ባለፈው ሰሞን አንድ ከ “ሰማእታት” የመታሰቢያ ሐውልቶች ጋር በተያያዘ ታሪክ ቀመስ ጽሑፍ መጻፌ ይታወሳል “አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” እንዲሉ ይህ ጽሑፍ ለንባብ ከበቃ በኋላ በፊት ለምን እንደሆነ በቅጡ የማይገቡኝ የነበሩ እጅግ የሚገርሙ ነገሮች ለምን ይደረጉ እንደነበር ከተለያየ አቅጣጫ በአካልና በመልእክት ካገኘኋቸው ግብረ መልሶች ተረዳሁ፡፡ በዚያ ጽሑፍ ላይ ኦሮሞና ትግሬ ነን የሚሉ ካድሬዎች በተለየ ሁኔታ ትኩረታቸው ተስቦ ነበር፡፡ አንዳንዶችም አነጋግረውኝ ነበር፡፡ በንግግራችን ውስጥ ከዚህ በፊት ያልተረዳኋቸው ነገሮች ግልጽ ሆኑልኝ፡፡ ለነገሩ ያልተረዳኋቸው ማለት ይከብዳል ነገሩ እጅግ የማገርምና ለማመንም የሚቸግር በመሆኑ ሁል ጊዜ እንግዳ ሰለሚሆንብኝና ለጉዳዩ ሁሌም አዲስ እንግዳ ስለሚያደርገኝ ነው፡፡ ባይሆን ስጠረጥራቸው የነበሩ ብል ይሻል ይመስለኛል፡፡
እናም እጅግ ገረመኝ በእርግጠኝነት እንደኔ ሁሉ ብዙው ሰው የሚደረጉ ነገሮች ዓላማቸው የገባው አይመስለኝም፡፡ ወያኔ ለካ አማራን እንዳያንሠራራ አድርጌ ሠብሬዋለሁ እንዳይነሣ አድርጌ አድክሜዋለሁ ብሎ ያምን ኖሯል፡፡ መቸም ሥራቸውን ያውቃሉና ነው እንዲህ ሊያስቡ የቻሉት፡፡ ለካ እንዲያው ሳናውቀው ገለውናል ጃል! ታዲያ እላቹህ እንዲህ ብለው እያሰቡ እያመኑ እያለ ይህ ጽሑፍ በዚያ ቅኝትና ይዘት መጻፉ አማራን በተመለከተ የነበራቸው ግምትና እምነት እንዳሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ከ 20ዓመታት ቅጥቀጣና ድቆሳ በኋላ እንደነሱ አባባል እንደዚህ ዓይነት ጽሑፍ በእኔም ብቻ ሳይሆን ከእኔም በኋላ በሌሎች ወገኖችም በአጋጣሚ ተከታትሎ በአንድ ሰሞን በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች መንጻባረቁና በአንባቢያን መወደዱ ለመግለጽ እጅግ በሚያስቸግር የመደነቅ ድባብ ውስጥ ከቷቸው ነበር፡፡
ይሄን ሁሉ ጉድ የማላውቀው የዋሁ የእግዚአብሔር በግ እኔ ደግሞ መደነቅ መገረማቸውን ሳይ እንዴ ይሄም ኖሯል ለካ ብዬ ሁኔታቸውና አስተሳሰባቸው ሁሉ እኔንም በተራዬ ከከባድ ድንጋጤ ጋር እጅግ እጅግ እጅግ አስደነቀኝ አስገረመኝ አዘንኩም፡፡ እንዲያው ሰው በተለያየ ምክንያት ዝም ሲል ጊዜ እጅ ሰጥቶ ተንበርክኮ መሰላቸውና ጭራሽም እንደሞተ ያህል ቆጥረውት ቁጭ አሉ፡፡ ወያኔ አማራን በተመለከተ አይቅበሩት እንጅ እንደሞተ እንዳበቃለት አድርገው ማሰባቸው ስሕተት እንደነበረ ከመጸጸት ጋር ይቆጩ ይዘዋል፡፡ እነሱ ዘመትንበት አጥፍተነዋል ያሉት ይህ ለሀገር፣ ለቅርስ፣ ለታሪክ፣ ለመለያ፣ ለማንነት፣ ለሃይማኖት ተቆርቋሪ የመሆንን ስሜት ወዴት ተደብቆ እንደተረፈ በአንከሮ እያጠኑት ይገኛሉ፡፡ በተለያዩ የብዙኀን መገናኛች ለመረዳት እንደቻላቹህት ማኅበረቅዱሳን አንዱ መደበቂያ መሸሸጊያ ነው ብለው በማመናቸው ማኅበሩን ለማፍረስ ለመዝጋት ሴራ እየጠነሰሱ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ማኅበር ከዚህ ቀደምም ቢሆን በወያኔ የዓይነ ቁራኛ የቅርብ ክትትል ስር የነበረ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩን አቅጣጫውን ለማሳትና ወደ ሚፈልጉት መንገድ ለመውሰድ በርካታ ጥረቶችን ሲየደርጉ ቆይተዋል፡፡
በየዓመቱ ከየዩኒቨርሲቲው (መካነ-ትምህርት) ተመርቀው የሚወጡትን የማኅበረ ቅዱሳንን የግቢ ጉባኤ አባላት እንደ ማንኛውም ተመራቂ ሁሉ ወያኔ የድርጅቱ አባል አድርጎ እያወጣ ማኅበረ ቅዱሳንን በአባላቱ ጠቅጥቆ ቢሞላውም ማኅበሩ ሃይማኖታዊ ማኅበር ከመሆኑ አኳያ እነኝህ የወያኔ አባላቶችም ከሃይማኖታቸው ይልቅ ወያኔ በሚፈልገው መጠን ለመርሑ ታማኝ ሆነው ባለመገኘታቸውና ምቹ ሁኔታ ስላላገኙ ወያኔ የሚፈልገውን ውጤት በሚፈልገው ፍጥነት ማስመዝገብ አልቻሉም፡፡ ከዚህ ሙከራ ክሽፈት በኋላ ወያኔ ማኅበሩን በአክራነትና በአሸባሪነት ከሶ ያለ ማፍረስ የተሻለ አማራጭ እንደሌለ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ከወጡ መረጃዎች መረዳት ተችሏል፡፡ እንግዲህ ወያኔ ይሄንን ሳይጣናዊ ምኞትና ሐሳብ ለማሳካት በአዲስ ጉልበትና ስልት (strategy) ሊዘምትብን እንደሆነ ግልጽ ሆኗል ማለት ነው፡፡
እንዳስተዋላችሁት ወያኔ ታሪካዊ ለሆነ ቀደምት የሀገራችን እሴቶች ጨርሶ ትኩረት አይሰጥም፡፡ የመንግሥት (የሕዝብ) የብዙኃን መገናኛዎች ከመጀመሪያው ጀምሮ በዚሁ ቅኝት እንዲሠሩ ተደርጓል፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በየዩኒቨርስቲው የአማራ አሻራ ይጎላበታል ያሏቸውን ቋንቋን ታሪክን ባሕልን ሥነ-ኪንን የተመለከቱ ዲፓርትመንቶችን (ከፍለ ጥናቶችን) አከታትለው ዘግተዋቸዋል፡፡ እነኝህ እኩይ እርምጃዎች የተወሰዱት በአጋጣሚ ወይም ከተራ ጥላቻ የተነሣ አልነበረም፡፡ እኔ እንደዛ ይመስለኝ ነበር እኔ ብቻም አይመስለኝም ብዙው ሰው እንደዚህ ይመስለዋል ብዬ እገምታለው፡፡ ነገሩ ለካ ከዚያም የከበደ ጫን ያለ ኖሯል፡፡ ለካ እነኝህ ስንት የተደከመባቸው ስንት መሥዋዕትነት የተከፈልንባቸው የሀገራችን እሴቶች ከነአካቴውም የእሱ ሀብት ነው እሴቱ ነው ከሚሉት ብሔረሰብ አባላት ልብ ዘንድም ሳይቀር እንዲደመሰስ፣ እንዲጠፋ፣ እንዲረሳ ይፈልግ ኖሯል ለካ!
ይሀንንም የጥፋት ዓላማ ለማሳካት ኖሯል ለካ ከትምህርት ሥርዓቱ እስከ ባሕላዊ ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን አትኩረው በሚሠሩ ተቋማትም ዘንድ ምክንያቱ ሳይገለጽልን ቦታ እንዲያጡ እንዲገለሉ እንዲወገዱ የተደረገው፡፡ ወያኔ ይሄንን የጥፋት ውጤት ለማስመዝገብ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ እሴቶቻችን በመጥፋታቸው ከሚደርስብን የጀርባ አጥንት ሥብራት ጉዳት በተጨማሪ በዘመኑ ሁሉ ይሄንን ለማድረግ ምን ያህል እንደደከመ፣ ምን ያህል አቅሙን እንዳባከነ፣ ምን ያህል የመንግሥትን ወይም የሕዝብን የገንዘብ የጊዜ የጉልበት ወዘተ. ሀብቶችን እንዳባከነ እንዳከሰረና ያን ሁሉ ዘመን በዚህ እኩይ ሥራ ተጠምዶ ይሄን ሁሉ ጉዳት ኪሳራ ለማስመዝገብ ባባከነው ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ጥረት፣ ወዘተ. ሀገርንና ሕዝብን ለሚጠቅም፣ ለሚያንጽ፣ ለሚገነባ ጉዳይ አውሎት ቢሆን ኖሮ የት ልንደርስ እንችል አንደነበረ ሳስበው ውስጤ እንደ እሳት በሚገርፉ ቁጭት ይቃጠላል፡፡
ከዚህ በላይ የእግር እሳት ሌላ ምን አለ ወገኔ? “ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል” አለ የሀገሬ ሰው፡፡ ተበድሮ ሲበላ ከርሞ መኸር ደረሶ ሰብሉን አጭዶ ከመረና ሲያልፍ ሲያገድም ከርቀት በኩራት ጉም ብላ ትታየዋለች ያኔ እየተበደረ ሲበላው የከረመው እህል ታወሰውና ክምሩን “አየ አንች ክምሬ ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል” ሲል በኃዘን ተናገረ፡፡ ለካ የአማራ ሕዝብና እሴቱ ያለ ይመስለናል እንጅ አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ለካ 23 ዓመታት ሙሉ ጉዱን አያውቅ እሱ የሚጠፋበት መንገድ ተቀይሶ እላዩ ላይ የጥፋት ሥራ ሲሠራበት ነበር የባጀው? ” ጉድ ሳይሰማ አሉ” እኮ በል ተጠየቅ ወያኔ የእፉኝት መንጋ ለምን? እኮ ለምን? ይሄ ነው እንዴ በይነ ሕዝብ? (ዴሞክራሲ?) ይሄ ነው እንዴ የብሔር ብሔረሰቦች መብት? ለካ እነዚህ ድንጋጌዎችህ ማጃጃያዎችህ ኖረዋል ለካ? ጭራሽም ልታጠፋን ትጥራለሃ ለካ? “የጊዮርጊስን ግብር የበላ ለፍልፍ ለፍልፍ ይለዋል ምን ነውሳ እኔን አያስለፈልፈኝ” አለ አሉ አንዱ እየለፈለፈ መሆኑን ሳያውቅ፡፡
ለካ በብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር አማራንና ኦርቶዶክስን አዳከምነው ተብሎ መፎከሩ ለዚህ ነው? በጣም የሚገርመው ቤተክርስቲያንንም የነፍጠኛ ሃይማኖት ብሎ በመፈረጅ የጥቃቱ ሰለባ አድርጓት መቆየቱ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአንድ ጽሑፍ ላይ እንዳነሣሁት ወያኔ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የአማራ የህልውና መዋቅር አድርጎ ነው የሚቆጥራት ጥርሱን ነክሶ ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት ሲሠራ የኖረውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ አባ ጳውሎስ የተባሉ ሰው አስቀምጠው ከአንድ አረማዊ እንኳን በማይጠበቅ ድፍረትና ጭካኔ የቤተክርስቲያኗን ሥር ሲቆርጥ መኖሩ የሚታወስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ታላቅና ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ነው፡፡ የእኒህን ሰው እርኩሰት አስከናቸው ባረፈበት ቦታ ሳይቀር በሚያሳየው ተአምር እየገለጸ ነው፡፡
ይሄንን ታውቁ ኖሯል ወገኖቸ? ለካ “የአንድ ብሔረሰብን ባሕል፣ ማንነት፣ ሃይማኖት፣ እሴት አስተሳሰብ በሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ለመጫን ነው ገዥዎች ሲጥሩ የኖሩት” እየተባለ በቁጭት ሲነገረን የኖረው ሠም ለበስ አነጋገር ኖሯል? ወርቁ ለካ የዚህን ብሔረሰብ ባሕል፣ ማነነት፣ አስተሳሰብ ወዘተ. ከዚህ በኋላ ማየት አንፈልግም የሚል ኖሯል ለካ? ለካ ለዚህ ነው ካድሬዎቹ ከዚህ በኋላ አማራዊት ኢትዮጵያ አትኖርም እያሉ የሚፎክሩት? እጅግ ደግሞ የሚገርመኝ ብአዴን ተብሎ በአማራ ብሔረሰብ ማኅበር ስም ለአማራ ሕዝብና እሴት ሊሠራ በተደራጀው የኢሕአዴግ አጋር ድርጅት ተቋቋመ ተብሎ በውስጡ ያሉ የአማራ ተወላጅ ነን ባዮች ይሄንን ናዚያዊ አስተሳሰብ እምነውበት የገዛ ሕዝባቸውን የገዛ ወገናቸውን እና እሴቱን እንዲያጠፋ እንዲደመስሱ ወያኔ ብዙ የሚጠብቅባቸው ከአማራ የወጡ መሆናቸው ነው፡፡
ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ናቸው? እንደኛ ይናገራሉ? እንደ ሰው እጅና እግር ዓይንና ጆሮ ያላቸው የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ናቸው? እውን ከአማራ ሕዝብ የተገኙ የወጡ ናቸው? አይገረማቹህም አይደንቃቹህም? ከዚህ የተነሣ ነው ለካ አማራነታቸውን (ከሆኑ) ጨርሰው እረስተውት “አማራ” እያሉ ጨርሶ የማይገባውን ዘለፋ በአደባባይ ሲዘልፉት ሲያዋርዱት ቅንጣት ታክል የማይሰማቸው፡፡ አሁን እነዚህ ሰለ እውነት ሰዎች ናቸው? የሰው ጭንቅለት አላቸው? ለማይሞላው በቃኝን ለማያውቀው ሆድ ብለው? እንደ እንስሳ? ሰው እንዴት የገዛ ራሱን ልዩና ባዕዳንን ሁሉ በእጅጉ የሚያስቀና ማንነቱን እሴቱን ሀብቱን እንደሰው ለምን እንዴት ብሎ ሳይጠይቅ በገዛ አንደበታቸው የሚናገሩትን ገደብ የለሽ የብሔር ብሔረሰብ መብት ተላልፈው፣ እራሳቸውን ከሰውነት ወደ ውሻነት አውርደው ቻዝ እንደተባለ ውሻ እንዴት ያለ አግባብ በገዛ ማንነታቸውና ሕዝባቸው ላይ የጥፋት ሰይፋቸውን መዘው ይዘምታሉ?
አሁን እነዚህ ሰዎች ናቸው? አሁን እነዚህ የሰው ጭንቅላት አላቸው? አፈር ያስበላችሁ በሉልኝ በቁማቹህ የሞታቹህ ናቹህ፣ በቁማቹህ የበከታቹህ በክቶች ናቹህ፣ በቁማቹህ የበሰናቹህ ብስብሶች ናቹህ እንስሳ የሚጥለውን እዳሪ እበት ፋንድያ ቁረን በጠጥን የሚያህልን እንኳን ዋጋ እርባና የሌላቹህ በድኖች ናቹህ በሉልኝ፡፡ ከእናንተ የተወለዱት ልጆቻችሁ ከእናንተ የተለዩ ሊሆኑ የሚችሉበት ተአምራዊ ዕድል ይኖር ይሆን? ለነገሩ እበት እዳሪ አዛባ ትልን እንጅ ምን ይወልድና፡፡ እውነት ይሄ ሁሉ ጉድ በእውን አይደለም በሕልም እንኳን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል? ጭራሽ እኔ ይደንቀኝ የነበረው ወያኔዎች እንዴት ግን ኢትዮጵያዊያን ሆነው ሳለ የጠላት ቅጥረኛ ሆነው በገዛ ሀገራቸው እሴት ላይ ጠላት ሊሆኑ ቻሉ? እያልኩ እድሜ ልኬን ሲገርመኝ የፈጣሪ ነገር ጭራሽ የባሱ አሉልህ ብሎ ይሄንን ያሳየኝ? ይሄንን ያሰማኝ?
“የአማራ ህዝብ ባሕል፣ አስተሳሰብ፣ ማንነት፣ ሥልጣኔ ወዘተ. በተቀረው ሕዝብ ላይ እንዲጫን አንፈልግም ” ነው ያላቹህት? እኮ ለምን? ሲጀመር “የኢትዮጵያ” ተብሎ የሚጠራው የሚታሰበው ባሕል፣ አስተሳሰብ፣ ማንነት፣ እሴት የአማራ ህዝብ ብቻ ነው ወይ? በራሱ ሂደት ከሌሎቹም ብሔረሰቦችም መልካም መልካም የተሻለ የተሻለውን ተሞክሯቸውን መርጦ፣ እራሱን የቀረጸ የገነባ አይደለም ወይ? ደናቁርት ሆይ! ደዳብት ሆይ! ምንም ነገርን ከማንም ሳይወስድ የራሱን ብቻ ባሕል በሉት አስተሳሰብ ቋንቋ ባሉት ምን ይዞ እንደ ደሴት እራሱን ነጥሎ ብቻውን የኖረና የሚኖር ብሔረሰብ ከኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ከመላው ዓለም አንድ ብሔረሰብ በሉት ጎሳ አንድ ብቻ እንኳን ልትጠቅሱልኝ ትችላላችሁ? አማራ የመሪነትን ሚና እንደመጫወቱ ከሌሎቹ ወገኖቹ ኋላ ቀር አስተሳሰቦችን እንዲተውና የተሻውን፣ የበለጠውን፣ የላቀውን አስተሳሰብ እንዲጨብጡ ማድረጉ፣ መጣሩ፣ ማሠልጠኑ ኩነኔው፣ ኃጢአቱ፣ ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው? ሥልጣኔ እንዴት ሆኖ የተስፋፋ ነው የሚመስላቹህ? ጠቃሚና የተሻሉ አስተሳሰቦችን፣ ተሞክሮዎችን ልምዶችን አንዱ ከሌላው በመውሰድ ያንንም ሥራ ላይ በማዋል አይደለም ወይ? አየ መለስ ነፍስህን አይማረው የደንቆሮ መጨረሻ፡፡
እንኳን እዚህ ለዚህ ወገን ለወገን ቀርቶ ስንት ኢትዮጵያዊ እሴት ነው ከእኛ ወጥቶ ለሌላው ዓለም የተረፈው? ሌሎቹ ብልጦቹ ከእኛ ወስደው የተጠቀሙ ስንት እግዳሉ ይታወቅ አይደለም ወይ? ይህች ሀገር የአማራ እሴቶች ያላቹህትን ሁሉ አጥታ ምን ይቀራታል? ታዲያ እነኝህ እሴቶች ጠቃሚ መሆናቸው ከታወቀ ከተመሰከረ እኮ በምን ምክንያት ነው የአማራ ስለሆኑ ብቻ ይጥፉ ይወገዱ የሚባለው? ይሄ ምን ማለት ነው? አማራ ከዚህ በኋላ ለሀገሩ ለወገኑ መሥራት አይችልም አይኖርበትም ማለት ነው? ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን ሥልጣን ኃላፊነት መያዝ አይችልም ማለት ነው? አዎ ይሄንን ማለታቹህ እንደሆነ በምትሠሩት ሥራ ሁሉ አረጋገጣቹህ፡፡
ግን በ 21ኛው መቶ ክ/ዘመን እንዲህ ዓይነት የድንጋይ ዘመን የአረማውያን አስተሳሰብን ሥራ ላይ ለማዋል መሞከር የለየለት እብደት አይደለም ወይ? ይቻላል ወይ? እስከ አሁን እንደቻላቹህ ነገም የምትችሉ ይመስላቹሀል ወይ? እኔ ወያኔ የፈለገውን ያህል ሲጠብ ሲደነቁር ቢኖር የዚህን ያህል ይጠባል ይደነቁራል ብዬ ለማሰብ እጅግ ይቸግረኛል፡፡ እጅግ ያሳዝናል እውነታው ይሄው ነው፡፡ የሚጠቅም ሆኖ እስከተገኘ ጊዜ ድረስ እምየ ኢትዮጵያና ሕዝቧ አይደለም ከአማራ ባሕር ተሻግራም ከአቦርጁኖችም ቢሆን ትወስዳለች ልትወስድም ይገባታል፡፡ የሠለጠነ የበሰለ አስተሳሰብ ማለት ይሄ ነው፡፡ ወይ ወያኔ የአረማዊነት ማጥ ውስጥ ሰምጠሽ ዐረፍሽው?
መልካም ሥራ የሠራ የዚህች ሀገር ምኑንም ነገሩን ሳይሰስት የመጨረሻ መሥዋዕትነት እየከፈል ሀገሪቱን በነጻነቷ የኮራች የደመቀች ባለታሪክና የሥልጣኔ መሠረት እንድትሆን ማድረግ የቻለ ሊደነቅ ሊከበር ጎሽ ሊባል ሊመሰገን ይገባል እንጅ እኮ በምን ሒሳብ ነው ስንት የሆነላትን ሀገር ታሪክ ገደል ከቶ በመቶ ዓመት ገድቦ፣ ከንቱ አመድ አፋሽ አድርጎ በገዛ ወገኖቹ እንደጠላት በክፉ ዐይን ሊታይ የሚገባው? ዛሬ ወያኔ በሠራው የክፋት ሥራ አማራነትና እሴቱን ተገላይ አላስፈላጊ የሚጠላና የማያሳፍርም ማድረግ የቻሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በርካታ ብሔረሰቦች ባሉበት ሀገር የአንድ ብሔረሰብ የበላይነት (Domination) የማይቀር ተፈጥሯአዊና የታሪክ ሀቅ ነው፡፡ የትም ዓለም ያለው ተሞክሮ ከዚህ የተየ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም የተለየች ልትሆን የምትችልበት ተአምር የለም፡፡
በእርግጥ ግፍንና በደልን በተመለከተ ተመሳሳይ የአሥተዳደር ሥርዓት ከነበራቸው ሀገራት እንጻር ሀገራችን ስትታይ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ምስክርነት ከጥንት ጀምሮ ሕዝቧ እግዚአብሐርን አምላኪ ሕዝብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሌሎቹ ሀገራት ሲፈጸሙ የነበሩ ዘርን መሠረት ያደረጉ ግፎችና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ፈጽሞ አልነበሩም አልተፈጸሙም፡፡ እያወራሁ ያለሁት እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ ላይ በርካታ ብሔረሰቦች እናሳም ሆኑ ምን ሠፍረው ያሉበት ቦታ ለምና አረንጓዴ ሆኖ የምናገኘው፡፡ ፋሽስት ጣሊያን ይሄንን እሴትና ቅርስ በማጥፋት ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለመከፋፈል ብሔረሰብን፣ ሃይማኖትን፣ ሞያን ሳይቀር መሠረት ያደረጉ ያልፈጠረው የሀሰት ስም ማጥፋት ያላደረገው ጥረት አለነበረም፡፡ ብዙዎቹ ፈጠራዎቹ ዛሬ ላይ እንደ እውነት ተወስደው ወያኔ ኦነግን ሻቢያና ኦብነግን የመሳሰሉ ድርጅቶች ከራሳቸው ዓላማ ጋር ተጣጥሞላቸው ሕዝባችንን እያሳሳቱበት ይገኛል፡፡
በሉ እንግዲህ አንተ መከረኛ ወገኔ ምን ላድረግህ ወዴት አባቴ ልሸሽግህ ባትወደውም እውነቱ ይሄው ነው ረ ተው በቃ በል? እንደ በግ እየተነዳህ ወደ መቃብርህ ትተምለታለህ እንዴ? ምን እሚሉት መደንዘዝ ነው እንዴት ያለ ፍዘት ነው? ምን እሚሉት ፍርሐት ነው ከሞት በኋላ ሌላ ሞት ያለ ይመስለሀል እንዴ? ምኑን ነው የምትፈራው? ምን አድርገ ልቀስቅስህ ምን አድርገ ላንቃህ ምን አድርገ ልታደግህ ኸረ እኔስ ጨነቀኝ፡፡ ምን አባቴ ልሁን? በአዋጅ አማራ ይጥፋ ተብሎ እስኪታወጅ ነው የምትጠብቅ? ገና ዛሬ ተጃጃልክ፡፡ ለነገሩ እሱም ቢሆን አልቀረም በይፋ በአደባባይ አማራን ኦርቶዶክስን አዳከምን ብለው ፎከሩ እኮ! ዓላማቸው ማዳከም ብቻ ይመስልሀልን? አንተን ለማጥፋት ስንት ነገር እንደተደረገና እየተደረገም እንዳለ እረሳኸው እንዴ? ዝምታህ እስከቸ ነው ነው? ወይስ አንተም እንደ ብአዴን ካድሬዎች አማራነትህን ማንነትህን መለያህን ክደህ አስደምስሰህ አስረሽነህ ማንዘራሽ ምናምንቴ ሆነህ ለመኖር ፈለክ? ይሄ ነው ፍላጎትህ አታደርገውም! ፈጣሪዬ ይሄንን ሳታሰማ ጥራኝ፡፡
ታዲያ ምን ነው መናቁ መገፋቱ መጨቆኑ መረገጡ አልሰማህ አለ? አላስቆጣህ አለ? የታለ አሳየኛ? ከየት አመጣኸው ይሄንን ፍርሐት አማራነት እኮ እንዲህ አልነበረም፡፡ አማራነት እኮ ከራሱ አልፎ ተርፎ ለአፍሪካዊያን ወንድሞቹ የነጻነት ትግል ከሙግት እስከ መሥዋዕትነት በተግባር አሳይቶ እንዳረጋገጠው ስለ ሌሎች ነጻነት የሚገደው የሚቆጨው የሚያንገበግበው ዕረፍት የሚነሳው የነጻነት የፍትሕ የእኩልነት ጠበቃ እኮ ማለት ነው፡፡ ይሄንን አኩሪ እሴትህን ቅርስህን ሀብትህን ማንነትህን የት ጣልከው ? ወዴት አደረስከው ምን በላብህ ምንድን ነው ፍላጎትህ ምንድን ነው ዓላማህ?
ኢትዮጵያ ከማንነቷ ከታሪኳ ከቅርሶቿ ከሃይማኖቷ ጋር ለዘላዓለም ትኑር፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Ayzon says
Ato G/Kidan,
Ayizon!
Weyanewoch lela 230amet bichemerum Amaran matifat ayichilum!!!!
“ምንድን ነው ፍላጎትህ ምንድን ነው ዓላማህ?”Melsun beTigst yitebequ::
“አየ አንች ክምሬ ያለሽ መስሎሻል ተበልተሽ አልቀሻል” ሲል በኃዘን geberew tenagere.
Abedariwes(Kuru Amara) min ale?
Bedehna geze yasqemetut terit(potential) le qurt gize yageleglal!!!!
PS.: Yemialeqsewen ayine keAlagibabe new yeteteqemut. Balebetiyewa betayew taznibotalech:-(
John says
What a trash article.
aradaw says
ከማጡ ወደ ድጡ አለ የሃገሬ ሰው
I have the chance to read the ሠዓሊ አምሳሉ articles. There is nothing that stops him from put his fingers everywhere. I just can not understand what he wants. Which Ethiopia is his? Once he even declared death to Betty Abera who was in some South Africa show. He wants us to pray the way he does, he wants us to eat what he eats. He wants us to wear what he does. He even wants or choose for us with whom we sleep. Where and when he stops meddling with everything. He is one of those who tries to condemn the tyrant TPLF but with his writing serves them very well. I can not say he is a direct and indirect part of them. His continues one-sided and biased history is very offensive and serves no good. His desire and ambition of domination, his unbelievable nostalgia made him blind to see what is going now and and also made him ignorant of the TPLF’s strategy and policy. There is a saying I heard recently and it will be well fit to mention to ሠዓሊ አምሳሉ, get life, the toothpaste is out of the the tube and you can not put it back, if you try it only be messy and nothing else. He must be joking when he ask the Ethiopian people to sacrifice their identity in favor of the one where he belongs. he tells us “በርካታ ብሔረሰቦች ባሉበት ሀገር የአንድ ብሔረሰብ የበላይነት (Domination) የማይቀር ተፈጥሯአዊና የታሪክ ሀቅ ነው፡፡ የትም ዓለም ያለው ተሞክሮ ከዚህ የተየ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም የተለየች ልትሆን የምትችልበት ተአምር የለም፡፡” In order his ambition to be realized all the other peoples wishes and ambitions have to be suppressed. To fulfill his ambition he writes this poisonous, divisive and mixed messages. He tries to get our sympathy by attacking Meles and Woyanes, but in fact it is focused on his nostalgic past domination and hegemony “አማራ የመሪነትን ሚና እንደመጫወቱ ከሌሎቹ ወገኖቹ ኋላ ቀር አስተሳሰቦችን እንዲተውና የተሻውን፣ የበለጠውን፣ የላቀውን አስተሳሰብ እንዲጨብጡ ማድረጉ፣ መጣሩ፣ ማሠልጠኑ ኩነኔው፣ ኃጢአቱ፣ ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው? ሥልጣኔ እንዴት ሆኖ የተስፋፋ ነው የሚመስላቹህ? ጠቃሚና የተሻሉ አስተሳሰቦችን፣ ተሞክሮዎችን ልምዶችን አንዱ ከሌላው በመውሰድ ያንንም ሥራ ላይ በማዋል አይደለም ወይ? አየ መለስ ነፍስህን አይማረው የደንቆሮ መጨረሻ፡፡” Dear Amsalu, reality is out there for you to see, open your eye, the Ethiopian political movement has gone may be five decades and a lot has changed, untangle yourself from your outdated thinking and come up with something that will take us forward. Castigating and scolding others, blaming the victim is an old tactic that will never work.
The country is gripped by woyane dictators and brutal repression fragmented with their policy. These are the burning issues that need to pull us together and find a common ground to fight and remove the common enemy. Asking us to abandon once heritage and carry a false identity will not brings us close at all.