• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የስደተኛው “ሲኦል ምድር” የመን እና የእኛ ስጋት …

July 5, 2014 11:36 pm by Editor 1 Comment

ሰሞነኛው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታገትና ወደ ኢትዮጵያ የመተላለፍ ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል። በአረብ ሃገር የሚገኙን ጨምሮ ኢትዮጵያውያንን በመላ አለም ከአድማስ አድማስ በተቃውሞና በድጋፍ እያነቃነቀም ይገኛል።

ምሽቱን በፊስ ቡክ በ Facebook ማህበራዊ ገጽ ከተንሸራሸሩት አስተያየቶችና ወቅታዊ መወያያ ርዕሶች መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታገት ሲሰማ የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋ እንደምትሰጥ ምንጩን ሳይነግረን መረጃ ያቀበለን የአውራምባ ታይምስ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ያስተላለፈው የማወያያ መጠይቅ አስገርሞ አሳዝኖኛል። ዳዊት በዚህ መጠይቁ “…አቶ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያ ፖስፖር ይዞ መቆየት የለበትም ትላላችሁ ?” በማለት ዳዊት ራሱ ለመረጃ ቅርብ እንደሆነ ባለሙያ በአለማችን ነባራዊ ሁኔታ የነጻነት ታጋዮችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያወቀ እንዳላወቀ ሆኖ በለቀቀው በሚመስለኝ መጠይቁ ሊያወያየን ከጅሏል …

ወዳጀ የአውራንባው ታይምስ ጋዜጠኛ  ዳዊት Dawit Kebede ይህን ጉዳይ ሲያነሳ በዘመነ ደርግ  “ሽፍታ ፣ ወንበዴ እና ገንጣይ! ” በሚል ስም ይወገዙ የነበሩት የወያኔ መሪዎች በሃገር ቤት ፣ እውቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ፣ የኩርዱ ነጻነት ታጋይ ኦጀላንን ጨምሮ በርካታ በአለማችን የምናውቃቸው የነጻነት ታጋዮች አንባገነን የሚሉትን መንግስት ለመጣል የሃገራቸው ፖስፖርት ይዘው እንዳልነበር ጠፍቶት አይመስለኝም። ሌላው ይቅርና በኢትዮጵያ ውስጥ የኤትራውን ጨቋኝ የኢሳያስን መንግስትን ለመጣል በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰው ቡድን መሪዎች በኤርትራ ፖስፖርት ይሆን የሚንቀሳቀሱት?  ብየ ዳዊትን እንድጠይቀውም አድርጎኛል። ይህ በዳዊት አፍንጫ ስር ያለ መረጃ ነውና ወዳጀ ዳዊት እንዲፈትሸው በማሳሰብ ዳዊት የአቶ አንዳርጋቸውን እንቅስቃሴ የማይደግፍ ከሆነ እንደ ዜጋ በግልጽ የራሱን ሃሳብ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ እንደሆነ የወንድም ምክሬን መክሬዋለሁ። በእኔ በኩል ግን ከላይ በሰጠው የወረደ ማወያያ ሃሳብ መነሻ ሚዛናዊነት መጉደል አካሄዱ ስላላማረኝም። ይህም በመሆኑ ወዳጀ ጋዜጠኛ ዳዊት ያነሳው ማወያያ ሃሳብ አላስደሰተኝም!  … ዳዊት የጀመረው ተራ ብሽሽቅ እንጅ መረጃ ቅበላ አልመሰለኝምና አዝኛለሁ! እግዚአብሔር ዳዊትንም እኛንም ይታረቀን ብየ ብዘለው ይሻለኛል:

(ከመነሻ እግረ መንገዴ ይህን ካልኩ ወደ የመን ሰሞነኛ እርምጃ እና እርምጃው ወዳስከተለው ስጋት በጨረፍታ ላምራ …

የየመን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት “ቀንደኛ” ተፈላጊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በማገትና በማስተላለፉ ረገድ ያሳየው ፍጥነት ብዙዎችን አስገርሟል። ላለፉት አስርት አመታት በየመን ምድር ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጸም ተመልካች የሆነው የየመን መንግስት የዛሬ አርምጃ ፍጥነት ብዙዎችን አስገርሟል።

ያልታደሉ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን ግፍ ከተበራከተባቸው አረብ ሃገራት መካከል የመንን የሚተካከላት የለም። ግፍ ተፈጽሞባቸው እዚህ ሳውዲ አረቢያ ያገኘኋቸው ግፉአን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመንን ምድር እንደ እንስሳ ተቆጥረው ያዩትን የስደትና እንግልትና እገታ ሲገልጹት “የሲኦል ምድር!” ማለት ይቀናቸዋል።  ስደተኛ ወገኖቻችን ዛሬ ድረስ በየመን ከተማ ፣ጉራንጉሮችና በየበርሃው የከፋ በደል እየተፈጸመባቸው ለመሆኑ የአደባበይ ሚስጥር በመሆኑ ዋቢ የሚያሻው አይደለም። የኢህአዴግ መንግስት  በኢኮኖሚ ሰደተኞች በሆኑ ዜጎቹ ላይ በየመን ምድር የሚፈጸመውን ግፍ ተቃውሞ አርባና ያለው እርምጃ መውሰድ ባለመቻሉ እስካሁን ያለው የስደተኞች ይዞታ አሳሳቢ እንደሆነ ቀጥሏል ።  በግዛት መሬቱ ላይ በዜጎቹ ግፍ ሲፈጸምብን መገደብ የተሳነው የየመን ስንኩል መንግስትም ቢሆን አለም አቀፍ ህግጋትን አክብሮ የወሰደው ቅንጣት እርምጃ ካለማሳየቱ በተዛማጅ የዛሬ አቶ አንዳርጋቸውን የማስረከብ እርምጃ ለኢትዮጵያ ሰላም በማሰብ ሳይሆን የፖለቲካ ጥቅምን ለማጋበስ የወሰደው እርምጃ ነው በሚል ብዙዎችን ቂም አስቋጥሯል።

በየመን በሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በግፍ በየባህሩና በርሃው ወድቀው ሲቀሩ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች የዜጎቻቸውን መብት ሲያስከብሩ አይተን ለማናውቅ ዜጎች የመንና ኢትዮጵያ  “አሸባሪ! ” ያሏቸውን ግለሰብ በታገቱበት ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሃገር ቤት ማስተላለፋቸው ዜና መሰማቱ ብዙዎቻችን አስደምሟል። ይህ ያልተጠበቀ ክስተትና በየመን የተወሰደ የማስተላለፍ እርምጃን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በየአቅጣጫው የተለያየ አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው። በርካታ ነዋሪዎች  ” አቶ  አንዳርጋቸውንና የሚመሩትን ድርጅት ስም ማንሳት በወንጀለኝነት ያስቀጣል ” የሚለውን ማስጠንቀቂያ እየጣሱ መንግስት “በአሸባሪነት ” ስለፈረጃቸው የቀድሞ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ የመጣው ይምጣ በሚል አንድምታ ድፍረት በተቀላቀለበት መንገድ ዋንኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

በኢትዮጵያ መንግስት  “ነውጠኛ አሸባሪ” የተፈረጁት እና በኢህአዴግ ላይ ጦር የሰበቀው የግንቦት 7 ድርጅት “አራጊ ፈጣሪ ናቸው” የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን “ለዲሞክራሲና ነጻነታቸው የተጉ፣ ብርቱ አርበኛና ታጋይ !” እያለ ከንፈሩን የሚጥላቸው እና የሚያደንቋቸው ብዙ ነዋሪዎች አጋጥመውኛል። የመንግስት ደጋፊዎች በበኩላቸው “ትልቁ አሳ ወጥመድ ውስጥ ገብቷል!” ብለው ያምናሉና ጮቤ ከመርገጥ ባለፈ በትምክህት “እኛ እንዲህ ነን!” በሚል በኩራት ሲናገሩ አድምጫለሁ! በማህበራዊ ድረ ገጾችና በሰሚ ሰሚ ወሬው ደርሶት አስተያየት ላለመስጠት የሚሸሸው ነዋሪ ብዙ ቢሆንም በሆነው ሁሉ ያደረበትን ስጋት ከመግለጽ የተቆጠበ ግን የለም። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታገትና ለኢትዮጵያ መንግስት መተላለፍ ከተደሰቱት ውጭ ያለው ብዙ ነዋሪ የበቀል እርምጃ እንደሚፈጽሚ ሲዝቱ ተስተውሏል።

“ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትን አላስከበራችሁም !” በሚሉ ተቃዋሚ ቡድኖችና “በሁለት አስርት አመታት ዲሞክራሲን አስፍኛለሁ፣ ሰብአዊ መብት አስከብሬያለሁ!” በሚለው ኢህአዴግ መካከል አመታት የዘለቀው መጓተት ባመጣው ጣጣ በርካቶች “ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ !” በሚል ዘብጥያ ወርደዋል። አቶ አንዳረጋቸውም ቢሆን በኢህአዲግ ላይ ጠንስሰዋል በተባለው መፈንቅለ መንግስት በሌሉበት የሞት ፍርድ የተበየነባቸው መሆኑ ሲታወስ “ተይዘው ወደ ኢህአዲግ እጅ  ተላልፈዋል !” የመባሉ ዜና በቀል አስቋጥሮ ፣ በዛቻና ፉከራው ታጅቦ ዳግም በፖለቲካ ትርምስ ፍጥጫ እንዳይከታትና ኢትዮጵያን ወደ ሌላ የመጠፋፋት አዙሪት እና ብጥብጥ እንዳይዶላት በነዋሪው ላይ ታይቶ የማይታወቅ ስጋት አጭሯል።

አዎ !  አረብ ሃገራት እንዲህ ናቸው ፣ በአረብ ሃገር  ያለን ስደተኞች መከራ ብዙ ነው 🙁 እኔም የሃገሬ ህዝብ በነቂስ ስለሚነጋገርበት ሰሞነኛ አጀንዳ ቢያገባኝ ይህችን ታክል መረጃ አቀብል ዘንድ ነፍሴ ፈቅዳለች ። ከዚህ ባለፈ መጻፍና መናገር ግን አቅሙ የለኝም ልበል ይሆን?

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Eyosias Mesfin Tesfaye says

    July 8, 2014 09:01 am at 9:01 am

    Bro there are lots of children who had askaris grandpas
    In Ethiopia that betrayal goes through there veins it’s
    a bad heredity Dawit can’t help it bro I am glad
    Time for askaris children is over soon
    Thanks a million Nebeyu

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule