ባለፈው ሰሞን አንድ ከ “ሰማእታት” የመታሰቢያ ሐውልቶች ጋር በተያያዘ ታሪክ ቀመስ ጽሑፍ መጻፌ ይታወሳል "አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል" እንዲሉ ይህ ጽሑፍ ለንባብ ከበቃ በኋላ በፊት ለምን እንደሆነ በቅጡ የማይገቡኝ የነበሩ እጅግ የሚገርሙ ነገሮች ለምን ይደረጉ እንደነበር ከተለያየ አቅጣጫ በአካልና በመልእክት ካገኘኋቸው ግብረ መልሶች ተረዳሁ፡፡ በዚያ ጽሑፍ ላይ ኦሮሞና ትግሬ ነን የሚሉ ካድሬዎች በተለየ ሁኔታ ትኩረታቸው ተስቦ ነበር፡፡ አንዳንዶችም አነጋግረውኝ ነበር፡፡ በንግግራችን ውስጥ ከዚህ በፊት ያልተረዳኋቸው ነገሮች ግልጽ ሆኑልኝ፡፡ ለነገሩ ያልተረዳኋቸው ማለት ይከብዳል ነገሩ እጅግ የማገርምና ለማመንም የሚቸግር በመሆኑ ሁል ጊዜ እንግዳ ሰለሚሆንብኝና ለጉዳዩ ሁሌም አዲስ እንግዳ ስለሚያደርገኝ ነው፡፡ ባይሆን ስጠረጥራቸው የነበሩ ብል ይሻል ይመስለኛል፡፡ እናም እጅግ ገረመኝ … [Read more...] about ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል
Archives for June 2014
ቅድመ ምረጫ 2007 እና የተቋሚዎች እጣ ፋንታ
መቼም የምርጫ ነገር ሲነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የጎላ ቀለም ያለው ምርጫ 97 ነው:: ምክንያቱም ከዚያ በፊት የነበሩት ምርጫዎች በኢህአዲግም ሆነ በደርግ መንግስት የነበሩት የይስሙላ ምርጫዎች ነበሩ:: ምርጫ 97ም ቢሆን የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት በአዲስ አበባ እስከ ምርጫው እለት ሲሆን በክልሎች ግን ምርጫው አንድ ወር እስኪቀረው ነበር በክልሎች ገዝው ኢህአዲግ ቀሪውን አንድ ወር አፈናውን እናወከባውን አጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ አልፎ አልፎ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ባሉበት ክልል ግድያም ይፈፅም ነበር:: (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) hoppytesfa@gmail.com … [Read more...] about ቅድመ ምረጫ 2007 እና የተቋሚዎች እጣ ፋንታ
ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በአገር ውስጥ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና አግባብ አላቸው ለሚሏቸው አካላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተቀምጠው እንዲመክሩ ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ ኢህአዴግ በውስጥ ችግሩ፣ በውጭ ተጽዕኖ ወይም በፖለቲካው የተፈጥሮ ባህርይ የሚከስምበት ደረጃ መድረሱን ያሳሰበው በ"ጥቁሩ ሰው" ኦባንግ ስምና ፊርማ የተበተነው የአኢጋን ደብዳቤ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥብበው እንዲሠሩ ጠይቋል፡፡ ይህንን ለኢትዮጵያና ለሕዝባቸው ሲሉ መሥራት የማይችሉ ከሆነ ከኢህአዴግ በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡ የፖለቲካ ዕርቅ በመጀመሪያ በተቃዋሚዎች ደጅ ሊተገበር እንደሚገባው ያሳሰበው አኢጋን፤ ይህንኑ ዕርቅ መሠረት በማድረግ ወደ ኅብረት እንዲመጡ በደብዳቤው ገልጾዋል፡፡ ወደ ኅብረት ሲመጡ የፖለቲካ ሥልጣን … [Read more...] about ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ
የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር (ክፍል 1)
የሰው ልጆች አብረው በማህበረሰብ ለመኖር ይቻላቸው ዘንድ ለአብሮ መኖር ፀር የሆኑ ምግባሮችንና ባህሪዎችን ማስቀረት መቻል አለባቸው። አለበለዚያ ማህበራዊ ኑሮ ሊታሰብ አይችልም። ሰውን ከእንሰሳ የሚለየው ከስሜት ባሻገር የማሰብና የማመዛዘን ክህሎቱ ነው። ህሊና አንድ ሰው በጎና ክፉውን፤ መጥፎና ጥሩውን፤ ትክክለኛና ሃሰተኛውን ነገር ለይቶ እንዲያውቅ የሚያስችለውን ችሎታ ወይም ክህሎት አመልካች ነው። የሰው ልጅ የማሰብና የማሰላሰል ልዩ ችሎታ ስላለው በሚኖርበት ማህበራዊ ስፍራ የሚከሰቱትን ነገሮች ሊገነዘብና ሊዳኝ ይችላል። ልጅ ሲያድግ በጎውና ክፉውን እየለየ የሚያውቀው ከአሳዳጊ ቤተሰቦቹ፣ ከጎረቤቱ፣ በሚኖርበት አካባቢ ከሚገኙ ሰዎች፣ ተቋሞች፣ ትምህርት ቤት፣ መስጊድ፣ ቤተ ክርስቲያን ወዘተ ነው። የህሊና ዳኝነትና ለሱ መገዛት መቻል የአንድን ሰው ነፃ መሆንና በራሱ ነፃነት በጎና … [Read more...] about የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር (ክፍል 1)
የማህፀን ኪራይ ክፍያ 500ሺ ብር ደርሷል
ፈላጊና ተፈላጊን የሚያገናኙ ደላሎች እስከ 60 ሺህ ብር ኮሚሽን ይከፈላቸዋል ባሎቻቸው ሳያውቁ በውጭ አገር ማህፀን አከራይተው የተመለሱ ሴቶች አሉ ማህፀን ማከራየትም ሆነ መደለል ህገወጥ ነው - የህግ ባለሙያ ማህፀን ለመከራየት ከአሜሪካና ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለትዳሮች በመበራከታቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደተስፋፋ ደላሎች የተናገሩ ሲሆን፤ የማህፀን ኪራይና የማህፀን ኪራይ ድለላ ህገ-ወጥ እንደሆነ የህግ ባለሙያ ገለፁ፡፡ የዛሬ 3 ዓመት ወደ ህንድ ሄዳ የማህፀን ኪራይ አገልግሎት እንደሰጠች የተናገረች አንዲት ወጣት፤ የ11 ወር ወጪዋ ተችሎ 250ሺ ብር እንደተከፈላት ገልፃለች፡፡ አሁን ክፍያው በእጥፍ አድጐ 500ሺ ብር መድረሱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የማህፀን አከራይዋንና ተከራዮቹን የሚያገናኙ ወኪሎች፤ክፍያው ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ … [Read more...] about የማህፀን ኪራይ ክፍያ 500ሺ ብር ደርሷል
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ "የእንዳልካቸው አባት የእንዳልካቸው ልጅ መውለድ አስተካክሎ እንደዚህ ነው እንጂ" በማለት አዝማሪ የገጠመላቸው ቢትወደድ መኮንን ማለት እኚህ ናቸው እኚሁ ትልቅ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ መጽሐፍትን የጻፉም ነበሩ። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ?
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ታላቅ የሕዝብ ቅልቅል ተካሂዷል። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፦ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በዘመነ መሣፍንት የነበሩት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ ፈፃሜ-ዘመነ መሣፍንትን ያበሠሩት የማዕከላዊ መንግሥትን እንደገና የማዋቀር ጦርነቶች እንዲሁም ሁለቱ የኢጣሊያ ወረራዎች የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚያ ጦርነቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሕዝብ ክፍል ሕይዎት እንዳሣጡ አይካድም። ያንንም ተከትሎ ከኑሮ አስገዳጅነት እና በአገዛዝ ኃይሎች የበላይነት የያዘው አካል በሚፈጥረው የፖለቲካ አሠላለፍ መለዋወጥ ምክንያት የአንዱ ጎሣ ወይም ነገድ አባሎች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች እና ጎሣዎች መካከል፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪ … [Read more...] about በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ?
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?
መለስ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ “የጅራፍ ድምጽ እንኳን አይሰማም” በማለት ሲመጻደቁበት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በ"ወረራ" እና "ወረራን መቀልበስ" በሚል ድራማ ተጀምሮ ከተቋጨ አስራ አምስት ዓመት አልፎታል። ኢህአዴግና ሻዕቢያ ጉዳያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ወይም በጡንቻ መቋጨት ያልቻሉበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን አለ። ሁለቱም ወገኖች ድንበር ላይ ወታደር አፍስሰው መቀመጣቸውን አስመልከቶ "አውቀው ነው" ከሚለው ውሃ የማይቋጥር አስተያየት ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በገሃድና በሹክሹክታ ሲሰማ ቆይቷል። የጎልጉል የዜና ምንጮች ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የላኩት መረጃ ግን በይዘቱ የተለየ ነው። ይህንኑ አዲስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያት እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ዜናው ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ አትመነዋል። የድንበር ውዝግቡ አንዲቋጭ … [Read more...] about የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?
“አባ” ግርማ! እንኳን ለግንቦት ፳ አደረሰዎ!
ወያኔ አሁን ደኅና ልማታዊ መነኵሴ አገኘች! ጎሽ! የለንደኑ ኤምባሲዋ፣ አዲሱን ወዶ-ገባ ለግንቦት ፳ አሰልጥና አስመረቀች! በድንኳን ባደረገቸው ድግስ ላይ በግልጽ ለዕይታ አበቃች። ማብቃቷንም በራሷ የሚዲያ መረብና እና በዓይጋ ድረ-ገጿ በተነች። “አባ” ግርማ፣ የለንደኗን ርዕሰ አድባራት ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሕንጻና ንብረቷን፣ እጅ መንሻ አድርገው በማቅረባቸው፣ አሁን የወያኔ ባለውለታ አሽከርነታቸውን አረጋገጠዋል። እንዲያ ነው እንጂ! ማጥ ውስጥ ከወደቁ አይቀሩ በቅጡ መንከባለል ይሻላል። ለወያኔ አድረዋል ስንል፣ “ስም አጥፊዎች” ተባልን። አሁን ደጋፊዎቻቸው ምን ይበሉ? በየሳምንቱ፣ የጥበቃ ዘበኞችን ቀጥራ ስታስጠብቃቸው የነበረችው በከንቱ አልነበረም። በነዚህ ፈርንጆችና ሶማሌ እንግዶች መሀል የሚታዩት ሁሉቱ ከሀዲ ግርማዎች ናቸው - ግርማ ከበደና፣ ግርማ ቡፋ … [Read more...] about “አባ” ግርማ! እንኳን ለግንቦት ፳ አደረሰዎ!
የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…
ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡ ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት … [Read more...] about የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…