
የሥነ ልሳን ወይም የሥነ ቋንቋ linguistics ተመራማሪዎች ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈለሰፉ የሚሏቸው ከፊሎቹ ሱመራዊያን አሁን ኢራን በሚባለው አካባቢ እንደሆነ ሲናገሩ ከፊሎቹ ደግሞ በግብጽና በሜሶፖታሚያ እንደሆነ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን እውነቱ ይህ እንዳልሆነ በሌላ ጊዜ በሚገባ እናየዋለን፡፡ እነኚህ ምሁራን የእኛን የግዕዝ ወይም የአማርኛ ፊደላትን ከደቡብ ዓረቢያ ባሕር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ በገቡ አፍሮ ዓረቦች ወይም ኢትዮ ሴማዊያን አማካኝነት ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ሃያ ዘጠኝ መሠረታዊ ፊደላትን ይዘው ገቡ በማለት ይናገራሉ፡፡
እንደመረጃ አድርገው ከሚያቀርቧቸውም ውስጥ አንድ ሁለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሴማዊ ቋንቋ የሚናገሩ ብሔረሰቦች መኖራቸውና እነኚሁ ብሔረሰቦች ደግሞ በመልክ ከሌላው አፍሪካዊ የተለዩ ስለሆኑ መጤዎች እንጂ ነባር አይደሉም ይላሉ፡፡ ከዚህ የተሳሳተ ድምዳሜ የሚያደርሳቸው ደግሞ መስፈርት አድርገው የያዙት የገዛ አስተሳሰባቸው ነው፡፡ እንደነሱ እምነት ሴማዊ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ሁሉ የግድ ከመካከለኛው ምሥራቅ መፍለስ አለበት፡፡ ልብ ቢሉ ግን ኩሻዊውም ራሱ ከየት ፈለሰና ? ምክንያቱም ሴምም ካምና ልጁ ኩሽም ያፌትም የአንድ ሰው የኖኅ ልጆች ናቸውና፡፡ በአንድ ቋንቋ ይግባቡ የነበሩ ቤተሰቦች ናቸውና፡፡ ዘፍ. 0.1 – V1
ስለዚህ በአንድም በሌላም ምክንያት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መፍለስ ግድ ሳይል ሴማዊም ሆነ ኩሻዊ ሌላም የቋንቋ ቤተሰብ በነሱ ግምትና እምነት በማይጠብቁት ቦታ ወይም በተለያዩ ስፍራዎች በነባር ሕዝብ ዘንድ የመነገር አጋጣሚ ይኖራል ማለት ነው፡፡ ኩሻዊ ቋንቋ እስያ ውስጥ እንዳለ ሁሉ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ መልካቸው አፍሪካዊ አይደሉም አፍሮ ዓረቦች ናቸው ለሚሉት ደግሞ አንድም እንዲህ የሚሉበት ምክንያት ሴማዊ ቋንቋ በመናገራችንም ነውና መልካቸው ከአፍሪካዊያን የተለየ ሁሉ ከደቡብ ዓረቢያ የግድ የፈለሰ መሆን አለበት ማለታቸው የተሳሳተ መሆኑን የሚያረጋግጠው አገውኛና ሌሎች በጎንደርና በጎጃም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍልም ያሉ ኩሻዊ ቋንቋ የሚናገሩትስ ? ነገር ግን እነሱ ከደቡብ ዓረቢያን ፈልሰው የገቡ ሕዝቦች ናቸው ከሚሏቸው ጋር ምንም ዓይነት የመልክ ለውጥ የሌለባቸው ማለት ነው ይሄንን እንዴት ሆኖ ሊሉ ይሆን ? ምክንያቱም ኩሻዊ ቋንቋ የነባር ሕዝብ ቋንቋ ነው ይላሉና፡፡
በመሆኑም የእነኚህ የዓለም አቀፍ ምሁራን መስፈርት እና ፍረጃ ጠለቅ እና ሰፋ ያለ መሆኑ የሚያጠራጥር ከግላዊና ቡድናዊ ፍላጎትና አመለካከት የጸዳ አቋምና መስፈርት እንዳልሆነ ይታያል፡፡ ለምሳሌ አማርኛን የወሰድን እንደሆነ ግእዝ ውስጥ የሌሉ ሌሎች ሴማዊያንም ያልነበራቸውን ከጊዜ በኋላ ከእሱ የወረሷቸውን እነ ሸ፣ ቸ፣ ጨ፣ ኘ፣ ጀ፣ አምስት የኩሽ የድምፅ ቤቶች አሉት፡፡ በተጨማሪም ከሴማዊያኑም ከኩሻዊያኑም የሌለ የራሱ ብቻ የሆነ “ዠ” የሚባል የድምፅ ቤትም አለውና አማርኛን አፍን ሞልቶ ሴማዊ ማለት አይቻልም ኩሻዊ ማለትም እንዲሁ፡፡
ከጥቂቶቹ በስተቀር ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ የእኛ ምሁራንም ከላይ የገለጽኩትን የባዕዳኑን ትንታኔ አምነው በመቀበል እነሱም ሲያናፍሱት ይስተዋላሉ፡፡ እንደእነሱ አባባል ግዕዝ ባሕር ተሻግረው የገቡት “አፍሮ ዓረቦች” ወይም “ኢትዮ ሴማዊያን” እና ነባሩ የኩሽ ነገድ ሕዝብ በመዳቀል የፈጠሩት ቋንቋ ነው በማለት ይናገራሉ፡፡ የሀገር ውስጥ ምሁራን ፊደሎቻችንን የአማርኛ ፊደላት መባሉን አይስማሙም እንደእነሱ እምነት “ፊደላቱ የግዕዝ እንጂ የአማርኛ አይደሉም አማርኛ ከግዕዝ ተውሶ ነው” በማለት ግራ የተጋባና የተምታታ እርስ በእርሱ የሚጋጭ እምነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ እንዲህ ማለቴ እነኚህ ምሁራን የግዕዝ ቋንቋ ባሕር ተሻግረው የገቡት “ኢትዮ ሴማዊያንና” ከነባሩ የኩሽ ነገድ ጋር በመዳቀል የፈጠሩት ቋንቋ ነው ብለው ካመኑና ሃያ ዘጠኙ መሠረታዊ ፊደላቱን ባሕር ተሻግረው ይዘውት የገቡት የኢትዮ ሴማዊያኑ ከሆኑ ፊደላቱ የአማርኛ እንጂ የግዕዝ አይደለም ማለታቸው እንደሆነ ልብ አላሉትም፡፡ ምክንያቱም በግልጽ እንደሚታወቀው አማርኛ ከኢትዮ ሴማዊያኑ ቋንቋዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛውም ነውና፡፡
በመሆኑም ግዕዝ ባሕር ተሻግረው የገቡት ኢትዮ ሴማዊያንና ነባሩ የኩሽ ነገድ በመዳቀል የፈጠሩት ቋንቋ ነው ብለው ካመኑ ፊደላቱ የአማርኛ መሆኑንም ሳያወላውሉ ማመን ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡ እነአለቃ ታዬ፣ እነተክለጻድቅ መኩሪያ፣ እነሀብተማርያም ማርቆስ፣ የመሳሰሉት ምሁራንም ቀዳማዊ ክብረ ነገሥትን፣ የአክሱም ነገሥታትን ስሞችን፣ በአክሱም ሰዎች ዘንድ ያሉ ትውፊታዊ መረጃዎችን እና የውጪ ምሁራን የጻፏቸውን መጻሕፍት ዋቢ በማድረግ አማርኛ ቋንቋን ቅ.ል.ክ. አንድ ሺህ ዓመታት በፊት ይነገር የነበረ ቋንቋ መሆኑን ይመሰክራሉ፡፡ በመሆኑም የአማርኛ የፊደል ገበታ የሚለው ሥያሜ የሚቆረቁራቸው ሥያሜ ሊሆን አይገባም ማለት ነው፡፡ እነኚህ ምሁራን አፍሮ ዓረብ የሚለውን ቃል እና ሳባዊያን የሚለውን ቃል እያቀያየሩ ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ፡፡ እንደእነርሱ ግምት ንግሥተ ሳባ የኢትዮጵያ ንግሥት ሳትሆን የደቡብ ዓረብ ወይም በአሁኑ አጠራር የመን ተብሎ የሚታወቀው አካባቢ ንግሥት ናት ብለው ያምናሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማለትም ሳባ ኢትዮጵያዊት መሆኗን የሚያረጋግጡ ከበቂ በላይ መረጃ አለንና ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡
የአገራችን ምሁራንም ይህን ብለው ማመናቸው አሳዘነን እንጂ የባዕድ ምሁራንስ ከዘረኝነት እና ከቅናት የተነሣ የኢትዮጵያ የሆነን ነገር ሁሉ አሌ ማለትን ወይም ማስተባበልን ጉዳዬ ብለው ከያዙት ከራርመዋል፡፡ ሳባን ብቻ አይደለም፡፡ እንደእነሱ እምነት የጎንደር አብያተ መንግሥታትን፣ የቅዱስ ላሊበላን ውብና ድንቅ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን፣ የአክሱም ሐውልትን የኢትዮጵያውያን ሥራዎች ሳይሆኑ የሌላ አገር ሰዎች ሥራዎች ናቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ የዜማው ሊቅ፣ ዘርዓያዕቆብ ፈላስፋውን፣ አሁን ደግሞ በቅርቡ ጃንሆይን ወይም ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴን በአጠቃላይ ዋኖቻችንን ኢትዮጵያውያን እንዳልሆኑ ይናገራሉ፡፡ ትንሽ ከቆዩ ደግሞ እነአበበ ቢቂላ፣ እነ ኃይሌ ገብረሥላሴንና በስደት ሀገር ድንቅ ድንቅ ሥራ እየሠሩ ያሉና ሠርተው ያለፉ ኢትዮጵያውያን ምሁራንንም ኢትዮጵያውያን እንዳልሆኑ አድርገው ሊያወሩ እንደሚችሉ ካላቸው ልምድ በመነሣት መገመት ይቻላል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለቅሪት ዘአካል ጥናት (archeology) ለሥነሰብእ ጥናት (anthropology) እና ለሥነቋንቋ ወይም ለሥነልሳን (linguistics) ጥናቶች እና ለመሳሰሉት በምንጭነትና መላምት ጠቋሚነት የማይተካ ሚና እንዳለው ይታወቃል፡፡ እነኚህን የታሪክ ምሁራን የሚያደናግራቸው እና የሚያሳስታቸው ነገር ንግሥተ ሳባን ዓረባዊት ናት ግዕዝንም ከነፊደሎቹ የደቡብ ዓረቢያ ነው ብለው እንዲያምኑ የሚያደርጋቸው ነገር የንግሥተ ሳባና የግዕዝ ፊደላት የታሪክ አሻራዎች እና ትውፊቶች በዓረብ ሀገሮች መገኘታቸው ነው፡፡ እንዲያው ግራ ተጋቡ ሲላቸው እንጂ በሳባ ጊዜም ይሁን ከሷም በፊት ከእሷም በኋላ በተለያየ ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ አብዛኛውን የመካከለኛው ምሥራቅን ወይም ሳውዲአረቢያን እና የመንን ከፋርሶችጋር በመፈራረቅ ትገዛ እንደነበር የራሳቸው የዓረቦችና የምዕራባዊያኑ ትውፊታዊ መረጃዎችና መዛግብት ሳይቀር የሚመሰክሩት ሐቅ ነው፡፡ እነሱ ካሏቸው መዛግብቶች አንዱም እንኳን እነሱ ኢትዮጵያን መግዛታቸውን የሚናገር የታሪክ መጽሐፍ ወይም ትውፊታዊ መረጃ የለም፡፡ እነሱም ይሄንን ብለው አያውቁም ይህ በሆነበት ሁኔታ ሳባ የየመን ንግሥት ብትሆን ኖሮ እኛ ከሰው ሀገር ንግሥት ጋር ፍቅር ላይ የምንወድቅበት እና ንግሥታችን ናት ብለን ድርቅ የምንልበት አንዳችም ምክንያት ባልነበር፡፡ ማንነታችንም ይሄንን የሚፈቅድ አይደለም፡፡
የፊደሎቻችንና የግዕዝ ወይም የአማርኛ አሻራዎች እዚያ አካባቢ የመገኘታቸው ምክንያት ማለትም ምሁራኑን ፊደሎቻችንና ግዕዝን ወይም አማርኛን ከደቡብ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተሻግሯል የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ያደረጋቸው እንዲህ የመሆኑ ብቸኛው ምክንያት ይኸው ነው፡፡ እሱም እንዳልኩት ሀገራችን ለረዥም ጊዜ ከፋርስ ጋር በመፈራረቅ አካባቢውን ትገዛው ስለነበረ በቅኝ ግዛቱ ወቅት በአንድም በሌላም ምክንያት ቋንቋውንና ፊደላቱን የማወቅ እና የመገልገል ዕድል ስላጋጠማቸው እንጂ እሴቱ ወይም ሀብቱ የእነርሱ ሆኖ ወደ እኛ ተሻግሮ አይደለም፡፡ ይህ ቢሆን ኖሮ ይህ ሀብት አሁንም ድረስ በእጃቸው በተገኘ ወይም እየተገለገሉበት በተገኙ ነበር፡፡ ነገር ግን ሀብቱ ወይም እሴቱ የቅኝ ገዢ ሀገር በመሆኑና እንደቅኝ ተገዢነትም ለቅኝ ገዢያቸው በነበራቸው ጥላቻ ወይም ለቅኝ ገዢያቸው እሴቶች በነበራቸው የባዕድነት ስሜት ወይም ሥነ-ልቡና ምክንያት የቅኝ ገዢ ሀገር እሴት ወይም ሀብት የሆነውን ቋንቋና ፊደላትን እየተገለገሉበት እንዲቆዩ ሳያደርጋቸው ቀርቷል፡፡ ወይም ደግሞ ይህንን በማድረግ ማለትም አሁንም ድረስ እየተገለገሉበት ባለመቆየታቸው የራሳቸው እንዳልሆነ አስመስክሯቸዋል፡፡ እናም ቅኝ ግዛቱ ሲያከትም በግድም ይሁን በውድ በፊደላቱ የመገልገላቸው ነገር አብሮ ሊያከትም ችሏል፡፡ የቀረ ነገር ቢኖር ፊደላቱ እዚያ አገልግሎት ይሰጡ እንደነበሩ የሚያመለክቱ ቅሪቶች ብቻ ነው፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ሳልጠቅሰው ለማለፍ የማልፈልገው ነገር ቢኖር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚከፈቱ የንግድ ድርጅቶች፣ የትምህርት ተቋማትና የሥራ ሒደቶች “ሸባ” እና “ሱባ” በሚል ሥያሜ እየተጠሩ እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር “ሳባ” ማለት ሲችሉ ለምን “ሸባ” ና “ሱባ” እንደሚሉ እንኳን በምክንያት ማስረዳት አለመቻላቸውን ከ6 ዓመታት በፊት ካነጋገርኳቸው በቅርብ ላገኛቸው ከቻልኳቸው በዚሁ ስም ከተጠሩ ድርጅቶች ተረድቻለሁ፡፡ ስገምት ግን እንደመሰልጠን ቆጥረውት ይመስለኛል ልክ እንዳልሆነ በማስረዳትም ሥያሜአቸውን እንዲያስተካክሉ ጥረት አድርጌ ነበር ድርጅቶቹ ሀሳቡን ወይም አስተያየቱን ቢያምኑበትም “የተመዘገብነውና የንግድ ፈቃድ ያወጣነውም በዚሁ ስም ስለሆነ እንደገና ወደኋላ ተመልሰን ለማስተካከል ብንሞክር ብዙ ነገሮችን ያበላሽብናል” በሚል ሰበብ ሥያሜያቸውን ለማስተካከል እንደማይችሉ አረጋገጡ፡፡
በጣም የሚያሳዝነው ግን አሁን ደግሞ የመንግሥት ድርጅት የሆነውና እንደ ሀገር አምባሳደር የሚቆጠረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ሸባ ማይልስ” በሚል ሥያሜ ልዩ ጥቅም የሚያስገኝ የበረራ ደንበኝነት አገልግሎት ዘዴ መዘርጋቱን በብዙኃን መገናኛ ማለትም በሬዲዮ (በነጋሪተ ወግ) እና በቴሌቪዥን (በምርአየ ኩነት) ባሰራጨው ማስታወቂያ አይተናል ሰምተናል፡፡
ከአርኪዮሎጂ (ሥነ-ቅሪት ዘአካል) እና ከአንትሮፖሎጂ(ሥነ-ሰብእ) ጥናትና ምርምር በተጨማሪ የሥነልሳን ጥናት የአንድ አካባቢ ቋንቋ ሥነልሳን የዚያን አካባቢ ሕዝብ ማንነት ለማወቅ ዋነኛ መለኪያ ነው፡፡ እንግዲህ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ “ሸባ” እና “ሱባ” የሚለው ቃል ዓረቢክ ነው፡፡ የእኛ ቋንቋ “ሳባ” ነው የሚላት፡፡ በአማርኛና በግዕዝ የተጻፉ መጻሕፍትም አንዳቸውም እንኳን “ሸባ” የሚል ቃል ተጠቅመው አያውቁም፡፡ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስም የአማርኛውና የግዕዙ “ዓረብ” የሚለውን ቃል የእንግሊዝኛው “ሸባ” በማለት ሲጠራው የአማርኛውና የግዕዙ “ሳባ” የሚለውን ደግሞ የእንግሊዝኛውም “ሳባ” በማለት ነው የሚጠራው፡፡ ለምሳሌ መዝ.፸፩፣፲ psalm 72÷10
ይህም ማለት ደግሞ የእንግሊዝኛው “ሸባ” ማለት “ዓረብ” ማለት ነው ማለቱ ሲሆን የእኛ ሰዎች ይህንን ቃል ማለትም “ሸባ” ወይም “ሱባ” የሚለውን ቃል “ሳባ” ለማለት መጠቀማቸው የሳባን ማንነት ኢትዮጵያዊት ናት ወይስ የመናዊት? የሚለውን ለመወሰን ቋንቋዎቻችንን የሚያጠኑትን እና የሚመረምሩትን የሥነልሳን (Linguistics) ባለሙያዎችን የተሳሳተ ድምዳሜ እንዲደርሱ ያደርጋል፡፡ እነሱ ይህ አጠራር አዲስ የመጣና እንዲህ በማለታቸው የሚያስከትለውን ችግር በማያውቁ ሥልጡን መሀይምናን አማካኝነት አሁን በቅርቡ ወደሀገራችን መምጣቱን ሳያውቁ ቃሉን ከእነዚህ ሰዎች አንደበት በመስማታቸው ብቻ የተሳሳተ ድምዳሜ ያደርሳቸዋል፡፡ “ሳባ”ን “ሸባ” ወይም “ሱባ” ብለን በመጥራታችንም ሳባን የእኛ ናት ለሚሉት የመኖችም ጥሩ ማስረጃና እንዲህ የሚሉትንም የእኛን ሰዎች ጥሩ ምስክሮች ያደርጋቸዋል፡፡ በመሆኑም ሲጀመር በቋንቋችን ያማረና በታሪካችንም ትልቅ ሥፍራ የያዘውን “ሳባ” የሚለውን ስም ሸባ ወይም ሱባ የምንልበት አንዳችም ምክንያት የለምና እንዲህ በማለት እየጠሯት ያሉትን ሰዎች እና ድርጅቶች በማስረዳት ከስሕተታቸው እንዲታረሙ እንድናደርግ መልእክቴን ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ አመሰግናለሁ፡፡
እንደ ኢትዮጵያዊ እንዲህ ዓይነት ስሕተት መሥራት በጣም ጸያፍ አሳፋሪና፣ አኩሪ ማንነትን መካድ ወይም ከማንነት መሸሽ በመሆኑ በተመሳሳይ በሌሎች ቃላትና ሥያሜዎች ላይም እንዲሁ ዓይነት ስሕተት በሰፊው ይስተዋላል እና ምነው ወገኔ ወርቅ የሆነ ማንነት እያለህ መናኛ የሆነውን የባዕድን ማንነት ወይም መለያ ሙጥኝ ማለትህ? በስንት ድካምና መሥዋዕትነት ድንቅ የሆኑትን መለያዎችህን ያነጹ ጽኑዓን አባት እናቶችህ ይህንን ነውርህን ቢያዩ ምንኛ እንደሚያፍሩብህና እንደምታስከፋቸውም ልብ ብለኸው ታውቅ ይሆን?፡፡
ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ ቀደም ሲል እንዳልኩት መጽሐፍ ቅዱስ የያዛቸው መረጃዎች ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ባሻገር ለታሪካዊ ክሥተቶች ጥናትና ምርምር ለአጥኚዎችና ተመራማሪዎች ዓይነተኛ ግብዓት ነው፡፡ ቅ.ል.ክ. ሰባት መቶ ዓመታት በፊት ልዑል እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል የተናገረውን ቃል እንመልከት፣ የዚህችን ሀገር ሥረመሠረትና ማንነት ለመረዳት ይበጃል፡፡ ኢሳ.፲፰ን ስናነብ በዚሁ አጭር ምዕራፍ ሁለት ጊዜ ተደጋግሞ የተጻፈን ቃል እናገኛለን፡፡ ቃሉም “እናንት ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደሆነ ወገን ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሒዱ” ይላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሱት ኢትዮጵያና ግብጽ በመሆናቸው ይህ ቃል በትክክል ለኢትዮጵያ ይሁን ለግብጽ ማንን ለመግለጽ እንደሆነ ግልጽ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ቃሉን ልብ ብለው ቢመለከቱት ግን ቃሉ በትክክልም ኢትዮጵያን የሚገልጽ እንደሆነ ይረዳሉ፡፡ “ወንዞች ምድራቸውን ወደ ሚከፍሉት ሕዝብ” በማለት ከ ዘጠኝ እስከ ዐሥራሁለት በሚደርሱ ታላላቅ ወንዞቿ ምድሯ የሚከፈለው ኢትዮጵያ እንጂ በወንዞች ሳይሆን በአንድ በዓባይ ለዚያውም በእኛ ወንዝ ብቻ ምድሯ የሚከፈለውን ግብጽ አለመሆኗን ይረዳል፡፡ ይህ ጥቅስ የሀገራችንን ታሪክ፣ ልዕልና ክብር ኃያልነት ወይም አጠቃላይ ማንነት ተጠቅልሎ የተያዘበትና የተገለጸበት ቃል ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሀገራችን ውጪ በእንደዚህ ዓይነት ቃል የተገለጸ ሀገር የለም፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጥንታዊ የአውሮፓ ታሪክ ጸሐፍትም ጭምር ገናና ታሪኳ በስፋት የተገለጸበት አጋጣሚ አለ፡፡ የጥንቱ የአውሮፓዊያኑ የዓለም ካርታ አትላንቲክ ውቂያኖስን ከሁለት ቆርጦ ደቡቡን ክፍል “የኢትዮጵያ ውቂያኖስ” ብሎ ይጠራው ነበር፡፡ በምሥራቁም ዓለም ከታሪክ እንደምንረዳው ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕንድን አልፋ እስከ ቻይና የባሕር ጠረፍ ድረስ ትገዛ እንደነበረ መዛግብት ቢያስረዱም አሁን ያለንበት እና የወደቅንበት ማጥ ይህንን ገናናና የከበረ ታሪክ የሚሰማውንና የሚያነበውን ሁሉ እውነት የነበረ እና የተደረገ መሆኑን እንዳያምን ወይም እጅጉን እንዲጠራጠር ሲያደርገው ይታያል ወይም ይስተዋላል፡፡ አንዳንዴም እንዲያውም “አይ ሌላ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች እንጅ ይህችማ ልትሆን አትችልም” በማለት በድፍረት ያለሐፍረት እስከመናገርና እስከ መጻፍ ሲደረስ ይታያል ለዚያውም ከኢትዮጵያዊያንም ጭምር፡፡ ነገር ግን ያቺ ገናናና ልዕለ ኃያላን የነበረችው ሀገር በእርግጥም ይህች ዛሬ ወድቃ የምናያት አገራችን ኢትዮጵያ መሆኗን መጽሐፍ ቅዱስ የምትገኝበትን መልክዐምድራዊ ቦታ ጭምር እንዲህ ባለ ቃል ይገልጻል፡፡ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፡፡ እሱም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል” ዘፍ. 2፡13 በማለት፡፡ በመሆኑን ግዮን ወይም ዓባይ ከኢትዮጵያ ውጭ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውስጥ ፈልቆ ምድሯን የሚከባት ወይም የሚዞራት ሀገር ያች ማለት ኢትዮጵያ ናት ስለሆነም ምንም የሚያደናግር ወይም የሚያምታታ ነገር የለም፡፡
እርግጥ ነው ትላንት የነበረችው የኢትዮጵያ አካለመጠን ወይም የቆዳ ስፋት ዛሬ ያለችው ኢትዮጵያ ብቻ እንዳልሆነች በዚህ ዘመን ያለን ኢትዮጵያዊያን የዓይን ምስክር በመሆንም ጭምር የምንረዳው እና የምናውቀው ሀቅ ነው፡፡ ነገር ግን ያቺ ትላንትና የነበረችው ግዙፏና ኃያሏ ኢትዮጵያ የግዛት አካሏ እየተቀነሰ እየተቀነሰ የሚቀነሰው የራሱን ስም እያወጣ ሲሔድ ኢትዮጵያ የሚለው ስም አሁን ያለችው ኢትዮጵያ መጠሪያ ሆኖ ቀረ፡፡ ይሄ መሆኑ ደግሞ ጥንት የምትታወቀዋ ያቺ ገናና ባለሰፊ ግዛት ኢትዮጵያ ትባል የነበረችው ሀገር ምንም እንኳ የግዛት አካሏ ሰፊና ግዙፍ ቢሆንም በወቅቱ ዋና ማዕከሉ ግን ይች አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያ እንደነበረ አሁን ድረስ ስሙን ይዛ መቆየቷም አንዱ ማረጋገጫ ነው፡፡ በመሆኑም የጥንቷ ኢትዮጵያ ገናና ታሪክና እሴቶች ሁሉ የማዕከሉ ወይም አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ሀብት መሆኑ እርግጥ ነው ማለት ነው፡፡ ወይም የሚያሻማ ጉዳይ አይሆንም ማለት ነው፡፡
አሁን ቀደም ሲል ወደአነሣነው የነቢዩ ኢሳይያስ ቃል ልመለስ እና “ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ” ረጅም አለ እንጂ እረጃጅም አለማለቱን ልብ ይሏል፡፡ እንዲህ ማለቱም ሊናገር የፈለገው የሕዝቡን ታሪክ እርዝማኔ እንጂ የሰዎቹን የቁመት እርዝማኔ አይደለምና፡፡ “ለስላሳ” አለ ጠባእዬ ሕዝቡን ሲገልጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላምና በፍቅር ለመጣው ሁሉ ያለውን ፍቅርና አቀባበል ሲገልጽ፡፡ “ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደሆነ ወገን” እንግዲህ ትልቁ ነገር ይህ ነው፡፡ ከላይ ያልነው ወይም የጠቀስነውን በዓለም ታሪክ ጸሐፍት እንደነ ሄሮዱቶስ እንደነ ሆሜር ባሉት ዘንድ የተነገረውን የጥንቷን ገናና ኢትዮጵያን ታሪክ ከዚህ ጋር ያያይዟል፡፡ ነቢዬ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት ሰባት መቶ ዓመታት በፊት ምን አለ “ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደ ሆነው ወገን” የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀግንነት ታሪክ ከማንም የቀደመ መሆኑን ሲያጠይቅ “ከመጀመሪያው” አለ “ወገን” ማለቱ በአምልኮተ እግዚአብሔር እንደምንዛመድ ለማጠየቅ፡፡ ከዚያም ቀጠለና “ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሒዱ” አለ፡፡ “ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ” ማለቱ ለጊዜው በዘመኑና ከዚያም በፊት የነበረውን ታሪኩን ሲናገር ነው ፍጻሜው ደግሞ በጌታ ምጽአት መቃረቢያ የምትኖረውን በብዙ የትንቢት መጻሕፍት የተነገረላትን ኃያሏን ኢትዮጵያን መግለጡ ነው፡፡ “ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ” አለ ወንዞች ብሎ የበርካታ ወንዞች ባለቤት መሆኗን ሲናገር፡፡ “ምድራቸውን” አለ ያ ታላቅና ገናና ያንን ሁሉ ታሪክ የሠራ ሕዝብ ከደቡብ ዓረቢያ ፈልሶ ምንትስ እንደሚሉት ቀባጣሪያን ዲስኩር ሳይሆን ከመጀመሪያውም መሠረቱ እዚያው መሆኑን ከየትም ስደተኛ መጻተኛ ሆኖ የገባ አለመሆኑን ሲያጠይቅ ሲያረጋግጥ “ምድራቸውን” አለ፡፡

ይህ ማለት ግን ከደቡብ ዓረቢያ ፈልሰው ወደ ሀገራችን የገቡ ወገኖች ጨርሶ የሉም ለማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ ከሴማውያንና ከኩሻውያን ከሌሎችም ነገዶች ከደቡብ ዓረቢያም ይሁን ከሌሎች የተለያዩ ሥፍራዎች 1ኛ. ቅኝ ገዥ ቅኝ ከሚገዛቸው ሀገሮች ወታደሮችን በገፍ የማጋዝና ላለበት ጦርነት የማሳተፍ ልማድ ነበርና ከፈርዖኖች ጋር በነበረን ጦርነት ምክንያት በውትድርና 2ኛ. በባርነት 3ኛ.በስደት እና በሌሎችም ምክንያቶች ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ወገኖች አሉ፡፡ ባሕልና ቋንቋቸውም ሲታይ ከመጡበት ሥፍራ ካሉ ሕዝቦች ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አላቸው፡፡ ከጊዜ ብዛት ባሕል ቋንቋቸውን ቀድሞ የግዕዝ ተናጋሪ ከነበረው አማርኛ ተናጋሪ ወይም አማራ ከሚባለው ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ ጋር ማስተሳሰር እና ከሀገሪቱ እሴቶች ጋር ለመዋሐድ ችለዋል፡፡ ይህም ሆኖ ከላይ እንዳልኩት ባሕል ቋንቋቸው ሲታይ ከመጡበት ሀገር እና ሕዝብ ባህል ቋንቋ ጋር ያለውን አንድነት በግለጽ ማየት ይቻላል፡፡ እነዚህም ሕዝቦች ከፊሎቹ በወቅቱ የመንግሥት አስተዳደር ማዕከል ከነበረችው አክሱም እና በዙሪያዋ ሲገኙ ሌሎቹ ደግሞ በሀገሪቱ የተለያዩ ሥፍራዎች ይገኛሉ፡፡ እናም እንግዲህ መጻሕፍት ሳይቀር የሚፈሯት የዚህች ሀገር ታሪክ በጥቂቱም ቢሆን ነገር ግን ግሩምና ስስት በሌለበት አጭር ቃል በኢሳ.08 እንዲያ ታስሮ ተቀምጧል፡፡
Wendime hoy ante ewunetegnaw ethiopian nehi! ethiopia honu yalastewalutin legna le ethiopianochi sile geletsikilin Egzihabiher yisxilin kemalet lela kale yelegnim.Indet sew tariku yene ayidelem bilo yikerakeral?be tiwulid ethiopia honu inji be astesaseb ethiopia alhonum.ye alemastawul libona barinet sir nachew.Wendime bante astesaseb betam korichalehu berta egnam kante gar nen!!!
THANK YOU SIR! AS PROF. MESFIN ALSO TOLD US, OUR HISTORY MUST BE RE-WRETTEN. FOR INSTANCE, THE 11TH CENTURY CHRONICLE OF ST. T/HIMANOT NOTICED ABOUT OROMO POPULATION. BUT HISTORIANS TOLD US THE 16TH AS A SPRING-BOARD.
“Saint”teklehaimanot was a politician.
The writer is a bunkrupt racist
ወንድሜ አምሳሉ የአንተን ጽሁፍ ሁሉን ተከታትያለሁ። በጣም ጎበዝ ልቦወለድ ጸሃፊ ነህ።
አንደንድ ጊዜ እውነት ነገር ትጨምርበታለህ። ይህ ደግሞ ጽሁፍህ ታሪካዊ ልቦወለድ አንዲሆን አድርጎታል።
ብዚህ ጽሁፍህ የጠቃቀስካቸው ነጥቦች ከቀድምት ደብተራዎችና የዋሻዎቹ መነኩሴዎች የተለየ አይደለም። ያው እራስህ የ21ኛው ደብተራ ነኝ ብለህ የል።
በመጽሀፍ ቅዱስ የተጠቀሱና አንተም እንድ መረጃ ያቀረብከው በሙሉ አንተው ስለምታወረው ኢትዮጲያ ሳይሆን የጥንቱን ለጥቁር ህጽቦች በግሪኮች የተሰጣ ነው። አንተ የጠቀስካቸው የመጽሀፉ ቁጥሮች በእንግሊዝኛ ኩሽ ነው የሚልው። የህም የህብሩዎቹ ለምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች በሙሉ የሰጡት ነው። ይህ ስምም ሐባሾች ወደ ምስራቅ አፍሪካ መጥተው አካባቢውን ሳያተረምሱት የተሰጣ ስም ነው። ይህን የመጽሀፍ ቅዱስ ስሞች ውስጥ ኩሽ የሚለውን ስም ወደ ኢትዮጵያ የቀየሩት ግሪኮች ናቸው። የአማሪኛውም መጽሀፍ የተተረጎመው ክግሪኩ ስነጽሁፍ ነው።
ሌላው ስለ ነገስታቱ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ጠበቃ ለመሆንም ሞክረሃል። ለምሳሌ ምኒልክ እና ሃይለ ስላሴን ተቅሳሃል። እንዴ ? እራሳቻው ሰዎቹ “ዘእምነገደ ይሁዳ ሞኣ አንበሳ[የይሁዳ አንበሳ)” እያሉ ይጽፉ ኣልነበራምን? ሌላው መረጃ ዳግሞ ኢጣሊያኖች ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ ናይጄሪያዊያን ለእርዳታ ሲመጡ “እኛም ኢትዮጵያን ነን ስልዚህ ሊንረዳችሁ መጣን” ሲሉ፡ የኃይለ ሥላሴ መልስ “እኛ ኔግሮ አይደለምን፡ ኣንፈልጋችሁም” አላቸው። ይህንን ዳግም ጸሀፊው ማርቆስ ገርቬይ ጥሩ አድርጎ ጽፈዋል።
ሌለው ስለ ንግሥት ሳባ የቀድሞ ተረቶችን ድርድረህልናል። ሴትዮዋ ሙሉ በሙሉ የአረቦች ንግስት ናት። በመጽሀፍ ቅዱስ ሁሉ ቦታ የተጠቀሰው ስለ ኢትዮጵያ መሆንዋ የምገልጽ የለም። አንደንድ ቦታ እስራኤሎችም አረቦችም “የአዜብ ንግስት” ይላሉ። አዜብ በህብሩና በአረብኛ “ደቡብ” ማለት ነው። ሼባም ትሁን ሳባ ንግስት የአረቦች ነች።
ኢትዮጵያ መሆንዋን የለፈፉ ግብጣዊያን ናቻው። ይህም ከግብጥ ኮፕትክ ቤተክርስቲያን ለሓበሻ ኦርቶዶክስ ተቀርጾ የተሰጣ “ክብራ ነገስትና ፍትሃ ነግስት” የሚባሉ በአረብኛ ተጽፎ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ የተሰጣ ሰነድ ነው። ይህም የሆነው ከሶሪያ ነጋዴዎች ውስጥ ፍሬምናጦስ እና ኤክሶዶስ የሚባሉ ወደ አክሱም 360 ዓም አካባቢ መጥተው ስለ ክርስትና ከሰበኩ በኋላ ወደ ግብጽ ሄደው ጉዳዩን ለኮፕቲኩ አሳወቁ። እስከዚያ ዲረስ ሃበሾቹ በጨረቀና በድንጋይ ያመልኩ ነበር። ስለ ኦሪት ሃይማኖት የሚያዉቁት አልነበራም። ኦሪት የኩሾች እምነት እንጂ የሴሜትኮች (ኣቢሲኒያና አረቦች) አልነበረም።
ከዚያ በኋላ ፍሬምናጦስ ከግብጥ ኮፕትክ ፕፕስና ተሹሞ ወድ አቢሲኒያ ተመለሰ። እዚያው ሞቶ እዚያው ተቀበረ። ከዚያ በኋላ ለሐበሾች እስከ 1954 (በሀይለ ስላሴ) ጊዜ ድረስ ጰጰሶች ከግብጥ ይመጡ ነበር። ይህ በዚህ
እያሌ የእክሱሞች ስርዋመንግስት ወንድቆ የ ዛጉዌዎች (አገው) ስርዋመንግስት አካባቢን ተቆጠጠረ። በዚ ጊዜ ውስጥ መለት 901-1270 ድረስ የኣገው ነገስታትና ግብጦች መሃል የሃይማኖት ጭቅጭቅ ተነሳ። በዚህ መሀል ግብጦቹ ተንኮል ሰሩ። ይህም “በኒቅያ ጉባኤ 360 የሃይማኖት ሊቃውንት በተገኙበት ሐበሾች/ኢትዮጵያኖች የራሳቸው ጰጰስ እንዳይኖራቸው ተወሰነ” ብለው አወጁ።
ከዚህ በመቀጠል ‘ክብረነገስቱና(የነገስታት ክብር) እና ፍትሐነግስት(የነገስታት ህግ) የሚለውን መጽሀፍና የነገስታቱ ክብር የተባሉትን 110 ሰዎችን ይዘው ከግብጽ ወደ ሀበሻ መጡ። እንግዲህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ “ሳባ ንግስት ለሰለሞን ወለደች። የኢትዮጵያ ንግስት ነበረች። ይህ ይህን አገር የሰላሞን ዘር መግዛት አለበት” ብለው ለቄሶች እና በወቅቱ ክርስትና ተከታዮችና፣ ወቶአደሩን/ሰራዊቱን አሳመኑ። በዚህ ጊዜ የሰራዊቱ አላቀ የአማረው ነገድ (ጎሳ)ይኩኑ አምላክ ነበር። ቀሶቹ በ ቄሴ ተክለ ሃይማኖት መሪነት። ሰራዊቱ በአማራው ዘር ይኩኑ መሪነት የዛጔን መንግስት በኃይል ገልብጠው በመቅቱ የስርዋመንግስቱ መሪ የነበረ ይትባረክ የተበለውን ከስልጣን አበረው ወርሂመኑ በተበለው ቦታ ደርሶበት አርደው ገደሉት። እንግዲህ ይህን ሸሪ የስሩ የግብጾች የሃይማኖት ሊኡካንና የሓበሻ ቀአሶችና የአማራው ሰራዊት/ወቶኣደር ናቸው።
ስለ ዚህ ሼባ ወይም ሳባ የሚትባል ነግስት በዚህ በ ኢትዮጵያ ምድር አልነበራችም። ነገር ግን ሃበሾች የአረብና እስራኤል ነገድ ዘሮች ስለ ነበሩ፡ ልክ መንዝና መረቤቴ ለጎንደር ይገብሩ እንደነበር ሁሉ ሀበሾችም በአረቢየ የኣሁኑ ያማኒያ መንግስት ግብር የሊኩ ነበር። መሰረታቸው እዚያ ስለሆነ።
በሌላ በኩል የኩሾች ንግስት እንዳኬ የሚትባል በኑቢያ ቴበስ እንደነበራችና፣ መቃብርዋ እዚያው መኖሩ እሙን ነው።
ለላው። ስለ ሰበ እና ሱባ ነገር አንስተህ ነበር። ሱባ ከኦሮሞ ጎሳ ውስት የቾ ልጅ ነው። ሰዴን ሱባ ይባላሉ። (ሶስቱ ሱባዎች) ማለት ነው። ሰበ የሚለው ደግም ጎስ፣ ብሔር፣ ወይም ነግድ የሚትሉት ሆኑ፣ የኩሾች ስም ነው። ሰበ አፋር፣ ሰበ ሳሆ፡ ሰበ ኦሮሞ፣ ሰበ ብሌን ይህ ስም ሳባዊያን ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስይመጡ የነበረ ነው። ስለዝህ ወንድሜ፣ ታሪክን አትበውዙ፣ አታምታቱ። ሃቀኛ መረጃዎች አሉ። አትደብቁ።
ፍዳሎቹ የአረቦች አይደለም።መሰረቱ የኩሾች (ኬሜቶች)በ አሁኑ ግብጽ ውስጥ የሚገኙ ህዝቦች ናቸው። ከዚያ ፌንቃዊያኒና ቀጥለው ግሪኮች ወሰዱት። እንዳገና ከግሪኮች ወደ ግዕዝ ተቀየሩ። ስም ተሰጣቸው ማለት ነው። ሐበሾች ግን ከኣረቢያ ነው የመጡት። ይህ ምንም የሚያወላዳ የለውም።
አቶ ቃሉ ኩሳ እድሜህ ስንት ነው? እርግጠኛ ባልሆንም ገና ጎረምሳ ትመስለኛለህ፡፡ እድሜህ እየጨመረ እየበሰልክ ስትሄድ ይህ አሳፋሪ በውሸትና በፈጠራ የተሞላ አስተሳሰብህ እንደሚያሳፍርህ አልጠራጠርም፡፡ እድሜህ ከጡረታ በላይ ሆኖ እንዲህ እያሰብክ ከሆነ ግን ይሄ የጤና አይደለምና ወደ ህክምና ማዕከላት ጎራ ብትል መልካም ነው፡፡ ፍጹም ኃላፊነትና ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ በእንጭጭ ጠባብነት ታውረህ የሌለ ነገር ስትዘባርቅ ቅንጣት ታክል እንኳን አይሰማህም፡፡ በእውነት በጣም አሳፋሪ ሰብእና ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ እንዲህ ብለህ የምታስበው ኦሮሞ ለዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ እሴቶች ባእድ ነው ብለህ ስለምታስብ ነው፡፡ ወንድምየ ተሳስተሀል እዚህች ሀገር ያለ ብሔረሰብ ሁሉ ካለበት ጊዜ ጀምሮ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ ያለደረገ ወይም ሊያደርግ የማይችልበት ምንም ምክንያት የለምና የኢትዮጵያ አኩሪ እሴቶች ሁሉ የአንድ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ብሔረሰቦች ነው፡፡ ለማንኛውም ብትታከም መልካም ይመስለኛል፡፡ በዚህ ከቀጠልክ ልታብድ ሁሉ ትችላለህ፡፡ ከበድ ያለ የስነ ልቡና ሁከት ውስጥ ነው ያለኸው፡፡ ይህ በሽታ ከተወሳሰበ የማንነት ቀውስ ውስጥ ከቶሀል ኢትዮጵያዊነትህንም አስክዶሀል፡፡ እስኪ ምህረት ይላክልህ፡፡
ይላክልህ፡፡ “አክሱማዊያን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔርን አያመልኩም” ብለህ ላልከው የደነቆረ አሳፋሪ ትችትህ የጠቀስኳቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ቢሆኑም ልጨምርልህ የአክሱም ሐውልት ቅርጽ የምን ይመስልሀል? እንደዛሬው ጥምቀት ሁሉ በኦሪቱ ሥርዓት የእግዚአብሔር ልጅነት ማረጋገጫ የነበረው ግዝረትን የሚያመለክት ነው እሽ? የአክሱም ሐውልት የተገረዘ ብልት ቅርጽ ነው፡፡ ሌላው በሐዋርያት ሥራ ላይ 8፤20 ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ታሪክ በአስተውሎት አንብብ እሽ? ይግለጥልህ፡፡
yekedemt debterawoch alk??? ante yetekeskwn selemen enemen? mizaneh menden new? ante debterawoch yalkachew likawent mehonachewen lemasawek men yetekes? Qaalluu.. men asebeh new Ethiopiawi aydelehem? yerasehen teteh yesew nafaki.. banda athun
I do not think the writer understands what it takes to do research. Instead of just claiming historians, linguistics, archeologists, … are wrong, I am expecting him to come up with evidences. Every one is wrong for the writer. I wish all researchers are wrong but still their account is trustable than your dreams. For future come up with your research or try to cite others work. For now you are failed.
Qaalluu: Where are u from?
Ethiopia is Ethiopia and it’s history been in the past and will remain in future.
Remember ALL we will pass BUT Ethiopia remain for GENERATION Y.
Thanks u
Ayu
በግዮን የተከበበች አገረ-ኢትዮጵያ ማለት ኣፍሪካ በሙሉ ማለት ነው። ለምሳሌ የንተን ጽሁፍ ጥቅስ እንውሰድ።
“የጥንቱ የአውሮፓዊያኑ የዓለም ካርታ አትላንቲክ ውቂያኖስን ከሁለት ቆርጦ ደቡቡን ክፍል “የኢትዮጵያ ውቂያኖስ” ብሎ ይጠራው ነበር፡፡ በምሥራቁም ዓለም ከታሪክ እንደምንረዳው ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕንድን አልፋ እስከ ቻይና የባሕር ጠረፍ ድረስ ትገዛ እንደነበረ መዛግብት ቢያስረዱም—” ይለል የንተ ጽሁፍ።
በግዮን ወንዝ የተከበባ የሚባለው አፍሪካን በሙሉ በአንድነት ኢትዮጵያ ለሚሉት እንጂ በቀበሌኛ በሚያስቡት “ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት/ኣቢሲኒያ/አቤክስ” ለሚሉት ስግብግበኞች እንደሚሉት አይደለም።
በግዮን የተከበበች ኢትዮጵያ/ኩሽ ሲሆን፡ ይህም በቀይ ባህር፡ መዲትራኒያን ባህር፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ እና ህንድ ዊቅያኖስ ናቸው። “በወንዞች የተከፋፋላች ማለቱም በአፍሪካ ውስጥ የሚግኙ ወንዞች የአሁንዋን ኢቲዮጵያን ቸምራው ማለት ነው።
ሌላው የንተው እና ደብተራዎች ተረት ደግሞ፣ ኩሽም/ሐም ፥ ሴምና ያፌት ሁሉ የተገኙ በአረብ/ኤስያ ነው ማለትህ ነው። አዳም/ኖህም እዚያው ተፈጠሩ ስትሉን ትንሽ አተፍሩም። የኤዳን ገነትም እዚያው እራቢያ ወይም የመኒያ ውስጥ ነው ሊትሉን ትዳደላችሁ።
ነግር ግን ይህን ምን ሊትሉት ነው?
“The Greeks looked to old Ethiopia and called the upper Nile the common cradle of mankind. Toward the rich luxuriance of this region they look for the “Garden of Eden.” From these people of the upper Nile arose the oldest tradition and rites and from them sprang the first colonies and arts of antiquity.”
The Greeks also said that Egyptian derived their civilization and religion from Ethiopia.
Ethiopians were the first men that ever lived, the only truly autochthonous race and the first to institute the warship of the God and the rites of sacrifice.”
“The highly developed Merodic inscription are not forwarded in Egypt north of the first cataract or in Nubia south of Soba.” (Wonderful of Ethiopia of the Cushite Empire Ch.I. page 17-21)፣ (Meroe-Crowfot pp.6,30)
በ1930ዎቹ ውስጥ አንድ ደብተራ ከፈረንጆች አገኛሁኝ ብሎ የጸፈው እንደፈረንጆቹ ለጥቁር አፍሪካዊያን ንቀት የተመላበት ነው ። “ኩሽ ወይ ሓም ወደ አፍሪካ ሲመጣ እንደ እኛው ነጭ ነበር። በኃላ ጠቆራ።” ይላል።
ነገር ግን መጀማሪያ ሰው መገኛ እዚሁ ኣፍሪካ ውስጥ ነው። አዲስቱን ኢትዮጵያ ጨምራው። የመጀመሪያ ሰው የተገኛው ጎና በሚባል ውንዝ ላይ አፍሪካ ውስጥ ወደ ምዕካላዊ አፍሪካ ነው። የሉስንም ጉዳይ ኣንዳት ረሱ (3-4 ሚልዮን ዓመት) መሆኑን። የመጀመሪያ የንግግር ዲምጽም በዚሁ አፍሪካ ነው።
እናንት እንደሚትሉን ከሆነ የአዳም እድሜ 5500 ከልደት በፊት፣ የኖህ ኣድሜ 3200 ከልደት በፊት፡ ዓመት ምህረት ሲጨመርበት ከ7000-8000 አይበልጥም። ይህም የተወሰደው ከ እስራኤሎች የሐሳብ ግምት ነው (ሃይማኖታዊ) ነገር ግን የሰው ልጅ በሚሊዮን የሚቆጠር እድሜ በዚህ ምድር አለው።
The latest evidence suggests that modern humans left Africa twice, first around 90,000 years ago, through Sinai into the Levant, an exodus which petered out.
The second exodus occurred 45,000 years later, along a route across the mouth of the Red Sea at the “Gate of Grief” in Ethiopia. Humans reached the Middle East and Europe via the valleys of Mesopotamia, and south East-Asia by “beach-combing” along the coasts. (This cannot quite be squared with the most resent evidence that early humans reached Australia around 60,000- 50,000 B.P)
Most likely, modern humans arrived in Siberia between 40,000-30,000 years ago, after evolving in Africa.” (Ideas, a history of thought and invention, from fire to freud (peter watson 2005 USA/ new York page 40-42)
One view is that language emerged in the click sounds of ancient tribes in Southern Africa (the San, for example, or the Hadzabe), clicks being used because they enabled the hunters to exchange information without frightening away their prey on the open Savannah. Another view is that language emerged 300,000-40,000 years ago, and even 1.75 million years ago, when early man would sing or human a rhythmical way.
The most important dates to remember, when major changes in technology occurred, are 2.5 millions years ago, 1.7 million, 1.4 million, 700,000, and 50,000-40,000 years ago.
The oldest artifacts yet discovered come from the area of the river GONA in Ethiopia. … To the untutored eye a primitive stone ax from Gona looks little different from any pebble in the area.” (Ideas, Peter Watson p. 23)
ዘርህ ይብዛልን ቃሎ
ምሁር፡የታሪክ ሊቅ፡በዕወቀት የተሞላህ ተኝታኝ ነህና ሁሌም ከፍ ብለህ ኑር ፡፡ባለህ ላይ አቅም ጨምር በርታ ብያለው፡፡
ኣምሃራ ሐሳብ ሰጪዎች ለምን ስድብ ያስቀድማሉ?
ኣንዱ ችግራቸው በያዙት ነገር ማሳመን ስለማይችሉ ነው። ታሪካቸው በተረት-ተረት የተሞላ ስለሆነ ነው። ሁለተኛ የ አረብ ዝርያ ስለአላባቸው የበታችነት ስሜት ስለአጠናወታቸው ቶሎ ይቆጣሉ ብዙ ያዋራልሉ። በባዶ ጉራ ይፎክራሉ፣ ያቅራረሉ። ጉዳቻው ሲነገራቸው ያብዳሉ። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ(ኩሻዊ) ስላልነበሩ ኢትዮጵያዊ መሆን ለነሱ ከፍታኛ ክብር ነው። የጥንቱ ኢትዮጵያዊ የነበረ አሁንም ያለው ምንም አይሰማውም። ምክንያቱ፣ ኢትዮጵያውነቱ(ጥቁርነቱን) የምነሰው የለምና። እነሱ ግን ስላልነበሩ ለመሆን የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የለም። ኢውነቱን ሲነግሩአቸው ያብዳሉ። እንድ የኦሮምኛ ተረት ነበር። “ውሻ ዘንድ የውሻ በሽታ(እብደት) አትናገር። ኢነሱም ያብዳሉና” ይላል።
ሌላው ሐሳብ ሰጪ ደግሞ ስለ እኔ ተጭንቀ ብዙ ብላዋል። ባንዳ፥ አእምሮው ልክ ያል ሆነ፣ ልጅ፣ የጃጀ ሽማግሊ ወዘተ፣ ብሎኛል።
እኔ ግን የጸፍኩት እውነትና። ከእውነተኛ ምንጭ ያገኛሁት ነው። ስልዚህ የእነተ ስድብ አይደንቀኝም። ምክንያቱ ሐሳቤን አምብባችሁ ስለተረዳችሁ ደስ ብሎኛል። በተጨማሪ ደግም። እኔ የቁምጥና ዘር የለብኝም፡ የኮማሪቶች ውላጅ አይደለሁም፡ በየልማና ባህል የተጠናወትኩ አይደለሁም። ስለዚህ ለአልባሌዎች ስድብ ደንታ የለኝም።
“ይላክልህ፡፡ “አክሱማዊያን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔርን አያመልኩም” ብለህ ላልከው የደነቆረ አሳፋሪ ትችትህ”የጠቀስኳቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ቢሆኑም ልጨምርልህ የአክሱም ሐውልት ቅርጽ የምን ይመስልሀል? እንደዛሬው ጥምቀት ሁሉ በኦሪቱ ሥርዓት የእግዚአብሔር ልጅነት ማረጋገጫ የነበረው ግዝረትን የሚያመለክት ነው እሽ? የአክሱም ሐውልት የተገረዘ ብልት ቅርጽ ነው፡፡
ወንድሜ አምሳሉ፣ እባክህ ከንዱ ወደ አንዱ አትዝለል። የባሰውኑ የተረት-ተረት ታሪክህን ያጋልጣል። ስለ ግርዛት በምልልሳችን ውስጥ አንስተሃል። መጀመሪያ ከእናንተ የተገረዛው ሰው እብርሃም ነው፡ የአረቦቹና የእስራኤሎቹ(ህብሩዎች) የእስማኤልና የይስሃቅ አባት መለት ነው። አሱም ወደግብጽ ከመጣና አጋት ከሚትባል የሳራ ገርድ (ግብጻዊት) እስማኤልን ከውለዳ በኃላ በ99 ዓመት እስማኤል በ13 ዓመቱ በአንድነት ለእግዚኣብሐር ቃል ኪዳን ለመግባት ለመጀመሪ በሴሜቲኮች ውስጥ ግርዛት ተጀመረ። ኦሪት ዘፍጥረት 17:23 አምብብ። ኩሾች ግን ከሱ በፊት ለብዙ ዓመታት ሲገረዙ ነበር።
ሌላ ደግሞ ስል አክሱም ሃውልት ተቀስክልን። ምኖ ጀል አክሱም የሓበሾች አይደለችም። ከባህር ማዶ መጥታችሁ ወረሳችሁ።
“ኣረብ ፋቂህ እንዲህ ብሎ ነበር። “ይህች ከተማ ጥንታዊት ናት ይባላል። ያሠራት አይታወቅም። አንዳንዶቹ ድዙ እለ ቃርናይን ይላሉ። —ኣረብ ፋቂህ አክሱምን የሠራት ድዙ እለ ቃርናይን ነው ይላል ያለው ይኽን የመሰለ ስም በነገስታት ዝርዝራችን የለም።” (የግራኝ ወረራ፥ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ግጽ 472)
“— የአገር ተወላጅ ጸሐፊ የተወው የጽሑፍ ቅርስ መሆን አለበት። እርሱም ወደ መጀመሪያው ደበስበስ ባለ አኳኋን እንደዚህ ሲል ያመጣዋል። “ከመዝኣ ጥንተ ሡሩሪሃ ለእምነ ጽዮን ገበዝ አክሱም ቀዲሙ ተሣለለት በመዝብር ኅበ ሀሎ መቃብሪሁ ለኢትዮጵስ ወልደ ኩሳ ወልደ ካም” ይላል። በዚህ በመዝብር ያለውን አንዳንዱ ጽሑፍ በመዝሙር ብሎት ይገኛል። (ግራኝ ወረራ ግጽ 473) ድሮም እናንተ በምዝሙርና በቀራርቶ ማን ይችላችዋል?
“በዚህም ሥፍራ የካም የልጅ ልጅ የኩሳ (ኩሽ) ልጅ የኢትዮጵስ መቃብር በአለበት ላይ መሆኑን ያመለክታል። ይዅም ሴማውያን ሳይሆኑ የመዠመሪያዎቹ ቆርቋሪዎች የካም ወገኖች (ነገደ ካም) መሆናቸው ነው። ልሆንም ይችላል። ከሴማዊያን (ነገደ ዮቅጣን) በፊት ያገሩ ጌቶች የካም ነገዶች እንደነበሩ ታሪክ ሁሉ ያመለክታል።” (ግራኝ ወረራ ት/ጸድቅ። መ፣ 473)
ይህ ማለት እንግዲህ እክሱም የነገዳ ኩሳ (የኦሮሞ፥ የቤጃ፣ የአገው፣ የከለው፥ የበለው፥ የሳሆ፥ የአፋር፡ የቅማንት ወዘተ)ማለት ነው።
ሌላ መረጃ ደግሞ የ ክፍላ ዘመኑ (21ኛው) ደብተራ ፕሮፌሶር ጌታቸው ሃይሌ እንዲህ ይላሉ። “በዚህ አጋጣሚ ሁለት ነገሮች ማስታውስ ያስፈልጋል። አንደኛው፥ ኩሳዊ/ካማዊ ቋንቋዎች ከአፍሪካ ውጪ ተናጋሪ የላቸውም። ፍጽም አፍሪካዊያን ናቸው። የውጪ ለመሞን ሐሜት እንኩዋን ቢመጣ ከአፍሪካ ውጪ ተናጋሪ ባላቸው በሴማዊ ቋንቋዎች እንጂ በኩሳዊ/ካማዊ ሊመጣ አይችልም። ሁለተኛ ኦሮሚኛ ከሱማልኛ፥ ከቅማንትኛ ፥ከአገውኛ ወዘተ ጋራ ያንድ አባት ልጅ ከሆነ ኦሮሞቹን ከነዚህ ለይቶ በቅርብ ጊዜ ከወዲያ ማዶ መጡ ለማለት ያስቸግራል። የአባ ባሕርይ ድርሰቶች ጌታቸው ሃይሌ ግጽ 100)
ፕሮፌሶር ጌታቸው በመቀጠል እንዲህ ይላሉ። “ እንደምናስታውሰው የአክሱም ‘ነገሥታት’ ስም ‘እለ’ የሚል መነሻ አለው። ለምሳሌ “እለ ዓምዳ” ፥ “እለ አለዳ” ፥ “እለ አዝጓጓ” ፥ “እለ ገበዝ” የሚባሉትን ‘ነገሥታት’ እናስታውስ። የ”እለ” ትርጉም “እነ” ነው፥ ብዙ ቁጥርን ያመለክታል። ሁለተኛው በዚህ ቃል ከሚጀሚሩ ስሞች አብሮ የሚሄደው ግሥም ብዙ ቁጥር ነው።”
ፕሮፌሰሩ በመቀጠል፥ “እለ” እና ግሡ የሚያመለክቱት ብዙነትን ከሆነ፥ ይህ እክሱማዊ የገዢ ስም አወጣጥ አባ ባሕርይ በክፍል 4 ስለ ሉባ ከጻፉልን ኦሮማዊ የገዢ ስም አወጣጥ ጋራ ተመሳሳይ ነው እኮ። እነዚህ ስሞች የነገሥታቱ ሳይሆን እንደ “ሥሉስ ኅይሌ” እንደ “ሜልባህ” የገዢ ሠራዊት ስሞች ይመስላሉ።” ይላል (ግጽ 101)
ፕሮፌሰሩ ሌላም ጥቅስ አላቸው። “ ዛጉዌውችም ተመሳሳይ የዓውደ ግዛት (ገዳ) ሥርዓት ሳይኖራቸው አይቀርም። ለምሳሌ የግዛት ዘመናቸው የተመዘገበ ሁለት የነገሥታት ዝርዝር አለ። ባንደኛው ዝርዝር ውስጥ ከተመዘገቡት 11 “ነገሥታት” 7ቱ በሁለተኛው ዝርዝር ውስጥ ከተመዘገቡት 9 “ነገሥታት” 8ቱ 40 40 ዓመት ገዝተዋል። ይህ 40 ዓመት ዓውደ ግዛት መሂን አለበት። አለዚያማ ይህ ሁሉ ተመሳሳይነት እንዴት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።” (አባ ባሕርይ ድርሰቶች ግጽ 101)
ይህ ሁሉ የሚያመለክተው አክሱም የኩሾች እንጂ የሴሜትኮች አለመሆኑ ነው። እኔ በቦታው በአካል ከ15 ጊዜ በላይ ተገኝቼ እንዳየሁት ከሆነ የአውልቱ ቅርጽ የኦሮሞ አባ ገዳዎች በግንባራቸው ላይ ይሚያዳርጉትን አዶዬ ወይም ካለቻን ይመስላል። የቦታው ስምም “ኦና” ይሉታል። ኦና በኦሮሚኛ ሰው ወይም ቤተሰብ ወይም አንድ ጎሣ ቆይቶበት ከተሰደደ ያ ቦታ “ኦና” ሆነ ይባላል። “የእነ እከሌ ኦንቱ” ይባላል።
“ለማንኛውም ብትታከም መልካም ይመስለኛል፡፡ በዚህ ከቀጠልክ ልታብድ ሁሉ ትችላለህ፡፡ ከበድ ያለ የስነ ልቡና ሁከት ውስጥ ነው ያለኸው፡፡ ይህ በሽታ ከተወሳሰበ የማንነት ቀውስ ውስጥ ከቶሀል ኢትዮጵያዊነትህንም አስክዶሀል፡፡ እስኪ ምህረት ይላክልህ፡፡” kkkkkkkkkkkkkkkk
lij Amsalu !!!!!!!!
“men asebeh new Ethiopiawi aydelehem? yerasehen teteh yesew nafaki.. banda athun”
kkkkkkkkkkkkkkkkkkk liji Eyoel!!!
for both of you this is enough.
የተሳዳቢውን ዝባዝንኬ ቃላቶችን ትተን “ባንዳ” የሚትለውን ስድብ እንመልካት። ባንዳ የሚትለው ቃል ኢጣሊያኒኛ ስሞን ትርጉሙም ቅጥረኛ ወቶአደር ማለት ሲሆን፥ በተጨማሪ በቅኝ በተያዙ ኣገሮች የሚገኙ ሰዎች አገራቸውን ክደው ለቅኝ ገዢው አገልገይ ሲሆኑ ይህ ስም ይሳጣቸውል።
በመሆኑም የተሳዳቢው ዘመዶች በኢጣሊያ ወረራ ጊዜ ግማሾቹ ከ ኃይለ ሥላሴ ጋር አገርን ክደው ወደ ውጪ ሲፈራጥጡ። አገር ውስጥ የቀረው ባንዳ በመሆን የኢጣሊያን ሰራዊት ሲያጋላግሉ ነበር። ይህ በተሪክ ተመዝግበው ይገኛል።
በሊላ በክኩል ግን ኦሮሞዎቹ በአገራቸው ውስጥ ጠላትን መቆሚያና መቀመጫ እያሳጣቸው ለአምሥት ዓመት ቆዩ።
ለምሳሌ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ (አባነብሶ)፣ ደጀዝመች ገረሱ ዱኪ (አባቦራ)፥ ጄኔራል ጃገማ ኬሎ፥ ደጀዝማች ከበደ ብዙናሽ፥ ደጀዝማች በቀለ ወያ፥ ደጀዝማች ገነነ በደኔ፡ ደጀዝማች (ሊሴ) ገብርማሪያም ጋሪ፥ ኃይለ መሪያም ማሞ (የጦሩ ገበሬ) ራስ አበበ ራጋ በቻራ ወዘተ። በጠም ብዙ ናቸው። ነግር ግን የአንተ ዓይነቱ ቀላዋጭ በእንግሊዝ እርዳታ ኃይለ ሥላሴ ሲመለስ ቶሎ ብለው የውስጥ አርባኛ ነን ብለው በቀጠፍ ወደ ስልጣን ኮርቻዎች ተፈናጠቱ። ለዚህ ነው አርባኞቹ “አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፡ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።” ያሉት።
የእናንት ዝባዝንኬ ስድብ አንድ ዮ ኦሮሚኛ ተረት አስተወሰኝ።
“በቅሎ አባትዋን ሲትጠየቅ፥ አጎቴ ፈረስ ነው ትላለች።” በመሆኑም ነው በማንነታቸሁ እያፈራችሁ በኢትዮጵያዊነት ስም የሚትነግዱ። ወይም ሀባሻናታችሁን (እቢሲኒያ፡ አጊኣዚያን፣ አረባዊያን) መሆናችሁን የሚተፍሩበት ጉዳይ ስለሆነባችሁ ነው ኢትዮጵያዊ ለመሆን ጉራ ቡራዩ የሚትሉ። እኛ ኩሾች/ኢትዮጵሶች በአፍሪካነታቸን እንኮራለን። የራሳችን ስለሆነና ማንም ሊገፈን ወይን ሊነሰን ስለማይችል እንደ እናንተ ቱልቱላ አንነፋም።
ኮሎኔል አሊርክሰንደር ቡላቶቭች ስለ ኦሮሞ ያላውን ልጥቀስላችሁ።
“in addition they have one very original custom. While living, a Oromo rarely boasts of his deeds, and it is considered improper if he himself begins to talk about how many enemies he killed (completely the opposite of Abyssinian behavior). After death, his brother or friend has the responsibility to recount where, when and what circumstances the deceased distinguished himself.” (Ethiopia through Russian eyes)
ዶክተር ኣምባቸው ከበደ የተባሉ ይህንኑ አባባል ከ ሩሲያኒኛ ቋንቋ ወደ አማሪኛ ስተረጉሙ እንዲህ ብለዋል። “በነገራችን ላይ ኦሮሞዎች ኣንድ አስደናቂ የሆነ ልማድ ኣላቸው። ይህን ያህል ጠላቶች ገድያለሁ ብሎ መናገር ነውር ስለሆነ የኦሮሞ ወንድ በሕይወት እያለ ይህን ጀግንነት ፈጽሚያለሁ ብሎ አይፎክርም (የሓበሾች ልማድ ግን የተገላቢጦሽ ነው።) ሰውየው ከሞተ በኃላ ግን የሟቹ ወንድሞች ወይም ጓደኞች፥ ሰውየው መቸ፥የትና በምን ዓይነት ሁኔታ ምን ዓይነት ጀብዱዎች እንደፈጸመ የመዘርዘር ግዴታ ኣለባቸው።” ይላል።
አቶ ቃሉ እኔ እኮ ቸገረኝ ጤነኛ ነህ ብየ እንዳልመልስልህ እንደ በሽተኛ ትዘበራርቃለህ፡፡ ሳታፍር ምን ይሉኛል ሳትል የማይመስል ነገርና ፈጠራህን መረጃ አድርገህ ታቀርባለህ፤ በሽተኛ ነህ ብየ እንዳልተውህ የምትዘባርቀው ነገር ብዙ ግንዛቤ የሌላቸውን ሰዎች ሊያሳስት የሚችል ነው ተቸገርኩ እኮ! ለምሳሌ በጣም የገረመኝ ነገር “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፡፡ እሱም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል” ዘፍ. 2፡13 ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የተናገረውን አንተ “በግዮን የተከበበች ኢትዮጵያ/ኩሽ ሲሆን፡ ይህም በቀይ ባህር፡ መዲትራኒያን ባህር፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ እና ህንድ ዊቅያኖስ ናቸው።” ብለህ ዘባረክ ወንዝ ማለትና ውቅያኖስ ባሕር ማለት ምን ልዩነት እንዳላቸው የማታውቅ ሆነህ ነው? ወይስ የአእምሮ በሽተኛ ስለሆንክ ስለምትዘባርቅ?
አቶ ቃሉ ግርዛት የኩሻውያን ባሕል እንጂ የሴማዊያን አይደለም ብለህ ከእኔ ያገኘኸውን መረጃ መልሰህ ለእኔ ትነግረኛለህ አታፍርም? ከዚህ በፊት በጽሑፌ የሙሴ ሚስት ሲፓራ ሙሴ ግርዛትን ሃይማኖታዊ ሥርዓት አድርጎ ከመደንገጉ በፊት በልጇ ላይ ግርዛት እንደፈጸመች መጥቀሴን አታስታውስም? ነው ወይስ ከሌላ ቦታ ላይ ያነበብከው መስሎህ ነው? ለነገሩ ይህ መረጃ የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ እንደመሆኑ መጠን ከከሌላ ቦታም ልታገኘው ትችላለህ፡፡
እናንተን ማስገረዝ ያስጀመሯቹህ ዐፄ ማን ነበሩ? ይሄንንም አታውቅም? ጭራሽ እራስህን “ኩሽ” በሚል ጭምብል ከልለህ ባሕላችን ነው ልትል ያምርሀል እንዴ አታፍርም? አሁን በቅርብ እኮ ነው መገረዝ የጀመራቹህት፡፡ አቶ ቃሉ አንተ እንደምትለው የኩሽ ነገድ እንደነበረውና እንዳለው ለምሳሌ እንደነ አገውና ቅማንት ባሉ ነገዶች ላይ ያለው አምልኮ እግዚአብሔርና ሥርዓተ አምልኮ የእናንተም ከሆነ ምነዋ ታዲያ ያ አምልኮ እግዚአብሔር፣ ጥልቅ የሆነው የአምልኮ እግዚአብሔር ሥርዓትና ባሕል በእናንተ ላይ የማይታየው ወይም የሌለው? እግዚአብሔር ማለት የዋርካ ዛፍና ሐይቅ ማለት ነው ካላልከኝ ማለቴ ነው፡፡ አገውንና ቅማንቶችን ካየህ ግን ያኔ የነበራቸው እሴት ሁሉ ዛሬም አላቸውና እነሱ ቢሉ ያምርባቸዋል አንተ ግን አይመለከትህም አርፈህ ተቀመጥ እሽ?
እናም ከዚህ በፊትም እንደነገርኩህ በስመ ኩሽ የኩሽ ነገድ የሆነውን ሁሉ የኛ ነው ማለት አትችልም በተጨባጭ ያለው ነገር ያንን የሚያሳይ የሚያረጋግጥ አይደለምና፡፡ ስለ ኦሮሞ ብሔረሰብ ከጻፉ የታሪክ ጸሐፍት ሰሎሞን ደሬሳ “የኢትዮጵያ ታሪክ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን” ፣ ተክለጻድቅ መኩሪያ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንድል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ” ፣ አለቃ ታዬ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ” ፣ አባ ባሕሪ “የ——- ታሪክ” ሌሎችም የኦሮሞ ሕዝብ ከውጭ መግባቱን መምጣቱን ሁሉም ይስማማሉ የሚለያዩት የገባበትን ዘመንና የመጣበትን ቦታ ነው፡፡ ግማሹ ከሱማሊያ ነው ሲል ግማሹ ከማዳጋስካር ነው ይላሉ፡፡ ዘመኑንም ግማሹ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው ሲል ግማሹ በ11ኛው ነው ይላሉ፡፡ ለማንኛውም በስመ ኩሽ ጠጋ ጠጋ ማለትህ የተሳሳተ አመለካከት ነውና ታረም፡፡ ከላይ እንዳልኩት ያንን ሁሉ እሴት የሚያሳዩ አሻራ የላቹህምና፡፡ እንደመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ሴምና ካም (ልጆቹ ከነአን፣ ኩሽ) ሁሉም መሠረታቸው አፍሪካ አይደለም፡፡ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተሸግረው የገቡ ናቸው፡፡ ይሄን የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ካልተቀበልክ ሴም ካም(ኩሽ) ያፌት የሚለውን የነገድ ግንድ ክፍፍልም ልትቀበል አትችልም ማለት ነውና ኩሽ ሴም እያልክ ልታወራ የምትችለው ነገር የለህም ማለት ነው፡፡
አማርኛ ሴማዊ ቋንቋ እንደ ሆነ ልታረጋግጥልኝ ትችላለህ? ሴማዊ ነው እንዳትል ኩሻዊ ድምጾችም አሉት ኩሻዊ ነው እንዳትል ሴማዊ ድምጾችም አሉት ከሁለቱ ያልሆነ ድምፅም አለው፡፡ ለዚህም ነው ይህ ፍረጃ አማርኛን እንደማይመለከት ኢሳ.18 በመጥቀስ ለማስረዳት የሞከርኩት፡፡
ወንድም እምሳሉ፣ በውነት በኔ መታመም ተጨንቀህ ሳይሆን። ውሻታችሁ ታረታችሁ ስለ ተገለጠባችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የእስራኤል ታሪክ እንጂ የአንተ አማረው ታሪክ አይደለም። እማራ እስክ 9ኛው ክፍለ ዘመን በዘንዶ ያምን ነበር። ይህ ደግሞ በተክልሃይማኖት ገድል ውስጥ ተጽፈዋል። ሓይቅ ሂንና አጥና። በዚያው ደብተራነትህን ታጠናክራለህ። ስለሙሴ እኔ ከንተ ጽሁፍ በፊት ነው የማውቀው። ለምንጮቼም አትጨነቅ። እንዲያውም የሙሴ ታሪክ ሌላ ሆኖዋል። የእስራኤሎች ኣዶሎጂ ፉርሽ እያሆነ ነው። ከመጽሀፍ ቅዱስህ፣ እንድሜ ርቆ ሀደዋል። እናንተ ድፍን ቅል ስለሆነችሁ ነው። ኦሮሞም ሲዳአማ (አለት ድንጋይ) ያላችሁ። በአጠገብ የ 4 ሚሊዮን የ ሉሲ(ድንቅናሽ) ኣጥንት እያለ። ስለ 5500 እና የማይቀያራው ተረታችሁ 3000 ትነግራናለህ። የቀደምት ደብታሮች የአዙሪት በሽታ ስለአጠናወትህ የመዳን ተስፈህ የመነመነ ነው።እግረ ቆራጣው ተክለህይማኖት ከዘንድ መቀለብ ነጻ አወጣችሁ። እንዲያውም ወደ ስልጣን አመጣችሁ።”በላ 6 ክንፉ ሰው፣” ክክክክ ከአገዎ ጋር በተደረግ ጦርነት እግሩ የተቆረጣ። በድንብ አምብብ። አደረህን ትድን ይሆናል። ስለ አማሪኛ ቀላቶችህ ደግም፣ 40% የኩሽ ቃላቶች መሆኑን አውቃለሁ። 60% እራብኛ ነው። የኩሾች (አገው፣ ቤጃ፣ ቅማንት፣ ዳሞት፡ ኦሮሞ ወዘት) ቋንቋ የተወሰደ ነው። ወንድሜ አታበድ፣ ብዙ ኣምብብ። ስለ ግርዛትና፣ የሞታ ሰው ሁኔታ የወሰዳችሁ ከኛ ካኩሾች ነው። መጀመሪያ እብርሃም፣ ካዚያ ሙሴ፣ ከግብጽ ካዋጣ ከ40 ዓመት ብሗላ አስገራዛቸው። ከዚያ ዮሴፍ የእየሱስ እንጄራ አባት ተከተለ።
የኦሮሞ ግዝራት ከ እናንተ” ዘእም ነገደ የሁዳ” ዘሮች ንጉስ ሳይሆን ከጥንት ከኣባቱ ከከም/ኩሽ የወረሳና። በገደ ሥርዓት ጋር አቆራኝቶ ዛሬ የደራሰ ነው። መረጀውም፣ የእስክንዲሪያ ቤተ መጽሀፍ ኣጨናንቆ ይገኛል። የሙሴን ሌላ ጊዜ እልክልሃለሁ።
በሽተኛነትህን ትጠራጠራለህ? አሁን ጤነኛ የሆነ ሰው ይሄንን ይጽፋል? አምላክን ያዋረድክ መስሎህ ነው ክርስቶስን ማንቋሸሽህ? እራስህን ነው የዋረድከው በምሳሩ ላይ ብትቆም ለራስህ ይብስብሀል፡፡ አረማዊ ሆነህ ነው እንጅ እስላም እንኳን ብትሆን ይሄንን ያህል ልትዳፈር አትችልም ነበር ምክንያቱም እስልምና ኢየሱስን በድንግልና እንደተወለደና ነቢያቸው እንደሆነ ያምላሉና፡፡ ጤናውን ይስጥህ ወንድሜ ከበድ ያለ ችግር ነው ያለብህ፡፡
እውነት ነው አቡነ ተክለሃይማኖት ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ ናቸው እንዳልከውም በዘንዶ ያመልኩ የነበሩትን ሰዎች አሳምነዋል የዚያን ጊዜው ይገርምሀል እንዴ? አንተን ጨምሮ አሁን በዚህ ዘመን እግዚአብሔርን የማያመልከው ምን ያህሉ ነው? ዋርካን ወንዝን ሐይቅን ቃልቻን ወዘተ. የሚያመልከው አይበዛም ብለህ ነው? እናም በዚያ ዘመን በአንድ ጎጥ አካባቢ የነበሩ ሰዎች ዘንዶ ያመልኩ ነበር ቢባል አይድነቅህ እሽ? ደግሞ አማሮች ናቸው አይልም ይሄንን ያለው ያንተ ሐሰተኛ አንደበት ነው፡፡ የተጠቀሰው አካባቢ የአማራ ሀገር ነው ካልክም በአማራ ሀገር ስንት ጎሳ እንደሚኖር አታውቅም? እናም እነዚያ በአንድ ጎጥ ያሉ ሁሉንም ሊወክሉ እንደማይችሉ የራሳቸውን የቡነ ተክለሃይማኖትን ማንነት አይተህ ልታረጋግጠው የምትችለው ሀቅ ነውና በራስህ እፈር፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አቆጣጠር ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ አሁን 7506 ዓመት ነው በመባሉ አይድነቅህ የተሳሳተም አይምሰልህ፡፡ የዘመኑ አቆጣጠር ስላልገባህ ነውና አይገርመኝም በሰው ዘንድ አንድ ሽህ ዓመት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ አንድ ዕለት ናት ይላልና ለዕለቷም እዕት አለባትና የዘመኑ አቆጣጠር እንደዚህ ነው እሽ? ይሄ ወደ ሰውኛ አቆጣጠር ሲለወጥ ብዙ ቢሊዮኖች (ብልፎች) ዓመታት ነውና አትጨነቅ፡፡
ስለግርዛት እኮ ነገርኩህ አይገባህም እንዴ? ግርዛትን በመጠቀም ከዕብራዊያኑ እኛ እንቀድማለን ብየ፡፡ አንተ የኛ ነው ትለኛለህ በእርግጥ እን አገውና ቅማንትን የወሰድክ እንደሆነ አዎ ባሕላቸው ነው ኦሮሞን በተመለከተ ግን ከዐፄ ምንሊክ በፊት ሌሎቹ ነገሥታት ሊያስለምዱ ሲሞክሩ አልሆን ብሎ ዐፄ ምንሊክ በአዋጅ እንድትገረዙ ማድረጋቸውንና ከዚያ በኋላ መገረዝ መልመዳቹህን አታውቅም? የአክሱም ሐውልትን ስጠቅስልህ አንተ ደግሞ በኦሮሞ ባሕል ግንባራቸው ላይ የሚያደርጉትን የወንድ ብልት ጠቀስክና ባህላችን ነው ለማለት ዳዳህ፡፡ ባሕልህን አለማወቅህ ገረመኝ ከኦሮሞዎቹ ግንባራቸው ላይ ይሔንን ቅርጽ የሚያደርጉት እነማንና ለምን እንደነበረ አታውቅም? ያን ማድረግ የሚችል ኦሮሞ የወንድ ብልት የሰለበ ብቻ ነው፡፡ ወንድ አግኝቶ መስለብ ያልቻለ ያንን ነገር ግንባሩ ላይ ማድረግ አይችልም ነበር እሽ? ባሕልህል ንገረኝ ካልከኝ ይሄው ነው፡፡ የተገረዘ ብልት ቅርጽ መሆኑ የተሰለበው ማን እንደሆነ ሊጠቁምህ ይችላል፡፡ ሌላ ጊዜ ግን እባክህን አንዴ መልስ በሰጠሁህ ላይ እየደጋገምክ አትጠይቀኝ ሰው ይታዘብሀል ጭንቅላትህን ክፍት አድርገውና የሰጠውህን መልስ በአስተውሎት አንብብ እሽ?
የኔ ወንድም ብዙ መዘባረቅ አያስፈልግም ወይ ኢትዮጵያዊ ነህ ወይ አይደለህም! ሐበሻ ፈላሻ ዓጋዘን ምን አመጣው? ሐበሻ የሚለው ቃል መሰረቱ ኢትዮጵያዊ
ሳይሆን ከደቡብ አረብ ነው። በአንዳንድ የአረብ ሃገሮች ውስጥ ትርጉሙ ድቅል ወይም ክልስ እንደማለት ሲሆን ሌሎች መረጃዎች ደግሞ ሐበሻት የሚባል ጎሳ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ፈልሶ ከኢትዮጵያውያን ጋር በመደባለቁ ሐበሻ የሚባለው ቃል የመጣው ከዛ ጊዜ ጀምሮ ነው ይላሉ። የአክሱም ነገሥታት ድንጋይ ላይ በቀረጹት ፅሁፋቸው እራሳቸውን የአክሱማውያን ሲሉ በሚገዙዋቸው ጎሳዎች ስም የኖባ ንጉሥ፣ የብሌሚ ንጉሥ፣ የሐበሻ ንጉሥ እያሉ ጽፈዋል።
በአሁኑ ዘመን ግን ሐበሻነት ፀረ-ኢትዮጵያዊ ideology እንጂ identity አይደለም አንዳንድ እውቀት ያነሳቸው enlightened ያልሆኑ inferiority complex የሚያጠቃቸው ወገኖች ከጥቁርነታቸው(ኢትዮጵያዊነታቸው) ለመሸሽ ሐበሻ የሚለውን ቃል በኢትዮጵያዊነት(ኩሻዊነት) ፋንታ ለመተካት ሲፍጨረጨሩ ይስተዋላሉ። የዛሬ ፫ሺሀ አመት የተደረገውን የዘር መዳቀል እያነሳ ዲቃላ ነኝ ሴማዊ ነኝ እያለ የሚፎክር ህዝብ ከኛው በቀር የትም ቦታ አይገኝም! ትላንት ከኬንያዊ አባት እና ከነጭ እናት የተወለደው ባራቅ ኦባማ እንኳን በጥቁርነቱ የሚኮራ ነው ዓለምም የሚያውቀው በጥቁርነቱ ነው። ለምን ቢሉ “ኩሻዊ ቁርበቱን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ፍፁም አይለውጥም” ብሏል ነብዩ ኤርሚያስ።
የኛዎቹ “ሴማውያን” ግን ወደ እውነተኞቹ ሴማውያን ሃገር ሲሄዱ ነው ማንነታቸውን የሚረዱት። አረብ ሃገር አቢድ(ባርያ) እየተባለ ወንዱና ሴቱ የሚደፈረው ተዘቅዝቆ የሚገረፈው ይባስ ተብሎ ይህ ውርደት በቪድዮ ተቀርፆ online የሚለጠፈው ያው የኛው ጉድ ነው። እስራኤል ውስጥ ያሉት አይሁድ ነን የሚሉት ፈላሻዎች እንኳን “ኩሺም”(የኩሽ ዘሮች) እየተባሉ ነው የሚጠሩት። ቁጥራቸው እንዳይጨምር
ሴቶቻቸውን clinically sterilize ማድረግ የእስራኤል መንግስት የተለመደ ተግባር ነው።
መቼስ የሃገሬ ሰው ነጮች የፃፉት ነገር ሁሉ እንደ ሙሴ ፅላት ከሰማይ የወረደ ነው የሚመስለው።Nilo-Saharan Semitic Cushitic የሚል መደብ ያመጡት አውሮፓውያን ሊንግዊስቶች ከ ፩፱ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነው። አውሮፓውያን ደግሞ ማንኛውንም ነገር ሲሰሩ ጥቅማቸውን ከእውነትም በፊት ቢሆን ያስቀድማሉ፤ አይፈረድባቸውም አንድን አህጉር ለመግዛት ታሪክን ማንሸዋረር ህዝብን ባለ በሌለ ነገር መከፋፈል ግድ ነው። ነገ ከየሃገሩ የተውጣጡ የአፍሪካ ምርጥ ምሁራንና ሊንግዊስቶች ታሪካችን፣ ቋንቋዎቻችን ላይ አዲስ ጥናት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
የአውሮፓውያን ሊንግዊስቶች ጥናት በአብዛኛው biased እና deliberately የተሳሳተ ነው። ለምሳሌ በዚህ አመዳደብ የሚያምኑ ኦሮሞዎች፣ሶማሌዎች….ቋንቋቸው
Cushitic ሰለተባለ ኩሻዊነት ለነሱና በነሱ ምድብ ላሉት ብቻ የተወሰነ ይመስላቸዋል። ነገር ግን በቅዱስ መፅሃፍ እና አያሌ ጥንታዊ መዛግብት የተጠቀሱት ኩሻውያን ነገሥታት ከ Nilo-Saharan ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚመደቡ የዛሬዋ ሱዳን ተወላጆች ነበሩ። ሌላ ምሳሌ:- Semitic የሚባሉት የዕብራይስጥና አረብኛ ቋንቋዎች መሰረታቸው ሙሉ በሙሉ cannanite (ከነዓናዊ) ሲሆን ማንም እንደሚያውቀው ደግሞ ከነዓናውያን የካም ዘሮች ነበሩ። ዛሬ አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት ፊደል ላቲን፤ ሮማውያን ከግሪኮች ግሪኮች ደግሞ ከከነዓናውያን የተዋሱት ካማዊ ፊደል ነው።
ኢትዮጵያን የሚያህል ትልቅ ስም ሐበሻ በሚል ተራ የውርደት ስም ሊተካ አይችልም
ሊዛባ አይችልም። ኢትዮጵያዊነት ፈጣሪ የለኮሰው የማይጠፋ እሳት ነው! ኢትዮጵያዊ በ፺፬ ሚሊዮን የሚወሰን ህዝብ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ኩሻዊነት ነው፤ ጥቁር ህዝብም ሁሉ የኩሽ ዘር ነው። ኢትዮጵያ የሚለው ቃል መስረቱ ግሪክ ትርጉሙም “ጥቁር ሰው” ማለት ሲሆን ግሪኮች የተለያዩ ቋንቋና ባሕል ያላቸውን ጥቁር አፍሪካውያንን በሙሉ Aethiop ብለው ሲጠሩ እነሱ የሚኖሩበትን የአፍሪካ ክፍል በሙሉ Aethiopia በማለት ይጠሩ ነበር። ሰባው ሊቃውንት በፕቶሎሚ ትዕዛዝ ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ሲተረጉሙ ኩሻውያን የሚለውን “ኢትዮጵያውያን” የኩሽ ምድር የሚለውን “ኢትዮጵያ” ብለው ተርጉመውታል።
ድሮስ መፅሃፍ የገለጠ ሰው ይሀን ሁሉ መቼ አጣው፤ ሥልጣኔስ ከተባለ የኩሽ ልጆችን ማን ይቀድማቸዋል በ ናይል ቫሊ ብቻ ሳይሆን በኤፍራጥስ ዳር mesopotamiaን፣ ነነዌን፣ ኤላምን የገነቡት እነማን ናቸው? የዛሬ 7500 ዓመት በ ta-seti የነገሡ በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ነገሥታት እነማን ነበሩ? የሴም ዘሮች ከብት ሲጠብቁ የያፌት ዘሮች አውሮፓውያን የሰው ሥጋ ሲበሉ የኩሸ ዘሮች በዙፋን የተቀመጡ ህግ፣ መንግሥትና አስተዳደር የነበረን ሥልጡን ህዝቦች ነበርን። ወደፊትም ዓለምን የሚያስደንቅ ሥልጣኔ ከኛው ይወጣል ዋናው አንድነት ነው። እኔ ቤተሰቦቼ አብዛኛዎቹ አማራ(ጎንደሬ) ሲሆኑ ጉራጌ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬም አለብኝ ሐበሻነትን ግን ነፍሴ ተቀብላው
አታውቅም ለኔ ስድብ ነው ኩሻዊነት ግን ክብሬ ነው። በኦሮሞ፣ በአማራ፣ በሐበሻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን እጅ ስትገባ ያኔ መልካም ቀኖችን እናያለን!