ሉቃ ም.14 ከቁ.15-24 “በእግዚአብሔርመንግስት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው፡፡ እርሱም ግን አንድ ሰው ታላቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙዎችን ጠራ፡፡በእራትም ሰዓት አሁን ተዘጋጅቷልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ ሁላቸውም በአንድነት ያማካኙ ጀመር ይላል፡፡” የሚገርመው የነዚህ ሰዎች ምክንያት ተራና የውሸት ምክንያት መሆኑ ነው “ፊተኛው መሬት ገዝቻለው ወጥቼ ላየው በግድ ያስፈልገኛል” አለ፡፡ ሰው መሬትን መርምሮ የሚያየው ከመግዛቱ በፊት እንጂ ከገዛ በኋላ ነው? ሁለተኛውም “አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቼአለው ልፈትናቸው እሄዳለሁ”አለ፡፡ በሬን የሚገዛ ሰው በሬውን የሚፈትነው ቀንበር መሸከም መቻሉን አለመቻሉን አይቶ ማረጋገጥ ያለበት ከመግዛቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ? በተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ላይ ታሪኩ በሰፊ ይገኛል፡፡ ምክንያተኛ ሰው ሌላው ቀርቶ እግዚአብሔር ሲጠራው … [Read more...] about “ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ”
Archives for July 2014
ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል
የአቶ ጌታቸው ረዳን የአማራ ነገድ ጋዜጠኞች እና ልሂቃኖች አማራውን በማዳከም የወያኔ መጋዝ ይዘው በግዝገዛው ሴራ ላይ እየተሳተፉ ናቸው። “ኢሳት” ጭምር። ጌታቸው ረዳ የሚለውን ጽሁፍ ሳነብ፣ ምንም እንኳ ከስብሰባው አዘጋጅ ከሞረሽ ወገኔ መግለጫ ይወጣል ብዬ ስጠብቅ እስካሁን ባላይም፣ በኢሳት ሴራ በጣም ማዘኔንና፣ የሞረሽ ወገኔን ደግሞ "እሰጥ - አገባ" ውስጥ አለመግባት የድርጅቱን በራስ መተማመን ያሳየኝ ክስተት መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ። ሞረሽ ስብሰባውን ሲጠራ በማስታወቂያው፡- በኢትዮጵያና በአማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ስላለው ጥፋት እና ጥፋቱን ለመከላከል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ማድረግ ስላለበት ተግባር ለመመካከር የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በኢትዮጵያ ታሪክ ጥልቅ እውቀት ያላቸውን ሶስት ምሁራንን ፕሮፌሰር ጌታቸው ሓይሌን፣ ዶክተር ሃይሌ ላሬቦ እና አቶ ጌታቸው ረዳን … [Read more...] about ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል
የአሸባሪነት ሕግና እኛ
የግንቦት ሰባቱ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በዚያ ኢትዮጵያዊያኑን በሚበላው ምድርና በሚበሉት አራዊት ከአካላቸው በስተቀር የሰውነት መገለጫ በሌላቸው ማሰብ የሚባል ነገር በማያውቁት ዘገምተኞች እጅ ሲታገትና በኋላም ተላልፎ ተሰጠ ሲባል ይሄንን ድንገተኛ አሳዛኝና ልብ ሠባሪ ዜና የሚገልጹትን ይዞች (ሊንኮች) እንዳየሁት ተጋርቸ (ሼር አድርጌ) በመጽሐፈ ገጼ (በፌስቡኬ) ለጠፍኩት (ፖስት አደረኩት) በማግስቱ አንድ ወዳጀ ምን ይለኛል? ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄንን ዜና ፖስት ያደረገ (የለጠፈ) አንተ ብቻ ሳትሆን አትቀርም አለኝ፡፡ አንተስ አላደረከውም? ስል ጠየኩት የለበጣ ፈገግታ እያሳየኝ “አዬ አንተ! ይሄንን ማድረግ በአሸባሪነት ሊያስከስስ እንደሚችል አታውቅም?” ሲለኝ እየቀለደ መስሎኝ ነበር በኋላ ላይ ኮስተር ብሎ “ቆይ! ምን አስበህ ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖርክ እንዴት እንዲህ … [Read more...] about የአሸባሪነት ሕግና እኛ
የረመዳን ወግ
ወቅቱ ረመዳን ነው፡፡ እነሆ ለረመዳን የሚሆን (አንድ ወግ) ልጋብዛችሁ፡፡ ኸሊፋው ዑመር ኢብን አል-ኸጣብ ዘወትር እንደሚያደርገው የነዋሪዎቹን ሁኔታ ለመታዘብ በምሽት በመዲና ጎዳዎች ላይ ይንጎራደድ ነበር፡፡ ወደ አንድ ሰፈር ሲደርስ በስካር መንፈስ የሚለፈልፍ ሰው ድምጽ ሰማ፡፡ ወደ ቤቱ ተጠግቶ በመስኮት ቢያይ ሰውዬው የወይን ጠጅ እየጠጣ ዓለሙን ሲቀጭ አገኘው፡፡ ዑመር አላስቻለውም፡፡ በመስኮት ዘሎ ገባና ሰውዬውን “አንተ ምን መስራትህ ነው?… ከሰው ብትደበቅ ከአላህ መሰወር የምትችል መሰለህ?… ወይን ጠጅ ለምንድነው የምትጠጣው?” በማለት ተቆጣው፡፡ ሰውዬው እንግዳውን ትክ ብሎ ቢያይ ዑመር ነው፡፡ በጣም ደነገጠ፡፡ ስካሩ በአንድ ጊዜ ለቀቀው፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ተረጋጋና ዑመርን እንዲህ አለው፡፡ “ኸሊፋው ልክ ነዎት! ወይን ጠጅ መጠጣቴ ሐጢአት ነው፡፡ ይሁንና እኔ አንድ … [Read more...] about የረመዳን ወግ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በተለይ በዚህኛው በርካታዎች በመሳተፋችሁና በግጥም ምላሽ በመስጠት ዝግጅቱን ላሳመራችሁ ሁሉ በድጋሚ ምስጋናችን ይድረሳችሁ - ቀጥሉበት:: የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በአፄ ሚኒሊክ - የአገዛዝ ዘመን ኤርትራ በሚገኝ - የስዊድን ሚሽን በኋላም ውጪ ሀገር - ብዙ የተማሩ በዕውቀታቸውም - ለሀገር የሰሩ በሹመት የቆዩ - ሆነው ነጋድራስ ታሪክ ያረሳቸው - እስከዛሬ ድረስ ገብረህይወት ባይከዳኝ - በሚል የጻፋችሁ ስህተት የለውም - ልክ ነው … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯
የአፍታ እፍታዎች
ያስገረሙኝና ፈገግ ያሰኙኝ የማህበራዊ ሚዲያ ‹‹ጥቅሶች›› 1. ‹‹የድሃ ልጅ ስሙ ሀብታሙ ነው›› 2. ‹‹ሰውና ድፎ በትዕዛዝ እንደፋለን›› 3. ‹‹ቁንጅና ይኑርሽ እንጂ ፀባይ በዱላ ይመጣል›› 4. ‹‹የሴት ልጅ ግርዛትና ሚስድኮል ይቁም›› 5. ‹‹ኡፍ በማለት ትንፋሽ እንጂ ብሶት አይወጣም›› 6. ‹‹ለህይወትህ ዋጋ፣ ለልጆችህ ዳቦ ስጥ!›› ሰፈር ውስጥ የሰማኋቸው አዲሶቹ የሸገር ልጆች ቃላት • ‹‹በጤ›› - በጣም ለማለት • ‹‹በኔ›› - በእናትህ ለማለት • ‹‹እሱ እኮ እምባ ነው›› - የቅርብ ተቆርቋሪ ነው ለማለት • ‹‹ጠበዘዝነው›› - በላነው ለማለት • ‹‹ዘጭ ብያለሁ›› - ጠግቤያለሁ ለማለት • ‹‹ኤም ጢ ›› - መስሚያዬ ጥጥ ነው/ አልሰማህም ለማለት ታክሲ ላይ ያነበብኳቸው፡ 1. ‹‹ሰው ብቻ ነው የምንጭነው፤ በስህተት የገባ ካለ … [Read more...] about የአፍታ እፍታዎች
አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የስደተኛው “ሲኦል ምድር” የመን እና የእኛ ስጋት …
ሰሞነኛው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታገትና ወደ ኢትዮጵያ የመተላለፍ ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል። በአረብ ሃገር የሚገኙን ጨምሮ ኢትዮጵያውያንን በመላ አለም ከአድማስ አድማስ በተቃውሞና በድጋፍ እያነቃነቀም ይገኛል። ምሽቱን በፊስ ቡክ በ Facebook ማህበራዊ ገጽ ከተንሸራሸሩት አስተያየቶችና ወቅታዊ መወያያ ርዕሶች መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታገት ሲሰማ የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋ እንደምትሰጥ ምንጩን ሳይነግረን መረጃ ያቀበለን የአውራምባ ታይምስ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ያስተላለፈው የማወያያ መጠይቅ አስገርሞ አሳዝኖኛል። ዳዊት በዚህ መጠይቁ "...አቶ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያ ፖስፖር ይዞ መቆየት የለበትም ትላላችሁ ?" በማለት ዳዊት ራሱ ለመረጃ ቅርብ እንደሆነ ባለሙያ በአለማችን ነባራዊ ሁኔታ የነጻነት ታጋዮችን ሁለንተናዊ … [Read more...] about አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የስደተኛው “ሲኦል ምድር” የመን እና የእኛ ስጋት …
“ምሁራን” በፊደሎቻችን ላይ የሚያነሣሷቸው ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
የሀገር ውስጥ ምሁራን በፊደሎቻችን ላይ ብዙ ዓይነት ቅሬታዎችንና ጥያቄዎችን ሲያነሡ ቆይተዋል አሁንም በየ ብዙኃን መገናኛው ማለትም በየነጋሪተ ወጉ(Radio) በየ ምርአየኩነቱ (Television) እና በየ መጣጥፉ በማንሣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለውጦችንም ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም እንዲመቻቸው ይመስላል የፊደሎቻችን ባለቤት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሆኑን ልቦናቸው እያወቀ እንደፈለጉ ያለከልካይ እና ጠያቂ ለውጥ ለማድረግ እንዲመቻቸው ከፊደላቱ ባለቤት ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተቃውሞ እንዳይነሣባቸው የፊደላቱን ባለቤት ለባዕድ ይሰጡታል ወይም የደቡብ ዓረቢያ ነው ብለው ይሰብካሉ፡፡ ፻ ዓመት ከሚጠጋ ጊዜ ጀምሮ ምሁራኑ በፊደሎቻችን ላይ ጥያቄ ሲያነሡ ቆይተዋል፡፡ የቀድሞዎቹ በተለየ ያነሡት የነበረ ጥያቄ እንደዛሬው መቀምር (Computer) ባልነበረበት ሰዓት የአማርኛ መጻፊያ መሣሪያ … [Read more...] about “ምሁራን” በፊደሎቻችን ላይ የሚያነሣሷቸው ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?
ተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል … [Read more...] about የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?
የየመን ኩባንያ የትምባሆ ድርጅት ከፍተኛ የአክሲዮን ባለድርሻ ሆነ
የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ውሳኔ ሰጠ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን ወስኗል፡፡ የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ … [Read more...] about የየመን ኩባንያ የትምባሆ ድርጅት ከፍተኛ የአክሲዮን ባለድርሻ ሆነ