አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል። በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል … [Read more...] about አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ
Archives for June 2014
ክስ
ለአንድ ዘጠኝ ቀናት በግል ጉዳይ ምክንያት ወደ ገጠር ወጣ ብየ ነበር፡፡ ሀገር ሰላም ብየ ከሄድኩበት ስመለስ ከሁለት ወራት በፊት “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉ የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን” በሚል ርእስ በጻፍኩት ጽሑፍ ምክንያት የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ገብሩ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ፈቃዱ ምኅተመወርቅ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው ከሔዱ በኋላ መከሰሳቸው ተነግሯቸው የእኔን ሙሉ የመኖሪያ አድራሻ ተጠይቀው እነሱም ከስልኬ በቀር የመኖሪ አድራሻየን እንደማያውቁ ሥራ የምንሠራው በስልክ እየተደዋወልን ቢሮ በመገናኘት እንጂ መኖሪያ ቤቴ ድረስ በመምጣት አለመሆኑን ሲገልጹ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሬን እንዲሰጡ በመጠየቃቸው ስልኬን መስጠታቸውን፤ በዚያ ስልክ ቁጥር መሠረትም ጣቢያው ድረስ ስለምፈለግ እንድቀርብ ለመንገር ለዚያ ክስ ጉዳይ የተመደቡ … [Read more...] about ክስ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ሲጠሩ የኖሩ - በዶክቶር ማዕረግ የውጪ ጉዳይን - የመሩልን በወግ በጥሩ ስራቸው - የሚነሱ ሁሌ ስማቸው ምናሴ - አባታቸው ኃይሌ ተብለው ሚጠሩ ባለስልጣን ናቸው ምስላቸው ተለቆ - ሳምንት ያየናቸው ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ እኚህ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪
የኢትዮጵያ መሰረታዊ የልማት ችግር የት ነው? እንዴትስ ይፈታል?
ስለ ልማታዊ መንግስት (developmental state) ስናወራ ልማታዊ የሚለው ቅጽል ስም ገላጭ በመሆኑ መጀመሪያ “ልማታዊ” ሲባል ምን ማለት ነው? ብለው ሰዎች እንዲጠይቁን ያደርጋል። ኣንዱ የዚህ ጥያቄ ምንጭ በኣሁኑ ዘመን ልማት ለሚለው ስያሜ ሰፊ ትርጉም ስለተሰጠው ሲሆን ኣንድ መንግስት ዛሬ ላይ ሆኖና ብድግ ብሎ “ልማታዊ መንግስት ነኝ” ሲል ማን ልማታዊ ያልሆነ ኣለ ብለው ሰዎች እንዲነሱ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሹ የሚያደርግ ጥያቄ ለማኝ ጉዳይ ነገር ያንጠለጠለ በመሆኑ ነው። ሁሉ እንደሚያውቀው በኣሁኑ ጊዜ ልማት ለሚለው ጽንሰ ሃሳብ የተሰጠው ትርጉም ሰፊ ሲሆን የሰው ልጆችን ሁለንተናዊ ኣዎንታዊ እድገት ይጠቀልላል። የኢኮኖሚ እድገት፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ዴሞክራሲና መልካም ኣስተዳደር፣ ወዘተ. ይሸፍናል። በመሆኑም ኣንድ መንግስት በዚህ በኣሁኑ ጊዜ ልማታዊ ነኝ ሲል ማንም … [Read more...] about የኢትዮጵያ መሰረታዊ የልማት ችግር የት ነው? እንዴትስ ይፈታል?
In Defense of Freedom of Speech and Association: The case of Zone9ners
"Once a government is committed to the principle of silencing the voice of opposition, it has only one way to go, and that is down the path of increasingly repressive measures, until it becomes a source of terror to all its citizens and creates a country where everyone lives in fear." Harry S. Truman Tigray People’s Liberation Front (TPLF), the core and the oldest of all EPRDF member parties, has a proven record to silence deliberately the voice of dissents and oppositions since its … [Read more...] about In Defense of Freedom of Speech and Association: The case of Zone9ners