ያስገረሙኝና ፈገግ ያሰኙኝ የማህበራዊ ሚዲያ ‹‹ጥቅሶች››
1. ‹‹የድሃ ልጅ ስሙ ሀብታሙ ነው››
2. ‹‹ሰውና ድፎ በትዕዛዝ እንደፋለን››
3. ‹‹ቁንጅና ይኑርሽ እንጂ ፀባይ በዱላ ይመጣል››
4. ‹‹የሴት ልጅ ግርዛትና ሚስድኮል ይቁም››
5. ‹‹ኡፍ በማለት ትንፋሽ እንጂ ብሶት አይወጣም››
6. ‹‹ለህይወትህ ዋጋ፣ ለልጆችህ ዳቦ ስጥ!››
ሰፈር ውስጥ የሰማኋቸው አዲሶቹ የሸገር ልጆች ቃላት
• ‹‹በጤ›› – በጣም ለማለት
• ‹‹በኔ›› – በእናትህ ለማለት
• ‹‹እሱ እኮ እምባ ነው›› – የቅርብ ተቆርቋሪ ነው ለማለት
• ‹‹ጠበዘዝነው›› – በላነው ለማለት
• ‹‹ዘጭ ብያለሁ›› – ጠግቤያለሁ ለማለት
• ‹‹ኤም ጢ ›› – መስሚያዬ ጥጥ ነው/ አልሰማህም ለማለት
ታክሲ ላይ ያነበብኳቸው፡
1. ‹‹ሰው ብቻ ነው የምንጭነው፤ በስህተት የገባ ካለ ይውረድ››
2. ‹‹ሰው አካውንት ይከፍታል፤ አንዳንዱ አፉን ይከፍታል››
3. ‹‹ጤነኛ ካልሆኑ መውረጃዎ ደርሷል››
4. ‹‹ባለጌና ዋንጫ ከወደ አፉ ይሰፋል››
5. ‹‹ሾፌሩን መጥበስ ክልክል ነው – በነገር!››
6. ‹‹መስኮት በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን››
7. ‹‹በጭነት መኪና መጥታችሁ እዚህ ትቀናጣላችሁ››
8. ‹‹ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ ቅሬታ፣ ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል፡፡››
9. ‹‹ለክቡራን ሌቦች ሂሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራ መጀመር አይቻልም፤ የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል››
10. ‹‹ኑሯችሁ ሳይሞላ ‹ታክሲው አልሞላም?› ትላላችሁ፡፡››
የዓባይ ዳር ጨዋታዎች – በደመቀ ከበደ by Demeke Kebede
Leave a Reply