
ሀብት ያላስመዘገቡ አመራሮችንና ባለሙያዎችን የጠቆመ ሰዉ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ ይደረጋል ሲል የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
ሀብት በማስመዝገብና በማሳወቅ ሂደት፤ አመራሮችንና ባለሙያዎች ሳያስመዘገቡ የቀሩትን ሀብት የጠቆመ ዜጋ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ እንደሚደረግ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።
ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስ እና መረጃ አስተዳደሥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፈርዳ ገመዳ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም በአዋጅ ቁጥር 668/2002 በግልፅ መስፈሩን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ እስካሁን 763 የመንግስት አመራሮችን ቢለይም፤ እስካሁን ሀብታቸውን ያስመዘገቡት 20 በመቶው ብቻ መሆናቸው ተጠቅሷል።
እስካሁንም 2 ሺሕ 272 የፌደራል ተቋማት መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሀብታቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።
ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ሰዎች በህግ ፊት ተጠያቂ ከመሆናቸው በፊት እንዲያስመዘግቡም ጥሪውን አቅርቧል። (ኢትዮ ኤፍ ኤም107 የኢትዮጵያዊያን)
በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች ግን ሌቦቹ ለጠቋሚዎቹ ጠቀም ያለ ብር በመክፈል ከዚህ ሊያመልጡ ስለሚችሉ መንግሥት በቁጥጥር ሥር ቢያውላቸውናሃብታቸው እንዳይንቀሳቀስ ቢያደርግ የተሻለ ነው ይላሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ሃብታቸውን ማስመዝገብ አለባቸው የተባሉትን ባለስልጣናት፤ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር በኮሚሽኑ እጅ ያለ ይመስላል። ይህ ሐቅ ከሆነ ማን እንዳስመዘገብ፤ ማን እንዳላስመዘገበም ኮሚሽኑ ያውቃል ማለት ይቻላል። ስለዚህ ለጠቋሚ ግለሰብ ወይም አካል የሃብቱን ፪፭% እንሰጣለን ማለት ሌላ የሙስና፤ የብቀላና የእንካ ስላንትያ በር መክፈት አይሆንምን?