀ ኃይላቸው ካለበት ቦታ Disengage አድርጎ / ተላቆ የውጊያ ግንባሮች የማፍረስ እና ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ እንደሚጓጓዝ መግለፃቸው አይዘነጋም። አዛዥ ኃላፊው ታደሰ ፤ "የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም … [Read more...] about በፊርማው ስምምነት መሠረት የትህነግ ታጣቂዎች ከ፱ ግምባሮች ለቀቁ
ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ
ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው ሲሉ ስብሐት ለፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ክሱን ያቀረቡት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት ነው። አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል። በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ
ይቅርታ ያደረገን ሕዝብ ማታለል አይገባም
ተሃድሶ ጥሩና መጥፎ ጎኖች አሉት። በተለይ ሥርነቀል አቢዮት በተለመደባት አገራችን ተሃድሶ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ያንን መዘርዘር ግን አሁን አስፈላጊ አይደለም። የዚህ ርዕሰ አንቀጽ ዓላማ በተሃድሶ ምክንያት እየደረሰ ያለውና መረን የለቀቀ ተግባር እርምጃ እንዲወሰድበት ለመጠቆም ነው። ትህነግ ያላሰበውን ሥልጣን ተቆጣጦሮ አዲስ አበባ ሲገባና ካድሬዎቹ የዲዛይነር ልብስ መልበስ ሲጀምሩ የተበላሸው ጭንቅላታቸው ያው በበረሃው እሳቤ ነበር የቀጠለው። ከዓመታት በኋላ የድርጅቱን መበስበስ እንደማያውቅ ሆኖ ያስደነቀው ሊቀጳጳስ መለስ ዜናዊ “እስከ እንጥላችን ገምተናል” ነበር ያለው። የዘራውን እንደሚያጭድ አለማሰቡ ዕውቀት ጸዴ በረኸኛ መሆኑን በራሱ አስመስክሮበታል። ያገኙትን ሁሉ መዝረፍ ሙያቸው አድርገው የተካኑት ትህነጋውያንና ኢህአዴጋውያን ሊቀ ደናቁርት ካድሬዎች በለውጥ ስም ልክ … [Read more...] about ይቅርታ ያደረገን ሕዝብ ማታለል አይገባም