በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች በስራቸው ከነበሩ የውግያ ግምባሮች ለቀው መውጣት እንደጀመሩ ተገልጿል።
ታጣቂዎቹ ከደቡብ፣ ማይ ቅነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት፣ ጨርጨር፣ ኩኩፍቶ፣ ሕጉምብርዳ፣ በሪተኽላይ እና አበርገለ ለቆ ግንባሮች ነው መውጣት እንደጀመሩ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተሰማው።
ከጥቂት ቀናት በፊት (የትግራይ ኃይሎች አዛዥ) ታደሰ ወረደ በሰጡት መግለጫ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን (orientation) ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን እንዳለቀ ኃይላቸው ካለበት ቦታ Disengage አድርጎ / ተላቆ የውጊያ ግንባሮች የማፍረስ እና ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ እንደሚጓጓዝ መግለፃቸው አይዘነጋም።
አዛዥ ኃላፊው ታደሰ ፤ “የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም ልናነሳው እንችላለን ምናልባት የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል” ማለታቸውም የሚወስ ነው። (@ቲክቫህ)
ትጥቅ የማስፈታቱ ውሳኔና ሒደት ለመቀበል የከበዳቸው በውጪ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ከግምባር መልቀቅ ማለት ትጥቅ መፍታት ማለት አይደለም እያሉ አሁንም በጸረ ሰላም አቋማቸው ጸንተዋል። በሌላ ወገን ከነዚሁ የደም ነጋዴዎች ጋር እየተናበቡ የሚሠሩ ኃይሎች ትጥቅ አንፈታም በማለት እንዲያውም ሥልጠናና ሥምሪት ላይ ናቸው የሚል መረጃ ከታማኝ ምንጮች ሲነገር ይደመጣል።
ትጥቅ እፈታለሁ ብሎ ሁለት ጊዜ ከፈረሙ በኋላ በዚህ ልክ ለሕዝብ መዋሸት አግባብ እንዳልሆነ የሚናገሩ ወገኖች ባንድ ወቅት ጄኔራል አበባው “ወያኔ ሞቶም ይዋሻል” ያሉትን ያስታውሳሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply