ከግንቦት 7 የተሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት … [Read more...] about የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ታገቱ
Archives for June 2014
“የድሮ ስርዓት ናፋቂ”?
ይህ ቃለመጠይቅ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ተስፋዬ ጋር (19 April, 2014) ካደረጉት ቃለምልልስ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው፡፡ አዲስ አድማስ፤ ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት በሬዲዮ ፋና ላይ በነፃው ፕሬስ ዙሪያ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ እርስዎም በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በውይይቱ ላይ “ዶ/ር ዳኛቸው ስሜታዊ ሆነው ነበር” የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” የሚል ትችትም ተሰንዝሮቦታል፡፡ የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው? ዶ/ር ዳኛቸው፤ የስሜታዊነቱን ነገር ያመጡት እንኳን እነሱ ናቸው፡፡ ስድብና ዘለፋውን በመጀመር እነሱ ይቀድማሉ፡፡ “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” ለሚለው በእውነቱ በናፍቆት ደረጃ ፍትህ ናፋቂ ነኝ፡፡ ዴሞክራሲና የህዝባችንን ነፃነት ናፋቂ ነኝ፡፡ የዱሮ ሥርዓት ናፋቂ የሚሉኝ “አሁን ያለንበት ወርቃማው ጊዜ ነው” የሚሉ ዜጎች … [Read more...] about “የድሮ ስርዓት ናፋቂ”?
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አምስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ለሀገር ለወገን - ውለታ የሰራ ስሙ ለዘለዓለም - ይኖራል ሲጠራ ነገር ግን ታሪኩን - ያረገውን በጎ አንባቢው አለበት - መረዳት ፈልጎ እኛ ለማስታወስ - ይሄንን አድርገን ለማቅረብ ችለናል - መላኩ በያንን እኚህ ስመ ጥሩ - ኢትዮጵያዊ ዶክቶር ሙሉ እድሜአቸውን - ደክመዋል ለሀገር። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፮
አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራከሩ
"ልንመሰገንበት በሚገባ ሥራ ወንጀለኛ መባላችን ያሳዝናል" አቶ መላኩ ፈንታ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከር ድርጊቱን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛም እንዳልሆኑ ለፍርድ ቤት ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. አስረዱ፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሦስት የክስ መዝገቦች ክስ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ አንደኛውን የክስ መዝገብ እንዲያሻሽል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ያዘዘው ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ ላይ ይግባኝ በማለቱና በማሳገዱ ተጠርጣሪዎቹ በሁለቱ የክስ መዝገቦች ላይ ብቻ የእምነት … [Read more...] about አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራከሩ
ጊዜ የማይሠጥ ሀገራዊ ጥሪ አለብን!
ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ የሰየመው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት (ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት)፤ ሀገራችንን ዕለት ከዕለት ወደ ባሰ አዘቅት እንድትገባ እየጎተታት ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው የሀገራችንን ሕልውና በንጥልጥል ላይ እንዲቀመጥ ሌት ከቀን እየጣረ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ በመቆም፤ በተለያዩ ድርጅቶች ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተዋደቁ ያሉ ታጋዮች አሉ። ይህ በዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል እየተደረገ ያለው ግብግብ፤ ለረጅም ዘመን እንዳለ ሆኖ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊው መንግሥት የፈለገውን እያደረገ ያለበትና፤ በታጋዩ ወገን ያለው ክፍል ደግሞ ላለፉት ፳ ፫ ዓመታት ባለበት የሚረግጥበት ሁኔታ አልተለወጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት … [Read more...] about ጊዜ የማይሠጥ ሀገራዊ ጥሪ አለብን!
የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?
ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ … [Read more...] about የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?
የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ
ይሞላ ብዪ ስኳትን፣ ህልሜ እልም እያለ ቢፈትነኝ ለህሊናየ አድር ብዪ ስማስን፣ ድካሙ ቢሸበርክኝ ተስፋ አልቆርጥም ባልኩ በተጋሁ፣ ህመሙ ቢደቁሰኝ ብላቴን ጌታ ታወሰኝ፣ ጸጋየ ህመሙ ዘልቆ ወጋኝ የጸጋየ ህመሙን ታመምኩ መላ ቅጡን አስጠፋኝ። ውስጤ ቢደማ ቢታወክ፣ የጸጋየ ሮሮ በአይነ ህሊናየ መጣብኝ የመጨረሻው እስትንፋስ ቃሉ፣ ሎሬት ህመሙ አመመኝ "እኔ ለእኔ ኑሬ አላውቅም " ብሎ ያለን የስንብት ጸጸት ቃሉን አዘከረኝ፣ ....... ........ ....... ......... ........ ...... የጸጋየ ጸጸት ... "የማይሰማ ወጨት ጥጄ - እፍ ስል የከሰመ ፍም፣ ውርዴም ይፈወሳል ብዬ - የሰው እከክ ስዘመዝም፣ በሰው ቁስል መቁሰል በቀር - እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡ የማይነጋ ህልም ሳልም - የዘመን ደዌ ሳስታምም፣ የማያድግ ችግኝ … [Read more...] about የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ
እውነት ኦሮሚያ የሚለው ስም በታሪክም በተረትም የማይታወቅ የህልም ዓለም ስያሜ ነው?
በትምህርትም ሆነ በሀብት ቀና የሚሉ የኦሮሞ ሕዝብ ልጆችን በተለያዩ የፀረ- መንግሥት እንቅስቃሴዎች በመፈረጅ ሲያሳስሩና ሲያስገድሉ የኖሩ የኦሮሞ ፍራቻ-ጥላቻ በሽታ ህመምተኞች በሚያከሂዱት ፀረ- ኦሮሞ ፐሮፓጋንዳ “ኦሮሚያ የህልም ዓለም ስያሜ ነው፤እስላሞችና ኦሮሞዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቁ፤ ስለኦሮሞ ሕዝብ ጨካኝነት የአገር ውስጥ የታሪክ ጸሐፊዎችና ተመራማሪዎች፤ እንዲሁም የውጭ አገሮች ጸሐፍት መስክረዋል፤ “ጋዳ/ገዳ” የማፊያ ሥርዓት ነው፤ምኒልክና ወታደሮቻቸው ክርስትያኖች ስለነበሩ የአርሲን ሕዝብ ጡትና እጅ አልቆረጡም፤ ይህንን የሚፈጽሙት አረመኔዎቹ ናቸው፤የኦሮሞን አመጽ ይመሩ የነበሩት የወለጋ ፕሮቴስታንቶች ናቸው፤ዛሬ ኢትዮጵያ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አገሩ አይደለችም፤ወንድ ልጅን መስለብ የኦሮሞ ባህል ነው፤ኦሮሞ እረኛ ነው፤ ወዘተ… የሚሉ ከህሙም ህሊናዎች … [Read more...] about እውነት ኦሮሚያ የሚለው ስም በታሪክም በተረትም የማይታወቅ የህልም ዓለም ስያሜ ነው?
እውን ሐበሻና ፊደሎቹ ከደቡብ ዓረብያ ፈልሰው የገቡ መጻእያን ወይም ውሑዳን ናቸውን?
የሥነ ልሳን ወይም የሥነ ቋንቋ linguistics ተመራማሪዎች ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈለሰፉ የሚሏቸው ከፊሎቹ ሱመራዊያን አሁን ኢራን በሚባለው አካባቢ እንደሆነ ሲናገሩ ከፊሎቹ ደግሞ በግብጽና በሜሶፖታሚያ እንደሆነ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን እውነቱ ይህ እንዳልሆነ በሌላ ጊዜ በሚገባ እናየዋለን፡፡ እነኚህ ምሁራን የእኛን የግዕዝ ወይም የአማርኛ ፊደላትን ከደቡብ ዓረቢያ ባሕር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ በገቡ አፍሮ ዓረቦች ወይም ኢትዮ ሴማዊያን አማካኝነት ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ሃያ ዘጠኝ መሠረታዊ ፊደላትን ይዘው ገቡ በማለት ይናገራሉ፡፡ እንደመረጃ አድርገው ከሚያቀርቧቸውም ውስጥ አንድ ሁለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሴማዊ ቋንቋ የሚናገሩ ብሔረሰቦች መኖራቸውና እነኚሁ ብሔረሰቦች ደግሞ በመልክ ከሌላው አፍሪካዊ የተለዩ ስለሆኑ መጤዎች እንጂ ነባር አይደሉም ይላሉ፡፡ ከዚህ … [Read more...] about እውን ሐበሻና ፊደሎቹ ከደቡብ ዓረብያ ፈልሰው የገቡ መጻእያን ወይም ውሑዳን ናቸውን?
ሕገወጥ ደም ሻጮች የከሰሩበት
ከአንድ ዓመት በፊት አንድ ህመምተኛ ለሚደረግለት ህክምና ደም የሚያስፈልገው ከሆነ፣ ቤተሰብ አሊያም ወዳጅ ዘመድ ምትክ ደም ሰጥቶለትና የሚያስፈልገው የደም አይነት ከደም ባንክ ወጥቶለት ይታከም ነበር፡፡ ይህ አሠራር ግን በርካቶች የሚያስፈልጋቸውን ደም በቀላሉ እንዳያገኙ የሚያደርግ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ቤተሰብ አሊያም የታካሚው የቅርብ ወዳጆችም ‹‹ደም ለግሱና ደማችሁ ተተክቶ ለታካሚው ሌላ ደም ይሰጠው›› የሚለውን ሐሳብ ሲሰሙ ሃሳቡን ይሸሻሉ፣ ከልገሳው ያፈገፍጋሉ እንዲሁም ይፈራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ደማቸው ተወስዶ እምብዛም ጥቅም ላይ መዋል የማይችል ግለሰቦች በደላሎች አማካይነት በሽያጭ ደም ይለግሳሉ፡፡ ደም ባንክ የእነዚህን ሰዎች ደም በምትክ ወስዶ ከባንኩ ለታካሚዎች ደም ቢሰጥም፣ በሕገወጥ መንገድ ተሸጦ ገቢ የተደረገው ደም ከሞላ ጎደል ይወገድ እንደነበር ባንኩ … [Read more...] about ሕገወጥ ደም ሻጮች የከሰሩበት