በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ መነሻ አሳብ ትረካ እና የእለቱ የውይይት አጀንዳ በሆነው ያለፉት 25 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ገለፃ በኋላ በምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተነሱ አስተያቶች እና የአካሄድ ጥያቄዎች:-
1. የመጀመሪያ ተናጋሪ፡-
1.1 “የዚህ ወይይት አጀንዳ ከጠበኩት በታች ወርዶብኛል በወላይቲኛ አንድ አባባል አለ – ያቺ እንትን’ኮ ወደቀች ቢሏት፤ ቀድሞም አቀማመጧ ለመውደቅ ነው አለች”፡፡
1.2 “ካሳ! አንተ ሚኒስትር ነህ በዛ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ሊቀመንበር በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ውስጥ ሆኖ PhD candidate መሆን አይቻልም ስለዚህ ስራህን ልቀቅ”
1.3 “ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይምጣና ያወየን፣ እናንተ ውረዱና ከእኛ ጋር ተቀመጡ”
2. ሁለተኛ ተናጋሪ
2.1 “ይቺ ሀገር አንደ ሀገር አንደትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት፣ በዚህ ስብሰባ አኛ የእናንተን እንከን እናውራ እናንተ ደግሞ ዝም ብላችሁ አድምጡን”፡፡
3. ሦስተኛ ተናጋሪ
3.1 “የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ የውይይት መድረክ ብዙ ቁም ነገሮች ተነስተው ነበር ነገር ግን አንዳቸውም ሳይተገበሩ ዛሬ ደግመን ተገናኘን”
3.2 “አቶ ካሳ የመንግሰት ስልጣን ይዘህ ለግል ጥቅምህ በማዋል የዩኒቨርስቲውን ህግ ጥሰህ PhD candidate ሆነሐል”
3.3 “ውይይቱን የመምራት ሞራል የለህም”
የአቶ ካሳ መልስ፡-
1. “እኔ ውይይቱን የመምራት ችግር የለብኝም፣ ከእኔ የምትበልጡ ትልልቅ ምሑራንና ባለዕውቀቶች እንደላችሁ እሙን ነው ነገር ግን በአጋጣሚ የቦርድ ሰብሳቢ ሆኜ እስከተቀመጥኩ ድረስ ወይይቱን የመምራት ኃላፊነት አለብኝ”
2. “ይህ የውይይት መድረክ በመላ ሀገሪቱ ባሉ የትምህርት ተቋማት የሚደረግ እና መድረኩም አንዲመራ የተያዘለት ፕሮግራም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆን በቦርድ ለቃነመናብርት ነው”
3. “አኔ ብማር ክፋቱ ምንድን ነው? እኔም’ኮ አንድ ዜጋ ነኝ፣ ትምሀርት የመጀመሩን እድል አግኝቼ ነበር ነገር ግን ጊዜ በማጣት ምክንያት ብቻ class attend ባለማድረጌ ለመቀጠል አልቻልኩም፣ ጊዜ ሲኖረኝ ግን ታሰተምሩኛላችው”
በመቀጠልም ከተሰብሳቢ ምሁራን አንዱ አጁን በማውጣት ማሳሰቢያ እንዳለው ተናገረ፤ አንዲናገር ዕድሉ ሲሰጠውም “በመጀመሪያ ይሄ ስብሰባ ሲጀመር በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በኮንሶ በአልሞ ተኳሾች ለተገደሉ ንፅሑን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ሊሆን ይገባ ነበር” በዚህ ጊዜ የስብሰባው አዳራሽ ለረጅም ደቂቃ ባልተቋረጠ ጭብጨባ ተስተጋባ ሲቀጥልም “ሁሌም ተደጋጋሚ አጀንዳ ነው ይዛችው የምትመጡት ካችአምና የትምህርት ጥራት አምና እና ዘንድሮም የትምህርት ጥራት ምንም አዲስ ነገር የለም፣ ለዚህ ስበሰባ የተመደበው በጀት ተቀንሶ በተለያዩ ክልሎች በተነሱ ግጭቶች የቤተሰባቸውን አባላት ላጡ ወገኖች ይሰጥ ለእኛ የሶስት ቀን ውይይት ይበቃናል”
* ቀጣይ ተናጋሪ
“ሰው አየሞተ እና ህዝብ ለተቃውሞ እየወጣ political crisis ውስጥ ገብተን ስለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት መወያየት አኔን ያሳፍረኛል”
“ታልሞ የተመጣው ነገር ለኢቢሲ ዜና የሚሆን ነገር ለመቃረም ነው”
* ሌላ ተናጋሪ
“Next time I don’t want to see these board members (አቶ ካሳን ጨምሮ መድረኩን እየመሩ ያሉትን የዩኒቨርሲቲውን የቦርድ አባላት ነው)
“ዶ/ር አድማሱ ባለፈው ጊዜ አሜሪካን ሀገር ውስጥ በሱፐር ማርኬት ውስጥ የደረሰብዎትን አይተናል እነርሱ እዛ ወላፈኑ ገና ለገና ይደርስብናል ብለው ይህን ካደረጉ አኛስ እዚህ እንፋሎቱ ውስጥ የምንቀቀለው ምን እናድርግ?” (ፎቶ: ለማሳያ የተወሰደ)
(መስከረም 9፣ 2009 ዓ.ም)
(ሱራፌል ሐቢብ)
Wondafrash says
Are you sure of talking what is going on ?
Lusif says
I admire the guy who said that politics is a dirty game. I think to is a tricky game too. It has its own rules and procedures. If one does not abide by those rules and follow those procedures, it is being like that ignorant frog that stays feeling comfortable in the boiling water.
I really appreciate the academic communities, despite, the pressure, hardship, lack of academic freedom, for their courageous commitment in fulfilling their professional duties and obligations.
Thanks to all of them, for producing an upright, inquisitive, fearless community of youth who do not want to live under servitude, demanded freedom, equality, justice, democracy, and peaceful, honorable harmonious living.
I really do not get what the ruling politician would loss by not honoring the principles of democratic way of life and peaceful living. If politics is a game they are playing it poorly and out of the ordinary. It is sad and unfortunate to the country, people, in fact, to everybody.
eunetu says
ይድረስ ትዝታየ ለሆነው
ለስድስት ኪሎው ግቢ
የዛሬ ባላባቶች/የነገውን ዛሬ ስለሚወስነው ብዙ አታስቡ!/
”ምሁረ ምሁራን”
አዲስ አበባ
ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ?
የፊታችሁ ወዝ/ኢሕአፓ ትለው የነበረው ላብ ሳይሆን/ ያበራል እኮ!
ምን እየበላችሁ ነው እባካችሁ?
ለመበላት/ለማብላት/እንጂ ለመብላት ባልታደለ ሕዝብ መካከል መኖር እንዲህ ያሳምራል ማለት ነው?
ወይ ጉድ!ይገርማል!ይህን የመሰለ ነገር ተቀብሎ የሚያስተናግድ አእምሮ ማግኘት መቻል???
ለሁሉም እስቲ አብረን እናውጋ /የት ሃገር ነው አሉ ሲያረጁ የሚጨዋወቱ ሃገር ሰዎች እናርጅና እናውጋ ይላሉ አሉ/
ማለትም እንደ ዛሬው እንመንትፍና እንብላና ሳይሆን በሥራ አርጅተው መልካም የአገር ጉዳይ አጀንዳ ጨዋታ ማለታቸው ነው አሉ!!!
በነገራችን ላይ ያ! ስንት በሳልና ላገር/ላስተማራቸው የዋህ ሕዝብ መብትና ነጻነት ሲሉ በርሃ ድረስ ወርደው የነበሩትን ጀግኖችን ያፈራው የአዲስ አበባው ዩኒቨርስቲያችን ሞቶ የተቀበረው እኮ ቂመኛው ሟቹ ፕራይም ሚኒስቴር የነበረው 40ውን ነባር መምህራን በዘር ለይቶ ያባረራቸው እለት ነው፤ የገዢው አማራ ቡድን ተሳታፊ መሆናቸውን ሳያውቁት ተቀጡበት!አይገርምም የእነ ዶ/ር መኮንን ቢሻው የተማሪዎች ፕሬዜዳንት መሆናቸው ሲያስጠምዳቸው? እባካችሁ ወገኖቼ ይች አገር እውነተኛና ታማኝ ልጆቿን የምትበላ፤ በአንጻሩ ግን ጩልሌ የጣሊያን እንቁላል/ቆርቆሮ ያለሽ በማለት ወገናቸውን ለባእድ ሲሰልሉ የነበሩትን የምትሾምና የምትሸልም በመሆኗ በደብተራ የተደገመ የመርገም ድግምት ሳይኖርባት አይቀርምና ማርከሻውን በእውነተኛ የሕዝብ ፍቅር ላይ በተመሰረተ የጋራ ትብብር እባካችሁ አብረን እንፈልግለት? ሁሉም ባለበት አካባቢ እየተቀራረበ ሃገራዊ ውይይት በማድረግ የማያልፍ ህያው ሃገርን የማዳን ሥራ እንሥራ? በተለያየ መንገድም በጥንቃቄ መልካም የሆነውን ሥራ በመደገፍ እንተባበር! ክፉን ክፉ በማለት እንቃወም!ተጸጽተው የሚመለሱ ካሉም ለመቀበል ልባችንን እናስፋው!ትዕግሥት ከጸጸት ያድናልና በመታገሥ የሚሞተውን የዋህ ወገናችንን ብቻ ሳይሆን ጨካኝ ገዳይ የሆነውን ሟችም አብሮ የማዳን ሥራ በማስተዋል በየሰፈራችን እየተመካከርን እንሥራ?
እውነት ነጻ ያወጣልና፣
አሁንም፣ ነገም፣ ሁልጊዜም!
እውነቱ ይነገር ነኝ፤
ቸሩ ቸር ያሰንብተን!
የገባው ብልህ ደግሞ፣
አሜን ቢል ይጠቀማል።