
የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ውሳኔ ሰጠ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን ወስኗል፡፡
የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡
ሼባ ኢንቨስትመንት እንዲገዛ ለተፈቀደለት 38 በመቶ አክሲዮን 1.3 ቢሊዮን ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ ኩባንያው ይህንኑ ገንዘብ እንደከፈለ የስም ዝውውር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
ብዙም ባልተመለመደ ሁኔታ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ሽያጭ ላይ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት የተቸገረው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያው ድርጅቱ በሲጋራ ላይ ብቸኛ መብት (ሞኖፖሊ ራይት) ያለው በመሆኑ፣ ይህ የብቸኝነት መብት የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ በሚይዝበት ወቅት ምን መሆን አለበት? የሚለው ጉዳይ ላይ አቋም መያዝ ባለመቻሉ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ የታክስ ዓይነቶች በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት የሚያስገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ትርፋማ ከሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚያደርግ ነው የሚለው ጉዳይ ቦርዱ በአክሲዮኑ ሽያጭ ላይ ለመወሰን እንዲቸገር ማድረጉ ነው፡፡
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የፕራይቬታይዜሽን ቦርድ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቅጣጫ በግልጽ ባለመረዳቱ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንዲሰጠው መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሁለቱም ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው የአክሲዮን ሽያጩ እንዲከናወን በማዘዙ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተሰበሰበው የፕራይቬይታዜሽን ቦርድ የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆን የሚያስችለውን ውሳኔ እንዲወስን ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች የትምባሆ ልማት የሚያካሂድባቸው የእርሻ መሬቶች ባለቤት ነው፡፡ የድርጅቱ መሥርያ ቤት ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ አመቺ አይደለም በሚል መሥርያ ቤቱ ከዚህ ቦታ ተነስቶ ወደ አቃቂ አካባቢ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ድርጅቱ ቃሊቲ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ የሚያካሂደውን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፣ ለበርካታ ዓመታት ከነበረበት ቦታ ይነሳል ተብሏል፡፡ (ምንጭ፡ ሪፖርተር፤ ሰኔ22፤2006/June 29,2014 – ተመሳሳይ ዜና Capital በሰኔ16፣2006/June 23,2014 ዕትሙ ዘግቧል፡፡ ፎቶውንም ያገኘነው ከዚያው ነው)
Is it at an expense of Ato Andargachew Tsegie who is detained in yemen?
ትምቦሐ ባፍንጫ ይወስድ የነበር
ሰው መብላት ጀመረ መፈብረክ ሲጀምር
ወደ ሳንባ ዘልቆ ሳያንሰው ማፈኑ
ሙሉ ሰው ፈለገ ከየመን ባሁኑ
ትምባሆ በደልከን ሆዳችንም ጨሠ
ኢትይጵያዊው ሲያዝን ጨካኝ ልቡ ራሠ
ድሮም ክብር የለህ ግማትሕ ክርፋቱ
የበለጠ ረከሥክ ተጠላህ በስንቱ
ወያኔ በክፋት በትቢቱ ማግጦ
ወገን አንዳርጋቸው ባንተ ተለውጦ
ለሥቃይ ሲዳረግ ላገር ተቆርቁሮ
ትማባሆ ገማሐኝ ከየመን ጋር አብሮ›
ትምባሆ ገማሀኝ ባያሌው ከረፋህ
መቀመቅም ውረድ አፋኞችን ይዘህ
እነሱም አፋኞች አንተም ያየር በካይ
ግም ለግም ነውና በተለምዶ ሲታይ
ሀብትነትህ ይውደም መናኛ ሆነህ ቅር
ጀግናን አስቀያሪ በተዘረፈ ብር
ወነጀለኛ ሲሆን ለፍትሕ ተምዋጋች
አንዳርጋቸው ሁሌም ጸናኢ ላገሩ ምዋች
መሆኑን ጠንቅቀን ስለምናውቅው እኛ
እፈር አንተ ርካሽ የነገር መናኛ
ሽብርተኛስ አንተ አፋኝ ሁለመና
በወግ አትመዘን አይስፍሩህ በቁና
ጉቦ መደረግህ ወግ መሥሎህ ከሆነ
የስጠህም ይፈር ይሕንን ካመነ
ጤናማ ላይገኝ ቀይ ባሕር ተሻግሮ
ትምባሆ በቃህኝ ከየመን አብሮ
Ahun yehen k Anadaregachwe gare men Agengnwe aye weche Ager yal swe endzhe Ayente hebrtseb nwe btame yasazenal Anadaregachwe yeteyazwe Ahune deru ego yeteshetwe bfete