በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች በቅድሚያ ትግላቸውን በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ ያድርጉ! እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ከሰኔ ፲፬ - ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (June 21 - 22, 2014) አራተኛ መደበኛ ስብሰባችንን በተሣካ ሁኔታ አካሂደናል። በሁለት ቀናት ጉባኤያችን የሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቁጥጥርና ፍተሻ ኮሚቴዎች ያቀረቧቸውን የ፮(ስድስት) ወራት የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን አዳምጠን ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ድርጅቱ ያከናወናቸው መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በአፈፃፀም የታዩ ድክመቶች እንዲታረሙ በማስገንዘብ፣ ለድርጅቱ ዓላማ ዳር መድረስ የሚያግዙ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል። ፩ኛ) የኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር እና የግዛታዊ አንድነት መጠበቅን … [Read more...] about የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት
Archives for June 2014
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አራት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ኃይለማርያም ማሞ - የጦሩ ገበሬ ፈረሱን እንደሰው - አስታጠቀው ሱሬ መተኮሱንማ - ማንም ይተኩሳል ኃይለማርያም - ማሞ አንጀት ይበጥሳል በማለት በዜማ - የዘመርንላቸው ኃይለማርያም - ማሞ ማለት እኚህ ናቸው። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? –፭” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፭
ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?
በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡ የጥናቱ ዘገባ ኢህአዴግ በየጊዜው ከሚያቀርበው የዕድገት ስሌት ጋር በግልጽ የሚጋጭ መሆኑ ተነገረ፡፡ በዓለማችን በሚገኙ 108 በማደግ ላይ ባሉ አገራት በየጊዜው ጥናት የሚያካሂደው ማዕከል ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ 10 መለኪያዎችን እንደ ግብዓት እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡ እነዚህም በሦስት ዘርፎች የተጠቃለሉ ናቸው - ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ፡፡ በተለይ በኑሮ ሁኔታ ሥር ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ … [Read more...] about ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?
“ፀሎታችን በቤታችን”
በተለያዩ ግዜያት ህጋዊ እና ህገወጥ በሆነ መንገድ ተሰደው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል ጥቂት የማይባሉ የኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የህዝብ ሙስሊሙን ሃይማኖታዊ ደንብ እና ስረአት አክበረው እንደሚኖሩ ይታወቃል። እነዚህ በሃገሪቱ ግዛቶች ሪያድ፣ ጅዳ፣ ደማም እና ጅዛን በሚባል ክፍለ ግዛቶች ውስጥ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚኖሩ የሚነገረው የእምነቱ ተከታዮች በደስታም ሆነ በሃዘን ግዜ ሃይማኖታቸው የሚያዘውን የፀሎት ስረአት ሃይማኖታዊ ወግ እና ስረአት ጠብቀው ለፈጣሪያቸው ጸሎት ማድረስ እንደማይቸሉ የሚገልጹ ምንጮች ሳውዲ አረቢያ በእስላማዊ ህግ የምትመራ እንደመሆኗ መጠን ሌሎች ሃይማኖቶችን ማራመድ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ በመንግስት ዘንድ በይፋ ከሚታውቀው ሃይማኖት ውጭ ምንም አይነት አማራጭ የጸሎት ስፍራዎች ባለመኖራቸው በኢትዮጵያውያኑ … [Read more...] about “ፀሎታችን በቤታችን”
ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን?
ነገሩ ግራ የገባው ነው! ለመሆኑ አሳባችን ምንድነው? እንዲሁ ስንጨቃጨቅና ስንነካከስ ምን ያህል ልንዘልቅ ነው? ንትርኩና መተላለፉ እጅ እጅ ብሎንና ሰልችቶን ሁሉን ትተን የእርቅ ያለህ! ለማለት ጊዜው ለመሆኑ መቼ ይሆን? ከጥል ወደ ፍቅር፤ ከመከፋፈል ወደ አንድነት፤ በስምምነት ለማደግ ቀጠሮ የያዝነው ለመቼ ነው? በፖለቲካው ውድድር ውስጥ ያለንን የበላይነት ለማስከበር የሞት የሽረት ትግል ስለምናካሄድ፤ የጋራ የሆነውንና የሁላችንም ችግር የሆነውን ይህን የእርቅ ጥያቄ እንዲስተናገድ ማን ቦታ ይስጠው? ይህ የእርቅ ችግር ግን እንደ ድልድይ ሆኖ ሁሉንም ጎራ ያገናኝ ነበር። በራሱ ችግራችንን ሁሉ ባይፈታም እንደ ጥሩ መነሻ ያገልግላል። ይህ የጋራ የሆነ የእርቅ ጉዳይ መደማመጥን ሊጠይቅ ነው። እኛ ደግሞ የለመድነው ሌላ ነው። ታዲያ ስንተላለፍና ስንዘላለፍ ችግራችንን አክርረነው እና … [Read more...] about ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን?
እውን ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነውን?
ከዓመታት በፊት “ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው” የሚለውን ጨምሮ ብዙ እንግዳ የሆኑ ነገሮችን የሚናገሩ ሦስት “አባቶችን” አውቅ ነበር አንደኛው ከሀገር ውጭ ናቸው፡፡ እነኝህ “አባቶች” ተከታዮች እያፈሩ መጡና ዛሬ ላይ እነሱ የሚሉትን የሚያምኑ ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባሉ ሰዎችን እያየን ነው፡፡ እነዚህን እንግዳ አስተምህሮዎቻቸውንም በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ (social media) በከፍተኛ ደረጃ እየናኙት ይገኛሉ፡፡ እውን ግን የናዝሬቱ ኢየሱስ መሲሑ ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነው? ይሄንን ብለው እየሰበኩ ያሉ “አባቶች” ይሄንን ትምህርታቸውን በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወይም ትውፊታዊ መረጃ በመስጠት አያረጋግጡም፡፡ የሆነ የራሳቸውን ነገር ይቀበጣጠሩና ክርስቶስንና ሌሎች ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ አባቶችን ሁሉ ኢትዮጵያዊያን ያደርጓቸዋል፡፡ እነኝህ አባቶች ሲያዩዋቸው የአእምሮ እክል … [Read more...] about እውን ክርስቶስ ኢትዮጵያዊ ነውን?
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫" በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሶስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በፊት የታወቁ - ገነው በስራቸው ዛሬ ሚታወሱ - በቴዲ ልጃቸው ስምህ ይጠራልህ - ብትሞትም ያላቸው ካሳሁን ገርማሞ - ማለት እኚህ ናቸው ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ እኚህ ሰው ማናቸው – ፬? ቃልም አልተነፍስ - ፍንጭም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬
አህያውን ትቶ ዳውላውን
በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊ የዜና መለዋወጫ መስኮች፤ “ትግሬዎች በዚህ መንግሥት ተጠቅመዋል? ወይንስ አልተጠቀሙም?” የሚለው ጉዳይ ዓይነታ መወያያ ሆኖ፤ መድረኮቹን ሁሉ አጣቦ ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ፤ አንድን ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች ሲያነሱ፤ ከትግሉ ዋና ግብ አንጻር ነው። እንዲያው ለወግ ያህል ወይንም ቁጭትን ለመዘርገፍ የሚደረግ ውይይት፤ የታጋዮችን ቀልብ አይስብም። ይኼ ጉዳይ በትግሉ ሂደት ውስጥ ለኢትዮጵያዊ ታጋዮች ምን ይጠቅማል? ትግሉን ወደፊት ከመግፋትና ከግቡ ከማድረስ አኳያ ምን አስተዋፅዖ አለው? ይኼ ወሳኝ ነው። ትግል በመርኅ የሚካሄድ እንጂ፤ በየተመቸው የሚነዳ መንፈስ አይደለም። በትግሬዎችና ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ በተነሳው ድርጅት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። በእርግጥ የዚህ ግንባር አባላት በሙሉ ትግሬዎች ናቸው። ይኼ በግልፅ ያለና … [Read more...] about አህያውን ትቶ ዳውላውን
በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ!
ሕዝበ ክርስቲያን በጰራቅሊጦስ መንገድ ሲሄዱ፤ፓትርያርክ፤ሊቃነ ጳጳሳት፤መነኮሳትና ቀሳውስት በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ!
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት 3ሺ ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው!
በስደት አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በተመጣጣኝ ዋጋ ተቀብሎ በማስተማር ከፈተኛ ስተዋጾ እያበረከተ የሚገኘው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ላለትፉት ሁለት አስርት አመታት ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመኩበት እና የሚኮሩበት ተቋም ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወላጆች እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች መሃከል በተፈጠረው አለመግባባት ት/ቤቱ እንደተቛም ህልውናውን ጠብቆ ወደፊት መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች። ሰሞኑን የት/ቤቱ የኪራይ ዘመን እና የት/ቤቱ ህጋዊ ፈቃድ የግዜ ገደብ በመጠናቀቁን ተከትሎ በተቋሙ ህልውና ላይ የጋረጠው አደጋ አሳስቢ መሆኑን በመጥቀስ ከወራት በፊት በማን አለብኝነት ት/ቤቱን በበላይነት ተቆጣጥረው እንዳሻቸው ሲዘውሩት የከረሙት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሹማምንቶች በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ተከሰቱ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት 3ሺ ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው!