
ምነው በቀደም ለት
እንቢልታ ሲነፋ ከበሮ ሲደለቅ፣
ከዘመናት ግዞት ነፃ የወጣንበት፣
ብለህኝ አልነበር አፍሪካ ነፃ ናት?
“‘አፍሪካ . . . ሀገራችን
አፍሪካ የኛ ናት
አፍሪካ አፍሪካ. . .”
ተብሎ ሲዘመር የጥቁሮች ነፃነት?
ታዲያ ዛሬ ለሊት፣. . .
የሰማሁት ዋይታ
ያዳመጥኩት ጩህት፣
ሲያከብሩ እዳትለኝ
የበአሉን ማግስት?
ዋሽተህኛል እንዴ . . . ?
ትርጉሙን አዛብተህ?
. . . ሆኖ እንዳይሆን ብቻ፣
ነፃ መሆን ማለት ካልሆኑ አቻ ላቻ ፣
ለወሬ ማድመቂያ ዳንኪራ መርገጫ፣
ነፃነት ነፃነት እያሉ ማፋጫ፣
ድቤ መደለቂያ በባዶ መንጫጫ ?
እኔን ነፃ ያርገኝ. . .
በዚች መሬታችን በምንኖርባት፣
የጥቁር ደም አጥንት በግፍ ባለቀባት፣
ነፃነት አግኝቶ ደምቆ `ሚኖርባት ?
የሰላምን አየር ተንፍሶ `ሚድርባት
ነጭ ነው ወይ ጥቁር . . . ?
“ጥቁር” እዳትለኝ!
. . . እቀየምሀለሁ
አገሬ ላይ ቆሜ ባሪያ ሆኜ ሳለሁ።
(ምንጭ: የብሌን ከበደ ፌስቡክ 2/7/2014
************************
ይህ ቅኝ ግዛት ማለት የነጭ ልማድ ነበር
የራስን አስንቆ የሌላውን ማክበር
ቋንቋን አሳንሶ ሰንደቅን አዋርዶ
ነጻነት ሲታሰብ ጅግና እንደበግ ታርዶ
እንደሻማ ቀልጠው እረ ስንቱ ነዶ…..
——–_______ወይ ነዶ!?
ዘመን ተቀይሮ የነበረው ጠፍቶ
ነጭ ደላላ ሆኖ ጥቁር በጥቁር ተገዝቶ
ዲሞክራሲ እያሉ.. ማጥ ጨምረው እያስዳከሩት
ስሌት ነው.. እያሉ የሚደመር የለ ተምሮ ማጣፋት
ዕድገት ነው.. እያሉ ተበድሮ ገዝቶ እየሸጡበት
ልማት ነው.. እያሉ እያፈናቀሉ እያመሳቀሉት
ቁጠባ.. እያሉ እያባካኑ እያመከኑት
ነፃነት.. እያሉ በቁሙ ሸጠው እያሰደዱት
እራስ ገዝ.. እያሉ ከልለው ሆኖ የቁም ከብት
ከባሪያ ያነሰ…ከነጭም ከጥቁር እዚያው በራሱ ቤት
ምን ነካው? ትውልዱ ወኔ አልባ የሌለው ሐሞት!
ምነው እነኛ አርበኖች ቀና ብለው ባዩት
ሀገር ትውልድና ሰንደቅ ሞተ ሞተውበት!
********************
በለው!