በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ መነሻ አሳብ ትረካ እና የእለቱ የውይይት አጀንዳ በሆነው ያለፉት 25 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ገለፃ በኋላ በምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተነሱ አስተያቶች እና የአካሄድ ጥያቄዎች:- 1. የመጀመሪያ ተናጋሪ፡- 1.1 “የዚህ ወይይት አጀንዳ ከጠበኩት በታች ወርዶብኛል በወላይቲኛ አንድ አባባል አለ - ያቺ እንትን'ኮ ወደቀች ቢሏት፤ ቀድሞም አቀማመጧ ለመውደቅ ነው አለች”፡፡ 1.2 “ካሳ! አንተ ሚኒስትር ነህ በዛ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ሊቀመንበር በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ውስጥ ሆኖ PhD candidate መሆን አይቻልም ስለዚህ ስራህን ልቀቅ” 1.3 “ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይምጣና ያወየን፣ እናንተ ውረዱና ከእኛ ጋር ተቀመጡ” 2. ሁለተኛ ተናጋሪ … [Read more...] about “ይቺ ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት”
Archives for September 2016
የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች
እንደ መግቢያ ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓትን የምትከተል አገር አይደለችም” ብዬ ፅፌ ነበር። ዛሬም ትንሽ አዳብሬ በዚሁ ላይ ትንታኔ መስጠት አምሮኛል። ይህ ጽሁፍ ደግሞ እንዲነሳልኝ የፈለኩበት ምክንያት በቅርቡ የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የሆኑት አቶ ስዩም መስፍንና አቶ አባይ ፀሃየ በቅርቡ በኢትዮጵያ “ወቅታዊ” ጉዳይ ላይ የተሰኘ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር ያዳመጠ ሁሉ የየራሱን ምልከታ ያስቀምጣል። እጅግ ብዙ ሰው ግን አዲስ ነገር የማይገኝበት ወቅታዊ የማይባል ያደርገዋል። አገሪቱን ህዝባዊ ተቃውሞ በሚንጥበት በዚህ ሰአት ቢያንስ ስለብሄራዊ መግባባት ስለ ብሄራዊ እርቅ ስለ ይቅርታ ማውራት ተገቢ ነበር። የፓለቲካ መሪ ምንም እንኳን የያዘው አቅጣጫ ለራሱ አዋጭ ቢመስለውም ነገር ግን ህዝብ ካልተቀበለው ራሱን ይመረምራል። ይህ ግን በኛ ሃገር … [Read more...] about የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች
ተራራም ይሰረቃል? የራስ ዳሽኑ ፖለቲካ
ራስ ዳሸን ተራራ ከትግራይ "ክልል" ካርታ የመውጣቱ አሲዮ ቤሌማ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ሲነገር፤ "ደፍረውናል! ንቀውናል! ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል!" የሚለው የኮሎኔል መንግስቱ ንግግር በጆሮዬ ላይ አቃጨለ። ድፍረቱ እና ንቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ በቁም የሞቱት ግን እኛ ሳንሆን እነሱ መሆናቸውን የሚያበስር የዜና እወጃ ነበር። ነገሩ እንጂ ሁሉም የተለመደ ነገር ነው። ውሃ ይጠፋል፣ መብራት ይጠፋል፣ ስልክ ይጠፋል፣ ገንዘብ ይጠፋል፣ ኮንዶሚንየም ህንጻም ይጠፋል። ይህ በህወሃት ፖለቲካ ጥርሳቸውን ላልነቀሉትም አዲስ ነገር አይደለም። ዘረፋም ለነሱ አዲስ አይደለም። መንግስት ሆነው ከተቀመጡ በኋላ እንኳን 10 ቶን ቡና ሰርቀዋል፣ የመብራት ጀነሬተሮች ሰርቀዋል፣ ከብሄራዊ ባንክ ወርቅ ሰርቀዋል ... የህዝብን ድምጽም በተደጋጋሚ ሰርቀዋል። ተራራ ተሰርቆ ሲመለስ ግን የመጀመሪያው … [Read more...] about ተራራም ይሰረቃል? የራስ ዳሽኑ ፖለቲካ
የተወጠረችው አዲስ አበባ ታስፈራለች – ብሶት ይንፈቀፈቅባታል!!
እድሜው አርባዎቹን ስለመሻገሩ ገጹ ይናገራል። በተፈጥሮ ያለው እርጋታ አዲስ አበባ ካጋጠመው ትንግርት ጋር ተዳምሮ አፍዞታል። ፊቱን ፈገግ የሚያደርገው ስለ አዲስ አበባ አራዳዎች ሲናገር በቻ ነው። ጨዋታውን የጀመረው በጫማ አሳማሪዎች ነበር። ጫማ አሳማሪዎች ደረጀ ወጥቶላቸዋል። “የታቀፉና ያልታቀፉ” ሁሉንም ገጠመኞቹን ሲያስረዳ “አዲስ አበባ እንደ ወበቅ ነች” ይላል። የወበቅ ጭንቀት የሚለቀው በደንብ ሲዘንብና አየሩን አፍኖ የያዘው ደመና ሲገፈፍ ነው። ወበቅ ለሱ በሽታ ነው። ነዋሪነቱ አውሮጳ ሲሆን አዲስ አበባ የከረመበት ምክንያት ቤት ቢጤ ስላለው እሱኑ ሸጦ ለአንዴና ላልተወሰነ ጊዜ የሚወዳትን “ወበቃም” ከተማ ለመለየት ነው። ቦሌ ፒኮክ ቁጭ ብለን ስናውጋ ቀድሞ አደራ ያለኝ ፊቱ ማስታወሻ አውጥቼ የሚነግረኝን እንዳልጽፍ ነው። ለወትሮም ቢሆን ስለማላደረርገው ተስማማሁና አወጋን። … [Read more...] about የተወጠረችው አዲስ አበባ ታስፈራለች – ብሶት ይንፈቀፈቅባታል!!
ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር
የአፍሪካ ነፃነት አብሪ ኮከብና በጀግና ህዝቧ አኩሪ ተጋድሎ ባለክብር የነበረቺው ኢትዮጵያ ዛሬ በከፋ ፈተና ውስጥ ገብታለች። በብርቱ ትግልና ጥንቃቄ መወገድ ያለባቸው ያገርና የህዝብ ደህንነት ስጋቶች ከፊቷ ተጋርጠዋል። የርስ በርስ ጦርነት ስጋት፣ የአስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እጦት፣ የማእከላዊ መንግስት አቅጣጫ ብዥታና የውጭ ጠላት ስጋት፣ ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህንና መሰል ያገርና ህዝብ ደህንነት ስጋቶች ለማስወገድና ጤናማ የፖለቲካ ድባብ ለመፍጠር ባስቸኳይ መንቀሳቀስና ሀገርና ህዝብን ካሳፋሪ ውድቀት ማዳን ያስፈልጋል። በኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ ያንዣበቡትን እነዚህን አደጋዎች ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? በእርግጥስ ይቻላል? እነዚህን ያገርና የህዝብ ህልውና ፈተናዎች በማስወገድ የኢትዮጵያን ሁኔታ ሰላማዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ማድረግ የሚችለውስ ማነው? የሁሉም ጥያቄዎች መልስ … [Read more...] about ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር
የፍቅር ብልሃቱ
ልዩነትን አድንቅ አንድነትን አድምቅ እንቆቅልሽ ፍታ ጥላቻ ይረታ ሁሉም ብሔረሰብ ነውና ቤተሰብ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት ተውክ አማራ ምንም እንኳን በአገር መንፈስህ ቢኮራ “እኔ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ተውክ ኦሮሞ ምንም እንኳን ጥሪህ ሁሎ ቢያድር ከርሞ “ኢትዮጵያዊ አማራ” ሆነህ ስትሄድ “ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ” አገኘህ መንገድ የልብ ትርታ ሲወጣ ገሃድ ብለው ሲጠብቁ እሳትና ጭድ ፍቅር ጣልቃ ገብቶ አደረገ ጉድ የፍቅር ብልሃቱ ግርም ማሰኘቱ አንቺዬ ድንቅ አገር ኢትዮጵያ የሚሉሽ ትግሬና ሶማሌ ደቡብን የያዝሽ ጉራጌ ጋምቤላ አፋርን ያቀፍሽ ስንቱን ልጠራ ነው በዙ ልጆችሽ ነግሩ ሲጠራ እንዲሁም ሲጣራ እኩልነት ሰፍኖ ፍቅርም ልቆ ገኖ ኦሮሞ አማራ ማለቱ ይረሳና ኢትዮጵያዊ ነኝም ማለት ይቀርና ከአሁን ማንነትህ አድገህ … [Read more...] about የፍቅር ብልሃቱ
“ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?”
“ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ይጀምራሉ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ ረፍት እንደነሳቸው ያስረዳሉ። አገሪቱ በደም እየታጠበችና በቂም እየነፈረች ጥቅም ህሊናና አእምሯቸውን ስለዘጋባቸው “ዜጎች” ማሰብ ለበሽታ አጋልጧቸዋል፤ ያነባሉ። ግራ በመጋባት “ህወሃቶች - ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?” በማለት ይጠይቁና አጭሩን መልዕክት “ከርስ እንደዚህ እውር ያደርጋል?” የሚል ጥያቄ ጠይቀው ይሰናበታሉ። “በጥልቅ ስንታደስ የጥፋት ሃይሎች ጊዚያዊ መነቃቃት ይከስማል” ሲል የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በህዳሴ ጋዜጣ ላይ ያሰፈረውን አመልክተው፣ “በፍጥነት ወደ ጥልቁ ብትገቡ ለአገሪቱ ዘላለማዊ መነቃቃት ይሆን ነበር” የሚል ርዕስ በመስጠት ከላይ በመግቢያ የተገለጸውን የጠቆሙት የሃዋሳ ነዋሪ መሆናቸውን የጠቆሙ ደንበኛችን ናቸው። ብዙዎች እንደሚስማሙት ራሱን … [Read more...] about “ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?”
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው
በትያትር ድርሰት ጽሁፎቹ ፤ በትርጉምና የግጥም ስራዎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ (ነፍሱን ይማርና) በ1987 ዓ.ም እዚህ በስደተኛነት ነዋሪ የሆንኩበት ሆላንድ ሀገር መጥቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጎልን ነበር። እንደሚታወቀው ጋሽ ጸጋዬ የወያኔ መንግስት ስልጣን ላይ እንደወጣ የደረሰው ወይም የጻፈው አንድ “ሀሁ ፐፑ” የተሰኘ የትያትር ስራው ለህዝብ እንዳይታይ ታግዶበት ነበር። አዋሳን በመሰሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ደግሞ ተዋንያን መድረክ ላይ ሆነው ትያትሩን ሲተውኑ በወያኔ ወታደሮች በዱላ እየተደበደቡ ተውኔቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ሌላው ቀርቶ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ለታላቁ ጸረ-ፋሽስት፤ የኢትዮጵያ ሰማእትና አርበኛ ለአቡነ ጴጥሮስ ማስታወሻ የደረሰውን “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” የተባለውን ትያትር ለህዝብ … [Read more...] about ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው
የሁለት እስረኞች ወግ!
አዋቂው፣ ዕውቁ እና ተወዳጁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ትሁቱ እና ሠላማዊው ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን በአካል ያየኋቸው በ2003 መጨረሻ በአንድነት ፓርቲ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነበር። ያኔ በጋራ የምንጦምርበትና ለእስር የዳረገን ዞን ዘጠኝ አልተመሠረተም ነበር። ነገር ግን ጓደኞቼ እና ባልደረቦቼ Soleyana እና Atnaf ሳንተዋወቅ በፊት እዚያ እንደነበሩ ኋላ ስናወራ ሰምቻለሁ። በርካታ ሰዎች በተገኙበት ያ ስብሰባ ላይ ዛሬ ዝዋይ ወኅኒ የተጣለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ተገኝቶ ነበር። ያቺ ስብሰባ እስክንድር ጥናታዊ ንግግር ያቀረበባት ስብሰባ ነበረች። ጥናታዊ ንግግሩ እና ውይይቱ በጥቅሉ በእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ የተከሰሱት 24 ሰዎች ላይ ማስረጃ ሆኖ መጥቷል። የእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ ብዙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች የተከሰሱበት መዝገብ ነው። የአዲስ … [Read more...] about የሁለት እስረኞች ወግ!
ምነዋ አቦይ ዓባይ!
ምነዋ አቦይ ዓባይ ጸሐዬ! በደም የሰከረውን ድፍርስ ዓይንዎን እያጉረጠረጡ ከስሙኒ ቀለሉሳ! ደኅናም ብቅል አልጠጡም? አቦይ በሚባሉበት ዕድሜዎ እንዲህ መዘላበድ?! ሽማግሌ አልነበሩም እንዴ?! ብቻ - አይ የኔ ነገር! ተሳስቼ! የናንተ ሽማግሌ የለውም ለካ! መዘላበድና መዛት ልማድዎ ነው። በዚያን ሰሞን፣ “ለጭቁን ብሔር ብሔርሰብ” ደረስንለት ባሉት አንደበትዎ፣ ኦሮሞ ወንድሞቻችንን “ልክ እናስገባዋለን” ብለው አልነበር። አቦይ ዓባይ! እግዚአብሔር፣ እንኳን ከዛተና ከወረወርም ያድናል። ኦሮሞው አንዲት ብረት ሳያነሳ በባዶ እጁ ልክ አስገባችሁ አይደል? ሲዋሹ መቼም ዕድሜዎን እንኳን ግምት ውስጥ አያስገቡም። ሲዝቱ በጆሮአችን እየሰማንዎት፣ በነጋታው፣ “አላልኩም! አልወጣኝም”፣ ተቆርጦ የተቀጠለ ድምጼ ነው እንጂ እኔ እንደዚያ አላልኩም እያሉ ሲዘላብዱ ያኔ ሰምተን፣ ታዝብንዎት። እንደገና … [Read more...] about ምነዋ አቦይ ዓባይ!