
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 18 ኪግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን ››የተባለ ማእድን ተያዘ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በድሬድዋ ከተማ ባደረገው ክትትል በተለምዶ ሶስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 1 ኪ.ግ የሚመዝን ‹‹አኳ ማራይን›› የተባለ ማዕድን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማእድኑን ወደ ውጭ ሀገር ለማስወጣትና ለመሸጥ በዝግጂት ላይ እንዳሉ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞችና በብሄራዊ መረጃ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
በዚህ ህግ የማስከበር ስራ ይህንን የሃገር ሐብት ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣዎች የተያዙ ሲሆን የተያዘው ማእድንም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ቀጣይ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ ህግ የማስከበር ዘመቻ ተሳትፎ ላደረጉ የድሬድዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋናውን የቀርባል።
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡
በዚህ ዝርፊያ ላይ ከመዐድን ሚኒስቴርም ሆነ ከሚኒስትሩ ታከለ ዑማ የተሰጠ መግለጫ የለም። የአዲስ አበባ ከንቲባነት ከሕግ ውጪ በሹመት ይዘውት የነበሩት ታከለ ዑማ በመሬት ዝርፊያ እጃቸው ይኖርበታል የሚል ክስ እየተመሠረተባቸው ባለበት ወቅት ወደ መዐድም ሚኒስቴር መዛወራቸው የሚታወስ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
We are in danger