በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ በሩቁ ያላችሁና በፊታችሁ ቆሜ የምታዩኝ
ቤተ እስራኤሎች፦
ክርስቲያኖች፦
ሙስሊሞች፦
ሁላችንም የምንስማማበትን በሙስሊሙ አባባል ዘቡር በሚባለው በዳዊት መጽሐፍ የተመዝግበውን በውስጥ ከሚሰቃየው ወገናችን ጋራ በመተባበር “ተካውኩ ከመ ማይ ወተዘርዎ ኩሎ አዕጽምትየ ወኮነ ልብየ ከመ ሰም ሰይትመሰው በማእከለ ከርስየ” (መዝሙር 22፡ ) ለማለት በዚህ ቦታ ተሰብሰበናል። ይህም “መላ ሰውነቴ ወደ ውሀነት ተለውጦ ተደፋ። አጥንቴም ደቅቆ ወደ አፈር ትቢያነት ተለውጦ ተበታተነ። ልቤም እንደሰም ቀልጣ በአንጀቴ ፈሰሰች” ማለት ነው።
ወደ ውሀነት ተለውጦ ወደ መሬት ከተደፋ ሰውነት እንባ አይታሰብም። ወደ ትቢያነት ተለውጦ ከተበተነ አጥንትም ቁመተ ሥጋ የለም። እንደ ሰም ቀልጦ በአንጀት ከፈሰሰች ልብ በሰውነት የሚሰራጭ ደም የለም። ኢትዮጵያውያን ሁላችንም ከዚህ ላይ ደርሰናል። ይህን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት እስከ ህልፈተ ዓለም የማይረሳውን ታሪክ ወያኔዎች ገና ሲመሰረቱ ባማራው ጀመሩት። በኦሮሞው ላያ ቀጠሉ፤ በየጠረፉ ባሉት ኢትዮጵያውያን ጎሳዎች ሁሉ ላይ ፈጸሙት።
ይህን ግፍና መከራ በእግዚአብሔር ቃል በመለካት መወገዝ እንዳለበት ከኔ በፊት ምስክርነታቸውንና ወገናዊ ስሜታቸውን የገለጹት ወገኖቼ ተናግረውታል።
እኔ መናገር የፈለጉት፤ ኢትዮጵያ አገራችንን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ስለሚያሳይና የዕለቱም በዓል ስለሆነ የደመራ በዓል ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በያመቱ እንዲታወስ ለምን እንዳደረግችና ለትግራይ አዛውንቶች ካህናትና ሊቃውንትም የሚመለከት ተገቢ ታሪካዊውን መልእክት ስላለው ላቀርብላቸው ስለፈለኩ ነው።
(ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply