ምነው በቀደም ለት እንቢልታ ሲነፋ ከበሮ ሲደለቅ፣ ከዘመናት ግዞት ነፃ የወጣንበት፣ ብለህኝ አልነበር አፍሪካ ነፃ ናት? "'አፍሪካ . . . ሀገራችን አፍሪካ የኛ ናት አፍሪካ አፍሪካ. . ." ተብሎ ሲዘመር የጥቁሮች ነፃነት? ታዲያ ዛሬ ለሊት፣. . . የሰማሁት ዋይታ ያዳመጥኩት ጩህት፣ ሲያከብሩ እዳትለኝ የበአሉን ማግስት? ዋሽተህኛል እንዴ . . . ? ትርጉሙን አዛብተህ? . . . ሆኖ እንዳይሆን ብቻ፣ ነፃ መሆን ማለት ካልሆኑ አቻ ላቻ ፣ ለወሬ ማድመቂያ ዳንኪራ መርገጫ፣ ነፃነት ነፃነት እያሉ ማፋጫ፣ ድቤ መደለቂያ በባዶ መንጫጫ ? እኔን ነፃ ያርገኝ. . . በዚች መሬታችን በምንኖርባት፣ የጥቁር ደም አጥንት በግፍ ባለቀባት፣ ነፃነት አግኝቶ ደምቆ `ሚኖርባት ? የሰላምን አየር ተንፍሶ `ሚድርባት ነጭ ነው ወይ ጥቁር . . . … [Read more...] about ቅኝ ግዛት!