• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአንድ ሕዝብ አንድ ሀገር ድርጅት ምንድን ነው?

September 28, 2016 07:12 am by Editor 1 Comment

ውድ ኢትዮጵያዊያን፤

በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sep. 18, 2016 አንድ ኢሜል ደረሰኝ። ሁለት መዝገቦችን አባሪ አድርጎ ነበር፤ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ባሸበረቀ ምልክት፤ አንድ ሀገር አንድ ሕዝብ ከሚል ድርጅት። ሁለቱን በየተራ አነበብኳቸው። ወዲያው የበለጠ ለመረዳት፤ ከተወሰኑ ጥያቄዎች ጋር መልስ ላኩላቸው። ድምጻቸው ጠፋ። ቀጥለው ከአንድ ሳምንት በኋላ፤ አሁንም የጀምላ፤“ድረገጻችን እይ!” ጥሪ ላኩልኝ። “ምነው መልስ ነፈጋችሁኝ!” በማለት መለስኩላቸው። ቀጥለው፤ “ያንተን ኢሜል አለገኝንም” ሲሉ መለሱልኝ። እድሜ ለቴክኖሎጂው ምጥቀት፤ በቀኗ የላኳትን ኢሜል ወደነሱ መራኋት። አይጥ እንደዋጠች ድመት፤ ድምጻቸውን አጠፉ።

በዚህ ጥርጣሬዬ ላይ፤ በቫይቨር አንድ ቡድን ተፈጥሮ፤ የዚያ አባል ተደርጌ፤ ስልኬ በቫይቨር መልዕክት ይጣድፍ ገባ። “እንዴ! ይሄ የምን ቡድን ነው? እኔንስ ማነው ከዚህ ያስገባኝ?”ብዬ ላክሁ። መልስ የለም። እንዲህ ከሆነ አልኩና፤ “በሉ ያስገባችሁኝ ከማላውቀው ቡድን ስለሆነ፤ ያስገባኸን ሰው፤ ስልኬን ሰርዝ።” በማለት ጻፍኩ። ወይነሱ! ጉዳያቸውም አልሆነ። ሳገላብጥ፤ ያስገባኝን ስልክ ቁጥር አገኘሁ። ብዙም ጥረት የሚጠይቅ አልነበረም። ያንን ቁጥር በመጻፍ፤ “አንተ ሰው ስሜን ሰርዝ አልኩ።” ወይ ፍንክች! የስልኩን ባለቤት ስም አግኝቼ፤ ስሙንና የስልክ ቁጥሩን በማስፈር፤ “አንተ ሰው የስልክ ቁጥሬን ከዚህ የቡድን መልዕክት አውጣው!” አልኩት። ይሄን ሁሉ ያደረግሁት፤ እንደኔ ሌሎችም ተመሳሳይ ችግር አጋጥሟቸው ይሆናልና፤ እኔ ጥዬ በቀላሉ ከመሄድ፤ ምንአልባት ሌሎችም ይታዘቡት ይሆናል በማለት ነበር። በመጨረሻ ይህ ስም የስልኩ ባለቤት ሳይሆን፤ ስልኩን ከሁለት ዓመት በፊት ያስረከበውና ዛሬ ሌላ ስልክ የያዘ ሰው ስም ነው። ማለትም፤ በድሮ ባለቤቱ ስም፤ አሁን ተጠቃሚ በመሆን የወሰደ የድብቅ ድርጅት ስልክ ነው። የት እየሄደ እንደሆነ ገምቱ!

ዋናው ነገር፤ ይህ የተቀነባበረ፤ የፀረ-ትግሉ ቡድን ስልታዊ እርምጃ ነው። እኔ ከብዙዎቹ በተለየ መንገድ፤ በኢትዮጵያ ሀገራችን እየገዛ ያለውን የትግሬዎች ቡድን በጣም አደንቃለሁ። ይህ የትግሬዎች ቡድን ዓላማውን በደንብ ያውቃል። ለዚህ ዓላማው የማያደርገው ነገር የለም። ከዚህ ዓላማው ደግሞ ፍንክች አይልም። ዓላማውም አማራውን ከምደረ ገፅ ማጥፋትና ኢትዮጵያን መበታተን፤ ከዚያም የትግራይን ሪፑብሊክ ማቋቋም ነው። ይህን ለማድረግ የማያውጠነጥነው ሴራ፤ የማይደርተው ነገር የለም። እናም ጎበዝ ነው። ይህ ቡድን ይህን ሠራ፤ ያንን ደገመ ቢባል ደንታው አይደለም። አንዳንዶቻችን ዛሬ ይሄን ሠራ፣ ነገ ያን ደገመ ማለቱን ትግል አድርገን ይዘነዋል። ይህ ወራሪ ቡድን ግን ይስቃል። እኛ ምን እያደረግን ነው? የዚህን የአማራን ዘር አጥፊና ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን ተግባር መዘርዘር ላይ ተወዝፈናል።

እኔ ለዚህ ለደረሰኝ ኢሜል መልስ ስሠጥ፤ አንድ ነገር ይዤ ነው። ማንኛውም የሕዝብ ወገን የሆነ ድርጅት ሲልክልኝ፤ ምንም እንኳ መርኀ-ግብሩ ፍፁም የማልወደውም ቢሆን፤ የሕዝብ አካል ነውና፤ በጠቅላላ ሀገራዊ ትግሉ ይታቀፍ ዘንድ፤ ወደ አንድ እንድንካተት በማለት ነበር። ከዚህ በፊት፤ በትግሉ ያሉ ድርጅቶች በአንድነት እንዲሰባሰቡ ብዙ ሙከራ አድርጌያለሁ። አልተሳካልኝም። አሁንም ይህን ወራሪ ፀረ-ኢትዮጵያ አጥፊ ቡድን በአንድነት እስካልተነሳንበት ድረስ፤ ትግሉ ይራዘማል። ወደ ዋናው መልዕክቴ ልመለስ። ይህ የተላከልኝ ኢሜል – ለብዙዎቻችሁ ተልኮላችኋል – ሀገር ወዳድ የሚመስልና፤ ከአማራው ክፍል የወጣ የሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችን ታሪክ ያላካተተ ከመሆኑም በላይ፤ ሌሎች አማራውን እንዲጠሉ “ይሄው የአማራው አደረጃጀት!” በማለት ይህ የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን ለቀመረው ማቃቃሪያ ዘዴው፤ መረጃ እንዲሆን ነው። እናም የኢሜሎችን አድራሻዎች ከየትም ሰብስቦ፤ የስልክ ቁጥሮችን ለቃቅሞ ዶሴውን አዘጋጅቷል። ብዙዎቻችን ባለማወቅ መንገድ የዚህ ስብስብ አባል ተደርገናል። ተመከቱ፤ ይህ የትግሬዎች ገዥ ቡድን፤ የመንግሥታዊ መዋቅሩን ለሱ ዓላማ ሙሉ በሙሉ ሲያውለው! ይህ ለማንኛችንም አዲስ አይደለም። ነገር ግን፤ ዘዴው አዲስ ነው፤ ቢያንስ ለኔ።

እናም ለዚህ የትግሬዎች ቡድን አንዱ የትግል ማደናቀፊያ፤ ታጋዮችን መከፋፈል ነው። ይህ ድርጅት የተፈጠረው፤ ይህን በተግባር ላይ ለማዋል ነው። በሀገር ውስጥ አልሠራለትም። በሀገር ውስጥ ትግሉ በግልጽ ተቀምጧል። በውጪ ላለነው መንገድ አለው። አሁን በውጪ ባለነው ታጋዮች በኩል ሁለት ክፍሎች ዘልቀው ይታያሉ። የመጀመሪያው ክፍል፤ በእድሜ እንደኔ በገፋነውና፤ “ኢትዮጵያዊ ነኝ!” እያልን ባደግነው በኩል የሚቀነቀነው ነው። እኔ በንጉሰ ነገሥቱ ጊዜ፤ በዩኒቨርሲቲ ተማሪነትና በአስተማሪነት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። በደርግ ጊዜ ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ትጥቅ ትግል ድረስ፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። ይህን የትግሬዎች ቡድንም ታጥቄ በጦርነት፤ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። ይሄን ሁሉ ያደረግሁት በኢትዮጵያዊነቴና ለአንዲት ኢትዮጵያ ነበር።

በዚህ ክፍል ያለነው በዚህ ዓላማ እንዳለን ነን። ከአርባ ዓመት ወዲህ ያሉትና የዛሬዎቹ ወጣቶች ደግሞ፤ ዛሬ በምድሯ ላይ ባለው የፖለቲካ ሀቅና፤ ዓይኑን አፍጥጦ ጎልቶ በመጣው ቅራኔ ተመስርተው፤ በትግሬዎቹ ገዥዎችና፤ እንዲጠፋ በፈረዱበት አማራ፤ በትግሬዎቹ ገዥዎችና በደሉ በበዛበት ኦሮሞ፣ አኝዋክ፤ ኦጋዴኒ፣ ወዘተ. ሆኗል። እኒህ ሁለት ክፍሎች፤ ማለትም ወጣቶቹና ቀደምተኞቹ፤ አንድ ጠላት አለን፤ የትግሬዎቹ ገዥዎች። እናም ባንድነት ብንሰለፍ የዚህን ወራሪ እድሜ ልናሳጥር እንችላለን። በመካከላችን ያለውን ክፍተት ለማስፋትና እርስ በርስ ለማባላት፤ ይህ ወራሪ የትግሬዎች ቡድን እየጣረ ነው። የግድ ይሄን ተገንዝበን፤ ተመካክረን ወደ አንድ ሰፈር መሰባሰብ ግዴታችን ነው። አንዳችን የሌላችን ጠላት አይደለንም።

በኔ በኩል እስከዛሬ በኢትዮጵያዊነት መታገሌ ትክክለኛና የምኮራበት ታሪኬ ነው። ይህ ከአርባ አምስት ዓመት በላይ የሆነውትግሌ፤ በተጨባጩ የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ተመርኩዤ የወሰድኩት የፖለቲካ ትግል ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ምን ጊዜም ቢሆን፤ የፖለቲካ ትግል የትናንት አይደለም። የፖለቲካ ትግል እኛ እያንዳንዳችን ወይም በጥቅል በያዝነው እምነት ላይ አይመሠረትም። በኛ ፍላጎትም አይካሄድም። ምኞት ጥሩ ነው። ፍላጎት ጥሩ ነው። ምኞትና ፍላጎት ግን በመሬቱ ላይ ያለውን ሀቅ አይተኩም። የፖለቲካ ትግል በመሬቱ ባለው የፖለቲካ ሀቅ ላይ የተመሠረተ ነው። በሀገራችን ባለው የአሁን የፖለቲካ ሀቅ ላይ የተመሠረተ ትግል እንጂ፤ በኔ ጭንቅላት ወይንም ፍላጎት ላይ የተመሠርተ ትግል ዕርባና የለውም። ስለዚህ እኔ እስከዛሬ የነበረኝ አቋምና ያደረግሁት የፖለቲካ ትግል ትክክልነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አሁን ግን፤ በሀገራችን ያለው ተጨባጭ የፖለቲካ ሀቅ፤ ሌላ ትግል ጠይቆኛል። አቤት ብየዋለሁ። በሀገራችን ያለው የፖለቲካ ሀቅ፤ የትግሬዎች የበላይነትና የአማራዎች እንዲጠፉ መደረግ፣ የትግሬዎች የበላይነትና የኦሮሞዎች መደቆስ፣ የትግሬዎች የበላይነትና የአኝዋክ ከቁጥር ውጪ መደረግ፣ የኦጋዴኑ መበደል ነው። እናም ትግሉ፤“አማራ መሆኔ ለመጥፋት ከዳረገኝ፤ ለአማራነቴ፤ ለሕልውናዬ መታገል አለብኝ!” ሆኗል። ኦሮሞውም፤ አኝዋኩም፣ ኦጋዴኑም፣ በተመሳሳይ መንገድ።

አሁን በውስጤ፤ የፖለቲካ አማራ ተፈጥሯል። አማራነትን ፈልጌ ወይንም ኦሮሞነትን ጠልቼ አልተወለድኩም። ኢትዮጵያዊነቴን ስወለድ ያገኘሁት የፖለቲካ ማንነት ነበር። ያኔ ሌላ የፖለቲካ ማንነት አልነበረም። አማራነት በሰውነት ውስጥ የሚዘዋወረውን ደም መምጫ ተናገሪ እንጂ ሌላ ሚና አልነበረውም። አሁን ግን አማራነቴ የፖለቲካ ማንነት ሆኗል። ያን ወደድኩም ጠላሁም መቀበል፤ ግዴታዬ ሆኗል። ይሄ ለሁላችሁም ግልጽ ስለሆነ ማተቱ መደረት ነው። እኔም በአማራነቴ፣ የአማራውን ሕልውና ለመጠበቅ፤ አማራ ነኝ ብዬ ተነስቻለሁ። ለአማራው በአንድነት መነሳት እታገላለሁ። ለሃያ አምስት ዓመት ተዘርዝሮ የማያልቅ በደል የደረሰበት ወገኔ፤ ሕልውናውን ለመጠበቅ ትግል ላይ ነው። ያሁኖቹ ከአርባ ዓመት በታች ያሉት ወጣቶች የያዙት ትግል ይህ ነው። አሁን በሀገራችን ባለ የፖለቲካ ሀቅ የጎላ ቅራኔ ላይ የተመሠረተ! ለዚህ ሲታገሉ፤ ይህ የኔ ትግል ሆኗል።

እስከዛሬ ኢትዮጵያዊያን ታጋዮች ወደ አንድ እንድንሰባሰብ ጥሬ ነበር። ዛሬ ትምህርት ወስጃለሁ። እኔ ስለፈለግሁ የሚሆን ነገር የለም። በቦታው ያሉ ታጋዮች ወሳኞቹ ናቸው። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ዕድልና ዕጣ፤ በምናውቃቸው በውጪ ባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሳይሆን፤ በትግሉ በተሰማሩት የአማራ ወጣቶች፤ የኦሮሞ ወጣቶች፣ የአኝዋክ ወጣቶች እና አሁን በትግሉ በሀገራችን በተጠመዱት ታጋዮች እጅ ነው። አሁን የምጥረው፤ በአማራ ስም ተለያይተው የሚንቀሳቀሱ በውጪ ያሉ ታጋዮች፤ ወደ አንድ እንዲሰባሰቡ ነው። በጎን ደግሞ ሌሎችም ተሰባስበው በዚህ በወራሪ የትግሬዎች ቡድን ላይ እንዲነሱ ነው። ይህ በሀገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ ሀቅ ግድ ያለው ነው። እኔ ሀቁን ተቀብዬ መታገል እንጂ፤ ራሴ በጭንቅላቴ ሀቅ ፈጥሬ፤ በዚያ ሀቅ መታገል አይደለም ሀገራዊና ታሪካዊ ግዴታዬ።

ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር ለመሥራት ዝግጁነቴን አብስሬ፤ ታታሪው የትግሬዎች ቡድን የሚያደርገውን አስተውለን መገንዘብ አለብን! እላለሁ። ገና ለገና ነገ በትግሬዎች ላይ አደጋ እንዳይደርስ ትግሬዎች ግራና ቀኝ አሁን በአማራው ላይ የግፍ ዶፍ ለሚያደርሱት ትግሬዎች ሲቆሙ፤ እኔ አማራ ነኝ የማልልበትና፤ ለአማራው እንዳልቆም የሚያግደኝ አእምሮ የለኝም። ዛሬ በአማራው ላይ ኢንተርሐውሜ እየተሰራ፤ ነገ በትግሬዎች እንዳይሠራ ብሎ መቆም መታወር ነው።

አንዱዓለም ተፈራ  – የእስከመቼ አዘጋጅ

ረቡዕ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፱ ዓመተ ምህረት


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    September 30, 2016 10:55 pm at 10:55 pm

    Dear Sir,
    I read your post with interest. I found sensible and informative. As you clearly stated, there is a misunderstanding and paradigm gap between your generation and current youth generation. From what I read and daily observations, your generation is too ideological, deterministic and self -righteous. Everything must be shaped, molded and craved out, according its visionary ideology, i.e. there is no other way, what so ever.
    The current Ethiopian generation of youth, regardless what ethnicity one belongs, is very dynamic and pragmatic. In this changing world, it is a valueless assent to be aware of what is not working and know what is actually working.
    The old generation has only a formula. Any individual of group that does not confirm to that formula, he is either… or….. I guess that is why Ethiopian political parties that are led by the old generation never get along. The current Youth generation has a flexible all weather formula. The youth’s mottoes are:- freedom, equality, justice and democracy. To be member of this efforts, just takes to be human.They believe that, only free and equal citizens can reach mutual consensus and respect, that ensure enduring peace and stability. It is not accidental that we all hear ” your blood is my blood. His death and suffering is ours’ too.” It is the result of development and growth of consciousness to a different level.
    Most Ethiopian youths destroyed and level down the dividing ethnic wall and are struggling against oppression and injustice, so that everyone can be free and equal. Not a particular group.
    There is no hatred or enmity between or among people, like many different groups propagate to make us believe. The Ethiopian youth, unlike any other group, very well knows what its enemy is: It is tyranny. Tranny has no ethnicity. It is a wild monster that devour on any thing, even the lesser monster of its own. That is why, from every corner, the Ethiopian youths joined hands and stood firm against such monster.
    Recently, I heard some individuals from the old generation acknowledging that they have been lagging behind the youths’ understanding of reality. That is obvious. However, there is still time and opportunities to reinforce the youths effort in any capacity one can.
    That is my understanding about the current position of The Ethiopian Youth.
    Thanks.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule