እንደ መግቢያ
ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓትን የምትከተል አገር አይደለችም” ብዬ ፅፌ ነበር። ዛሬም ትንሽ አዳብሬ በዚሁ ላይ ትንታኔ መስጠት አምሮኛል። ይህ ጽሁፍ ደግሞ እንዲነሳልኝ የፈለኩበት ምክንያት በቅርቡ የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የሆኑት አቶ ስዩም መስፍንና አቶ አባይ ፀሃየ በቅርቡ በኢትዮጵያ “ወቅታዊ” ጉዳይ ላይ የተሰኘ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር ያዳመጠ ሁሉ የየራሱን ምልከታ ያስቀምጣል። እጅግ ብዙ ሰው ግን አዲስ ነገር የማይገኝበት ወቅታዊ የማይባል ያደርገዋል። አገሪቱን ህዝባዊ ተቃውሞ በሚንጥበት በዚህ ሰአት ቢያንስ ስለብሄራዊ መግባባት ስለ ብሄራዊ እርቅ ስለ ይቅርታ ማውራት ተገቢ ነበር። የፓለቲካ መሪ ምንም እንኳን የያዘው አቅጣጫ ለራሱ አዋጭ ቢመስለውም ነገር ግን ህዝብ ካልተቀበለው ራሱን ይመረምራል። ይህ ግን በኛ ሃገር ፓለቲካ አለመታየቱ ያሳዝናል። ስልጣን ለሚወዱ ባለስልጣናትም የስልጣን እድሜ የሚጨምረው ይቅርታና መታረም መለወጥ ነበር።
በዚህ “ወቅታዊ” በተሰኘው የነዚህ የህወሃት መሪዎች መግለጫ ውስጥ አንድ ነገር ስላስደመመኝ በዚያ ላይ በተለይ ለነዚህ ለሁለቱ መሪዎችና ለተከታዮቻቸው ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። በዚህ ገለፃ ወቅት አቶ ስዩም ስለ ፌደራል ስርአት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የፌደራል ስርአት “አለም የሚቀናበት” ነው ይሉናል። እንዴውም የኢትዮጵያ የፌደራል ስርአት የሌሎች ፌደራል አገሮችን የፌደራል ስርአት የገለበጠ ነው ይላሉ። ይህንን ሲያስረዱ የሌሎች ሃገራት የፌደራል ስርአት ፌደራሉ የተወሰኑ ስልጣኖችን ይሰጥና ከዚያ ቀሪው በሙሉ የኔ ነው ይላል ይሉናል።ይሰስታል አይነት ነው። ስልጣን የሚሸነሽነው ከላይ ያለው የፌደራል ስርአት ነው ይላሉ። በአንፃሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርአት ደግሞ የተገነባው ብሄሮች ትንሽ ትንሽ ቆንጥረው ስልጣን ወርውረውለት የተቋቋመ የፌደራል ሥርዓት ሲሆን ብዙውን ስልጣን ግን ብሄሮች ለራሳቸው እየተደሰቱበት እንደሆነ ያስረዱናል። ይህንን ሳዳምጥ አቶ ስዩም በከፍተኛ ሁኔታ የፌደራልን ጽንሰ ሃሳብ አለመረዳታቸውን አሳየኝ። ተከታዮቻቸው ሁሉ እንዲሁ ከተረዱት በውነት ከስረዋል። እኚህ ሰው እንደኔው ተራ ሰው ቢሆኑ አልሟገትም ነበር። ነገር ግን እኚህ ሰውና ፓርቲያቸው ያመኑበትን ተግባራዊ የሚያደርጉና ያደረጉ በመሆናቸው የኝህ ሰው ግንዛቤ አገርን ስላወከ ነው ለሙግት ያስነሳኝ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply