• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሁለት እስረኞች ወግ!

September 16, 2016 07:51 am by Editor Leave a Comment

አዋቂው፣ ዕውቁ እና ተወዳጁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ትሁቱ እና ሠላማዊው ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌን በአካል ያየኋቸው በ2003 መጨረሻ በአንድነት ፓርቲ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነበር። ያኔ በጋራ የምንጦምርበትና ለእስር የዳረገን ዞን ዘጠኝ አልተመሠረተም ነበር። ነገር ግን ጓደኞቼ እና ባልደረቦቼ Soleyana እና Atnaf ሳንተዋወቅ በፊት እዚያ እንደነበሩ ኋላ ስናወራ ሰምቻለሁ። በርካታ ሰዎች በተገኙበት ያ ስብሰባ ላይ ዛሬ ዝዋይ ወኅኒ የተጣለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ተገኝቶ ነበር። ያቺ ስብሰባ እስክንድር ጥናታዊ ንግግር ያቀረበባት ስብሰባ ነበረች። ጥናታዊ ንግግሩ እና ውይይቱ በጥቅሉ በእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ የተከሰሱት 24 ሰዎች ላይ ማስረጃ ሆኖ መጥቷል።

የእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ ብዙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች የተከሰሱበት መዝገብ ነው። የአዲስ ነገሮቹን ዐብይ ተክለማርያም እና መስፍን ነጋሽ ጨምሮ፣ ከእስክንድር ሌላ አምስት ጋዜጠኞች በዚህ መዝገብ ተፈርዶባቸዋል።

እስክንድርን እና አንዱዓለምን ከዚያ በኋላ ያገኘኋቸው እና የማናገር ዕድል የገጠመኝ ከታሰሩ በኋላ በቃሊቲ (እኔ ራሴ ከመታሰሬ በፊት) ነው። እስክንድር ነጋ ላይ በወቅቱ ለሕወሓት ወገንተኛ የሆኑ ጦማሪዎች ያልጻፈውን ጻፈ እያሉ ሥሙን ሲያጠፉ እውነቱ ምንድን ነው ልለው ነበር የሔድኩት። በኋላ በጥቂት ቀናት ንግግር ብቻ ነፍሴን በቀናነቱ አለመለማት። እስክንድር በጣም ሲመክረኝ ከነበሩ ነገሮች ውስጥ ነውጥ-አልባ (non violent) የትግል ስልት ላይ ፍፁማዊ እምነት እንዲኖረኝ እና ለምሠራቸው ሥራዎች በሙሉ ኃላፊነቱን ለመውሰድ እንድዘጋጅ ነበር። አድርጌዋለሁ/አደርገዋለሁ ብዬ አምናለሁ። ነውጥ-አልባ ፀረ-ጭቆና ትግሌ ይፋዊ የሆነበት እና ወደፊትም የሚሆንበት ምክንያት ለእርሱ ያለኝ አድናቆት እና ክብር የሚገለጽበት መንገድ ስለሆነ ነው።

አንዱዓለም አራጌንም ከዞን ዘጠኝ ባልደረቦቼ እና ሌሎችም ጋር እንጠይቀው ነበር። ስክን ያለ፣ ሃይማኖቱን አጥባቂ እና በመብቱ የማይደራደር ሰው ከገጠማችሁ – እሱ አንዷለም አራጌ ነው። አንዱዓለምን ልንጠይቀው መጀመሪያ የሔድን ግዜ፣ ስለእኛ ጠየቀንና “አዪዪ፣… ይሄ መንግሥት ያስራችኋል” አለን። ያለውም አልቀረ፣ በዓመት ከምናምኑ ታሰርን። አንዱዓለም ከታሰረ በኋላ ሁለት አስገራሚ መጽሐፎች ጽፏል። ‘ያልተሔደበት መንገድ’ እና ‘የሀገር ፍቅር ዕዳ’ የሚሉ ናቸው። መጽሐፍቱን ማንበቡ የአንዱዓለምን ሠላማዊነት እና ባለራዕይነት ማመን ለማይፈልጉት ሳይቀር ያሳምናል።

አንዱዓለም የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነው። በአንደኛው መጽሐፉ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል፣ ‘በ1998 ስታሰር [ያኔ ትዳር አልያዘም ነበር] ሳልወልድ ታሰርኩ እያልኩ ሲቆጨኝ ነበር፤ ተፈትቼ አግብቼ ከወለድኩ በኋላ ደግሞ መልሼ ስታሰር የማላሳድጋቸውን ልጆች ወልጄ እያልኩ እቆጫለሁ’ በማለት ቁጭት የማይቀር መሆኑን እና እያንዳንዱ ባለራዕይ መስዋዕትነት እንደሚከፍል ይነግረናል።

ጋዜጠኛ እስክንድርም የአንድ ልጅ አባት ነው። ጓዳው የማይጎድልበት እስክንድር ብልጭልጭ ነገር ሳያሸንፈው ያለውን ሁሉ እውነትን ለጉልቤዎች በመናገር (speaking truth to power) አሳልፎ የሰጠ ሰው ነው። እስር ቤት የተወለደው የታላቁ እስክንድር አንድያ ልጁ ናፍቆት እስክንድር እና ጋዜጠኛ ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል አሁን ሁለቱም ለስደት ተዳርገዋል።

ለአዲስ ዓመት ከግፍ እስር የተፈታው ‘የሙስሊሞች ጉዳይ’ ጋዜጣ አዘጋጁ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ስለ እስክንድር ነጋ አውርቶ አይጠግብም። ቃሊቲ አብረው በታሰሩበት ወቅት የተመለከተውን ሲነግረኝ፣ “እንደሱ ሥነ ስርዓት ያለው ሰው የለም። ሁሉን በዕቅድ ይመራል። እስር ቤት ውስጥ ስፖርት የሚሠራበት፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብበት እና እያንዳንዱን ነገር የሚያደርግበት የማይዛነፍ ሰዓት አለው። ከፅዳት ሠራተኞቹ ጋር በሳምንት ሁለቴ ቤት ያፀዳል። ከሰዎች ጋር አብሮ የበላበትን ሰሀን የሚያጥበው እሱ ብቻ ነው…” ~ ሽብርተኛ ተብሎ የ18 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት እስክንድር ነጋ።

እስክንድር ሌላ ቢዝነስ እየሠራ ወይም ተሰድዶ ‘የተደላደለ’ ኑሮ መኖር ሲችል፣ ስለእውነቱ እና እምነቱ የእኔ እና የእናንተን ዕዳ ደርቦ እየከፈለ ነው። አንዱዓለም ከዐሥር ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰተ ድርቅን አስመልክቶ ለተጎዱ ወገኖች መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ሲል ብቻውን ሠላማዊ ሰልፍ የወጣ ዜጋ ነው። በቲፎዞ መኖር አለመኖር፣ ጥቅም ቀርቶ ያላቸውን በማጣት እና ባለማጣት የማይሸበሩት እኒህ ፍፁም ሠላማዊ የትግል አውራዎች የማይገባቸውን ፍርድ ተሸክመው በወኅኒ፣ በአስቀያሚ አያያዝ ተጥለው ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት እነዚህ መሰሎቹን ንፁኃን ነፍሶች በማሰር እና በማሰቃየት የማይቀረውን ነውጥ እና መከፋፈል ሲጠራ ኖሯል። ዛሬ (ዘንድሮ) ለዚህ ሕያው ምስክር ነች።

መስከረም 3, 2009 ሁለቱ ንፁኃን ከታሰሩ እነሆ አምስት ዓመታቸው። (ምንጭ: BefeQadu Z. Hailu)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule