As I promised in my latest article entitled “Giving Negotiation a Fair Chance”, this article provides a glimpse into the plausible alternative futures of Ethiopia. My latest article got both positive and negative feedbacks. Some people misunderstood my suggestion and considered it as an effort to extend the ethnic apartheid rule of TPLF. This is regardless of a clear statement in the article that hinted the kind of negotiation I was talking about. I wrote in that article, “Rather than admitting … [Read more...] about A glimpse into the plausible alternative futures of Ethiopia
Archives for September 2016
ሞረሽ የዐማራ ድምጽ ሬዲዮ ሥራውን ጀምሯል!
የመጀመሪያውን ፕሮግራም ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ሞረሽ የዐማራ ድምጽ ሬዲዮ ሥራውን ጀምሯል!
የአንድ ሕዝብ አንድ ሀገር ድርጅት ምንድን ነው?
ውድ ኢትዮጵያዊያን፤ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sep. 18, 2016 አንድ ኢሜል ደረሰኝ። ሁለት መዝገቦችን አባሪ አድርጎ ነበር፤ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ባሸበረቀ ምልክት፤ አንድ ሀገር አንድ ሕዝብ ከሚል ድርጅት። ሁለቱን በየተራ አነበብኳቸው። ወዲያው የበለጠ ለመረዳት፤ ከተወሰኑ ጥያቄዎች ጋር መልስ ላኩላቸው። ድምጻቸው ጠፋ። ቀጥለው ከአንድ ሳምንት በኋላ፤ አሁንም የጀምላ፤“ድረገጻችን እይ!” ጥሪ ላኩልኝ። “ምነው መልስ ነፈጋችሁኝ!” በማለት መለስኩላቸው። ቀጥለው፤ “ያንተን ኢሜል አለገኝንም” ሲሉ መለሱልኝ። እድሜ ለቴክኖሎጂው ምጥቀት፤ በቀኗ የላኳትን ኢሜል ወደነሱ መራኋት። አይጥ እንደዋጠች ድመት፤ ድምጻቸውን አጠፉ። በዚህ ጥርጣሬዬ ላይ፤ በቫይቨር አንድ ቡድን ተፈጥሮ፤ የዚያ አባል ተደርጌ፤ ስልኬ በቫይቨር መልዕክት ይጣድፍ ገባ። “እንዴ! ይሄ የምን ቡድን ነው? እኔንስ ማነው ከዚህ … [Read more...] about የአንድ ሕዝብ አንድ ሀገር ድርጅት ምንድን ነው?
ከህወሃት የአናሳዎች ቁማር ጨዋታ ይጠንቀቁ!!
በቅርቡ ብዙዎቻችሁ እንደተመለከታችሁት፣ ህወሃት ሶማሊዎች ኦነግን ወይም ግንቦት ሰባትን በመቃወም ወጡ የሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው። መታወቅ ያለበት እውነት እንዲህ ዓይነቱን የህወሃት ድራማ እየተጫወቱ ያሉት ክልሉን አስተዳድራለው የሚለው አሻንጉሊት ፓርቲ አባላት ብቻም ሳይሆኑ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከሶማሊ ላንድ እንዲሁም ከኬኒያ የመጡ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች መሆናቸውን ነው። እብደት፣ ንዝላልነትና ስርዓት አልበኝነት የተጠናወተው የክልሉ የህወሃት ቅጥረኛ ፕሬዚዳንት አብሲ ኢሌ፣ ዛሬ የቡና ቤት ሰራተኞች ሳይቀር በማስገደድ ሰልፍ አስወጥቷል። የህወሃት አገዛዝ ይህንን ለምን አደረገ? በመጀመሪያ ይህ የሚያሳየው ህወሃት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ባበጃቸው ታዛዥና አሻንጉሊት የነበሩ ፓርቲዎችም ጭምር ሳይቀር መተፋቱንና ተስፋ መቁረጡን ነው። በነዚህ ሁለት ትልልቅ ክልሎች (ኦሮሚያና አማራ) … [Read more...] about ከህወሃት የአናሳዎች ቁማር ጨዋታ ይጠንቀቁ!!
በኢህአዴግ ጎጆ ያልበሰበሰው ማን ነው?
ተሰብሳቢዎቹ አገሪቱን “በስብሰናል፣ ሸተናል፣ ማስተዳደር አቅቶናል …” እያሉ ራሳቸውን የሚሰድቡት የኢህአዴግ ምክርቤት አላባት ናቸው። በእነርሱ አነጋገር አንድም “ልውጥ” ሰው መካከላቸው የለም። ሰብሳቢዎቹ “ቅምጥ” የሚባሉት ታማኝ የህወሃት ታዛዦች “ጓድ ሃይለማርያም ደሳለኝና ምክትላቸው ደመቀ መኮንን” ነበሩ። የኃይል አሰላለፉ በራሱ የቤቱንና የአስተዳደሩን መብከት የሚያሳብቀው ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎች ፊት የቆሙት ራሳቸው ኢህአዴጎች ነበሩ። በፊት አውራሪዎቻቸው ፊት ቆመው ሪፖርት የሚያቀርቡት ሰዎች ኢህአዴግ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በፊት አውራሪዎቻቸው የተሾሙ ነበሩ። የተሾሙት በድርጅቱ መዋቅር ስር ባሉ አደረጃጀቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ዘልቀው በመግባት እንዲያጠኑ ነበር። ከሙስና ጀምሮ ኢህአዴግ “ገለማሁና፣ በሰበስኩ” የሚልበትን መስመር መርምረው እንዲያቀርቡ የተሰየሙት … [Read more...] about በኢህአዴግ ጎጆ ያልበሰበሰው ማን ነው?
የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ!
* "አሰቃዩኝ" ስትል ፍልቅልቋን የ 6 ዓመት ብላቴና ለሚስን ቀጠፈቻት * ገዳይ ኢትዮጵያዊት ትናንት በሞት ተቀጣች * ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ ሁሉም ልብ ይሰብራል ይህን ሁለት ቀን ተረብሻለሁ፣ ምክንያቴ ብዙ ነው፣ ከምንም በላይ ከሪያድ የደረሰኝ መልዕክት ህመም ሆኖኛል ሰው ልምጣ ሲል እሷ "የመጨረሻ ቀናቶቸን የወላጆቸን አይን ሀገሬን ልይ እርዱኝ! ወደ ሀገሬ እንድገባ እርዱኝ!" የምትለው ታማሚ የኮንትራት ሰራተኛ እህት መልዕክት ጨካኙን ሰው ሆዴን አባባው። ማምሻውን ያነኑ ቪዲዮና ድምጽ ሳስተካክል ሌላ መረጃ እዚያው ሪያድ ደረሰኝና ቅስሜ ሰብር ብሎ አመሸ ... ኢትዮጵያዊቷ ሌላ የቤት ሰራተኛ በሞት መቀጣቷን ሰማሁ! እናም ወደ መረጃው አቀናሁ ... ድርጊቱ ሲፈጸምና መረጃው ሲናኝ ተከታትዬ መረጃ አቅርቤበት ነበርና ያንኑ ጊዜ እያስታዎስኩ የፍርድ ውሳኔውን ዜና ገለባብጨ … [Read more...] about የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ!
መለኮታዊ ጥያቄ
"ኤርምያስ ሆይ ምን ታያለህ" (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 1፡11)፡፡ እ.አ.አ 1519 ቤተሰቦች ልጆቻቸውን አሥርቱን ትእዛዛትና (አቡነ ዘሰማያት) በጥልቀት እንዲያጠኑ በማስተማራቸው (በርካታ ክርስቲያኖች በአውሮጳ) በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፡፡ እ.አ.አ በ1536 ቲንደል የሚባል የእግዚአብሔር ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎሙ በእንጨት ላይ ታስሮ በእሳት ተቃጥሎ ተገድሎአል፡፡ ጆን ዊኪሊፍ መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን በመተርጎሙ ተወግዞአል፤ ከሞተ ከ44 ዓመት በኋላ አጥንቱ ወጥቶ እንዲቃጠል ተድርጎአል፡፡ እንዲህ ዓይነት እኩይ ድርጊት እንዲከናወን ያደረጉት የቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ጨካኝ የሆኑ በዘመኑ የነበሩ የፖለቲካ ሰዎች አማካኝነት እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ከላይ የተመለከትነው እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርምያስን የጠየቀበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል … [Read more...] about መለኮታዊ ጥያቄ
“ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጂ በተመሪ አይደለም”
የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም ታሪክ ሰሩ። ከፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላዎች ፊት ለፊት እውነትን ተጋፍጠዋል። ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። እንዲህም አሉ... "ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለበት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን፤ ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን? መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ … [Read more...] about “ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጂ በተመሪ አይደለም”
የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት
የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኗል፤ ይህ የሚያከራክር አይመሰለኝም፤ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ በጠመንጃ ጉልበትና በሲአይኤ ድጋፍ ሰንጎ የገዛ ቡድን በቃህ ቢባል አይደንቅም፤ ሌላው ጥያቄ ‹‹የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የሚቻለው እንዴት ነው?›› የሚል ሲሆን በዚህ ላይ ስምምነት ያለ አይመስለኝም፤ መልሱ ሰላማዊ ወይም የትጥቅ ትግል የሚል ምርጫ ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔን አገዛዝ ለማውረድ የተሰለፉትስ እነማን ናቸው? ዓላማቸውስ ከቃል ባሻገር ምንድን ነው? የሚልም ይሆናል፤ ባልተቀነባበረ መንገድ በተለያዩ ቦታዎች አሁን የሚታዩትና በያለበት ኩፍ ኩፍ የሚሉት የመንተክተክ ምልክቶች ለወደፊቱ ሥርዓት ያለውን ሰልፍ አያሳዩም፤ አዲስ ነገርና የምሬቱ መግለጫ መገዳደል መጀመሩ ነው፤ ገዳይ መለዮ ለባሹ ብቻ መሆኑ እየቀረ ነው፤ እነዚህ ምልክቶች ለውጥ … [Read more...] about የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት
እንባችን ተሟጧል
በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ በሩቁ ያላችሁና በፊታችሁ ቆሜ የምታዩኝ ቤተ እስራኤሎች፦ ክርስቲያኖች፦ ሙስሊሞች፦ ሁላችንም የምንስማማበትን በሙስሊሙ አባባል ዘቡር በሚባለው በዳዊት መጽሐፍ የተመዝግበውን በውስጥ ከሚሰቃየው ወገናችን ጋራ በመተባበር “ተካውኩ ከመ ማይ ወተዘርዎ ኩሎ አዕጽምትየ ወኮነ ልብየ ከመ ሰም ሰይትመሰው በማእከለ ከርስየ” (መዝሙር 22፡ ) ለማለት በዚህ ቦታ ተሰብሰበናል። ይህም “መላ ሰውነቴ ወደ ውሀነት ተለውጦ ተደፋ። አጥንቴም ደቅቆ ወደ አፈር ትቢያነት ተለውጦ ተበታተነ። ልቤም እንደሰም ቀልጣ በአንጀቴ ፈሰሰች” ማለት ነው። ወደ ውሀነት ተለውጦ ወደ መሬት ከተደፋ ሰውነት እንባ አይታሰብም። ወደ ትቢያነት ተለውጦ ከተበተነ አጥንትም ቁመተ ሥጋ የለም። እንደ ሰም ቀልጦ በአንጀት ከፈሰሰች ልብ በሰውነት የሚሰራጭ ደም የለም። ኢትዮጵያውያን ሁላችንም ከዚህ … [Read more...] about እንባችን ተሟጧል