• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት

June 25, 2014 12:34 am by Editor 1 Comment

በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች በቅድሚያ ትግላቸውን በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ ያድርጉ!

እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ከሰኔ ፲፬ – ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (June 21 – 22, 2014) አራተኛ መደበኛ ስብሰባችንን በተሣካ ሁኔታ አካሂደናል። በሁለት ቀናት ጉባኤያችን የሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቁጥጥርና ፍተሻ ኮሚቴዎች ያቀረቧቸውን የ፮(ስድስት) ወራት የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን አዳምጠን ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ድርጅቱ ያከናወናቸው መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በአፈፃፀም የታዩ ድክመቶች እንዲታረሙ በማስገንዘብ፣ ለድርጅቱ ዓላማ ዳር መድረስ የሚያግዙ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል።

፩ኛ) የኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር እና የግዛታዊ አንድነት መጠበቅን በተመለከተ፦

በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዐላዊ መብቱን የተነጠቀ፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅምም ለባዕዳን ተላልፎ የተሸጠና የአገሪቱ ግዛታዊ አንድነት ፈጽሞ ያልተጠበቀ መሆኑን ከቀረቡት ተጨባጭ ማስረጃዎች ተገንዝበናል። የአገሪቱን የባሕር በር ወያኔ ተገዶ ሣይሆን ወዶ እና ፈቅዶ ለሻዕቢያ ከሸጠው ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የተነሣም ኢትዮጵያ መተናፈሻ የሌላት ዝግ መሬት ሆናለች። ስለዚህ ኢትዮጵያ የወጪ እና የገቢ ንግዷን ጂቡቲን በመሣሰሉ ትናንሽ አገሮች መልካም ፈቃድ ላይ እንዲመሠረት በማድረጉ በዕድገቷ ላይ ከፍተኛ መሠናክል ሆኗል። «ወደብ ለሌለው አገር ስለ ዕድገት አይታሰብም» ማለት ባይቻልም እንኳን፣ የዕድገት ግስጋሴው ግን ወደብ ካላቸው ጋር ፈጽሞ ሊወዳደር አይችልም።

ከዚህ በተጨማሪ በመሬት ስፋት አንፃር ከአየርላንድ ሪፑብሊክ ግዛት የሚበልጥ ከ፰(ስምንት) ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሆነ የአገሪቱ ለም እና ድንግል መሬት ለ፺፱(ዘጠና ዘጠኝ) ዓመታት ለሕንድ፣ ለቻይና፣ ለፓኪስታን፣ ለግብፅ፣ ለጅቡቲ እና ለሌሎችም አገሮች ባለኃብቶች በጣም በርካሽ ገንዘብ ተሸጦ ገበሬው ጦም አዳሪ እና አገር-የለሽ ሆኗል።

ከምዕራባዊ የአገሪቱ ድንበር በቁመት ከሰሜን ወደ ደቡብ ፩ሺህ፮፻(አንድ ሺህ ስድስት መቶ) ኪ.ሜ.፣ በወርድ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ፶(ሃምሣ) እስከ ፷(ስድሣ) ኪ.ሜ. ጥልቀት ያለው ለሙ እና ድንግሉ መሬት ለሱዳን በገጸ-በረከትነት ተሰጥቷል።

በቋንቋ ላይ የተመሠረተው የፌደራል አገዛዝ አደረጃጀት የሕዝቡን ነባር የአንድነት እና የአብሮነት ስሜት ንዶታል። ይህንንም ወያኔ ሆን ብሎ ኃይልን በአካተተ ፕሮፓጋንዳ ጭምር በመታገዝ የሕዝቡን የአንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት በእጅጉ እንዲሸረሸር አድርጓል።

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ከዐማራ የጸዱ ክልሎች ለመመሥረት በተያዘው ዘር የማጽዳት እና ዘር የማጥፋት ዘመቻ ዐማራው የማይኖርባቸው ክልሎች ተፈጥረዋል።

ይህ አጠቃላይ ሁኔታ ተዳምሮ ሲታይ የሕዝቡ ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እና ግዛታዊ አንድነት ያልተጠበቀ እና ያልተከበረ መሆኑን ለመገንዘብ አይከብድም። በመሆኑም ዛሬ በትግሬ-ወያኔ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉት ኃይሎች የትግል ሥልታቸውን ዳግም ሊመረምሩ ይገባል። በአንድ አገር ላይ ሰላም፣ ዕኩልነት፣ ዲሞክራሲ እና ፍትኅ የሚሠፍኑት በቅድሚያ አገሪቱ ኅልውናዋ ሲጠበቅ ነው። ስለሆነም «በቅድሚያ የመቀመጫዬን» ነውና፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች የትግሉን አቅጣጫ በቅድሚያ በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ እንዲያደርጉት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

፪ኛ) በዐማራው ላይ የሚካሄደውን ሁለንተናዊ ጥቃት በተመለከተ፦

ባለፉት ፶(ሃምሣ) እና ፷(ስድሣ) ዓመታት ብቻ ሣይሆን፣ ከዚያም ቀደም ሲል ጀምሮ፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሱ የውጭ እና የውስጥ አጥፊ ኃይሎች የመጀመሪያው የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉት «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም የረዥም ዘመናት ታሪካችን አሻራዎቻችንም ሆነ ዛሬ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ አጉልተው ያሣያሉ። ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ዐማራው በኢትዮጵያ ምድር የመኖር መብቱን ተገፍፏል፤ በአገሩ ውስጥ ተንቀሳቅሶ በፈለገው እና ባሻው የሥራ መስክ ተሠማርቶ የመሥራት የዜግነት መብቱን ተነጥቋል፤ በነገዱ ማንነት ብቻ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ በጅምላ ተሠልቧል፣ ጭፍጨፋ እና ግድያ ተፈጽሞበታል፤ እህቶቻችን እና እናቶቻችን ጡታቸው ተቆርጧል፤ ዐማራው ኃብት እና ንብረቱን ተነጥቆ፣ በአገሩ እንደ ባይተዋር ተቆጥሮ በግፍ ከመኖሪያው ተባርሯል።

ለአብነት ያህል ባለፉት የ፮ ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ካድሬዎች እና በተላላኪዎቻቸው ከተፈፀሙት ግፎች መካከል፦

  •  በመጋቢት ወር ሁለተኛ ሣምንት መጀመሪያ በአምቦ ከተማ አካባቢ፣ ዳኖ ወረዳ (ከምዕራብ ሸዋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ የዐማራ ተወላጆች በኦሕዴድ ካድሬዎች አማካይነት «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው ተባርረዋል፤ ፳፮(ሃያ ስድስት) ዐማሮች በአሠቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በተለይ አቶ ጌጡ ክብረት የተባሉት የዐማራ ተወላጅ በአሠቃቂ ሁኔታ በገጀራ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘግቧል።
    • በግንቦት ወር «የአዲስ አበባን ከተማ መስፋፋት እንቃወማለን» በሚሉ አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች በሚመራው እንቅስቃሴ ተሣታፊዎች፦ በአምቦ፣ በዓለማያ፣ በነቀምት እና በሮቤ (መዳወላቡ) ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የዐማራ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና አልፎ ተርፎም ኢሠብአዊ ግድያ ፈፅመዋል። በተለይም በነቀምት ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ፯ ተማሪዎች በትግሬ-ወያኔ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ተገድለዋል። በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ትማር የነበረችዋን የዐማራ ተወላጅ ከፎቅ ፈጥፍጠው ገድለዋታል። ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. በቅፅ ፪፣ ቁጥር ፳፩ ባወጣነው መግለጫችን በይበልጥ እንደተብራራው፣ በጊምቢ ከተማ እና አካባቢው (ምዕራብ ወለጋ) ከሚኖሩት ዐማሮች መካከል በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩት ቤት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው እንዲፈናቀሉ ሆኗል። በአጠቃላይ በጊምቢ ከተማ እና በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩት ዐማሮች የንብረት ይዞታ ውስጥ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። ከዚህ በተጨማሪም በግንቦት ፮ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. የአካባቢው የኦሕዴድ ካድሬዎች በዐማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል። ከስቡ ስሪ ወረዳ (ምሥራቅ ወለጋ) ፪መቶ ዐማሮች ‹‹ይህ አገር የእናንተ አይደለም፣ አገራችሁ ግቡ፤›› ተብለው ኃብት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው ተባርረዋል። በወለጋ በአክራሪ ኦሮሞዎች እና በኦሕዴድ ካድሬዎች አማካይነት በዐማሮች ላይ በስፋት የሚፈፀመው ግፍ አሁንም ያልተገታ መሆኑን የመገናኛ ብዙሃን እስካለፈው ሣምንት መጨረሻ ድረስ የዘገቡት ጉዳይ ነው።
    • በዘንድሮው ዓመት በ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ብቻ የትግሬ-ወያኔ ካድሬዎች «ሕገ-ወጥ ግንባታ አካሂዳችኋል» እና «ቦታችሁ ለልማት ይፈለጋል» የሚሉ ሠንካላ ምክንያቶችን በመደርደር፦ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በደብረማርቆስ፣ በደሴ፣ በሐረር እና በሌሎችም ከተሞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን በግሬደር እና በሰው ኃይል አፍርሰዋል። የትግሬ-ወያኔዎች በየዓመቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈፅሙት ሆን ብለው የክረምትን ወቅት ጠብቀው ነው። የዚህ ድርጊት ቀዳሚ ተጠቂዎች ደግሞ ዐማሮች መሆናቸው ይታወቃል።

በአንድ ቃል በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ዐማራው በየዕለቱ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፀምበት፤ ቀኑ የጨለመበት፤ ድምፁ ሰሚ ያጣበት፤ ግፉን ተመልካች ያላስተዋለለት ሆኗል።

ሐ) በዐማራው ላይ በሚደርሰው ግፍ እና በደል የተቃዋሚ ድርጅቶች እርምጃ፦

በሚያሣዝን ሁኔታ «በኢትዮጵያዊነት» ስም የተደራጁት የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች እንኳን ስለዐማራው ችግር ተቆርቁረው የሚያደርጉት ረብ ያለው ሥራ የለም። በዐማራው ላይ የሚፈፀሙትን ግፎች እና በደሎች «በዐማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የደረሰ» እየተባሉ የሚሰጡት መግለጫዎች ዛሬ የዐማራውን ኅልውና ሆን ብለው የሚክዱ መሆኑን እና ለችግሩም የሚሠጡትን ዝቅተኛ ግምት በገሃድ ያሣያል።

መ) ዐማራው ኢትዮጵያዊነቱን ሣይለቅ በዐማራነቱ የመደራጀቱ አስፈላጊነት፦

አሁን ያለውን «የዐማራውን ጉዳይ ሆን ብሎ የማጣጣል» ሁኔታ መለወጥ የሚችለው፣ የዐማራው ልጆች ተደራጅተው «አለንልህ» ሲሉት እና ከጠላቶቹ አንፃር አቻ ወይም ጉቢ ኃይል ሲፈጥሩ ብቻ እንደሆነ የምክር ቤቱ አባላት ባደረጉት ሠፊ ውይይት ሙሉ በሙሉ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስለሆነም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የጀመረውን ዐማራን የማደራጀት ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል፤ አባላት እና አካላትም ሳይሰለቹ እና ሳይታክቱ የእያንዳንዱን ዐማራ በራፍ በማንኳኳት የድርጅቱ አባል እንዲሆን፤ ድርጅቱንም በዕውቀት፣ በገንዘብ፣ በመረጃና በመሳሰሉት እንዲደግፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

Moresh Wegenie: mwaoipr@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Hailu says

    July 7, 2014 10:37 pm at 10:37 pm

    This is an important ideas. By the way the most fullish idea of most “Amharas” is “we are Ethiopian ,we proud of our country not by being Amhara….” But there should not be an Ethiopian unless stopping violation of our right. So all of Amharas should first proud of himself and tried to struggle about his or her right. This idea was the Prof. Astrat’s . We would have been saved if we had had followed his idea. So, we have to struggle more that when/where ever to be an Amhara!
    Thank you

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule