ለአንድ ዘጠኝ ቀናት በግል ጉዳይ ምክንያት ወደ ገጠር ወጣ ብየ ነበር፡፡ ሀገር ሰላም ብየ ከሄድኩበት ስመለስ ከሁለት ወራት በፊት “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉ የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን” በሚል ርእስ በጻፍኩት ጽሑፍ ምክንያት የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ገብሩ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ፈቃዱ ምኅተመወርቅ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው ከሔዱ በኋላ መከሰሳቸው ተነግሯቸው የእኔን ሙሉ የመኖሪያ አድራሻ ተጠይቀው እነሱም ከስልኬ በቀር የመኖሪ አድራሻየን እንደማያውቁ ሥራ የምንሠራው በስልክ እየተደዋወልን ቢሮ በመገናኘት እንጂ መኖሪያ ቤቴ ድረስ በመምጣት አለመሆኑን ሲገልጹ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሬን እንዲሰጡ በመጠየቃቸው ስልኬን መስጠታቸውን፤ በዚያ ስልክ ቁጥር መሠረትም ጣቢያው ድረስ ስለምፈለግ እንድቀርብ ለመንገር ለዚያ ክስ ጉዳይ የተመደቡ የጣቢያው የሥራ ኃላፊዎች በተደጋጋሚ በመደወል እኔን ለማግኘት ሲሞክሩ አልነበርኩምና ስልኬም ለቀናት ጠፍቶ ነበርና ሊያገኙኝ አለመቻላቸውን፤ ከዚያም ዋና አዘጋጁ ኤልያስ እዛው ታስሮ ሲቀር ዋና ሥራ አስኪያጁ ፍቃዱ ለሰዓታት እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ መለቀቁን ሰማሁ፡፡
ከሳሹ የጂማ ዩኒቨርስቲ (መካነ ትምህርት) ሲሆን ክሱ ከሀቅ የራቀ ቢሆንም እሱ እንደሚለው ጽሑፉ የአንድ ብሔርን ማንነት ስለሚያንቋሽሽ በጽሑፉ ሳቢያ በተማሪዎቸ ቁጣ ተቀስቅሶ ንብረቴ ወድሟል፣ በሰው ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ የመማር ማስተማር ሒደቱ ተስተጓጉሏል ወዘተ. የሚል ነው፡፡ ሳይቆራረጥ እንዳለ የወጣው ጽሑፍ ይሄንን ይመስላል https://www.goolgule.com/monuments-for-martyrs-or-victims/ ከዚህ ጽሑፍ በኋላ ለቀረቡልኝ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሰጠሁት ምላሽም ይሄንን ይመስላል https://www.goolgule.com/my-reply/ ኤልያስና ፈቃዱም ጽሑፉ የመጽሔቱን አቋም የሚያንጸባርቅ አለመሆኑን፣ በግልም ቢሆን ጽሑፉን እንደማይደግፉ እንደማይስማሙበትም ነገር ግን እንደ የብዙኃን መገናኛ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ ኃላፊነትና መብት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ጽሑፉን ሊያስተናግዱት እንደቻሉ፤ በመሆኑም ሊያስጠይቃቸው እንደማይገባ አስረድተዋል፡፡
ስለ እውነት ከሆነ ኤልያስና ፈቃዱ እንዳሉት ሁሉ ያ ጽሑፍ ብቻ አይደለም ሌሎች ጽሑፎቸም የእኔን የጸሐፊውን ብቻ እንጅ በጭራሽ የመጽሔቱን ወይም የመጽሔቷን ሠራተኞች አቋም አያንጸባርቁም፡፡ የሚገርመው ነገር ጽሑፎቸ ሁሉ ሲወጡ ከእነሱ ጋራ በሐሳቦቹ ካለመስማማታችን የተነሣ ሳንወዛገብ ሳንጨቃጨቅ ሳንከራከር ቀርተን አናውቅም፡፡ በመጨረሻ ላይ እንደመፍትሔ አድርገን የምንወስደው በተለያዩ ምክንያቶች አንዳንድ የጽሑፎቹ ሐሳቦች ተቆርጠው እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ቀሪውና የለዘበው እንዲወጣ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ጽሑፉ ሳይቆራረጥ እንዳለ የሚወጣው “በጎልጉል” የመካነ ድር ጋዜጣና በአንዳንድ ሌሎች መካነ ድሮችም ነው፡፡
በዚህ መልኩም በዚህች መጽሔት መጻፍ ከጀመርኩበት 2004ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ትላንቱ የመጨረሻው ጽሑፌ ድረስ ስንሠራ ቆይተናል፡፡ በዚህ ቆይታ ታዲያ ልጆቹ እንደሚፈሩትም በእኔ ጽሑፎች ላይ ብቻ ሁልጊዜ በፖስታ(በወረቀት መልዕክት) በኢሜይል (በመ መልዕክት) በስልክ (በመናግር) ማስጠንቀቂያ፣ ተቋውሞ፣ ማስፈራሪያና ዘለፋ ሳያጋጥም ቀርቶ አያውቅም፡፡ በዚህ አጋጣሚ መጽሔቷን ወይም የመጽሔቷን ሠራተኞች በሆነው ነገር ሁሉ ማዘኔንና ለሆነው ነገር ሁሉ ይቅርታ ማለት መውደዴን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ቀሪው የሥራ ዘመንም የምትፈልጉትንና የምትመኙትን ያህል እንዲሆንላቹህም እመኛለሁ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኘ ልናገረው የምችለው ያ ጽሑፍ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንን፣ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ተቆርቋሪ የሆነን፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ የማይሸፍጥን፣ ለሀገርና ሕዝቧ ጥፋት የማይመኝን ማንኛውንም ዜጋ ቅንጣት ታክል የሚያስቆጣ፣ የሚያበሳጭ፣ የሚያናድድ፣ የሚያስከፋ አንድም ነገር የለበትም፡፡ የኢትዮጵያንና የሕዝቧን ህልውናና ደህንነት የማይሹ የማይመኙ ለጥፋቷ ተግተው የሚሠሩ የሚያሴሩና የሚሸርቡ የጥፋት ኃይሎች ቅጥረኞች ግብረአበሮችና ደጋፊዎችን ግን ጽሑፉ በእርግጥም ያስቆጣል ያበሳጫል ያናድዳል ያስከፋል፡፡ ሲጀመር እኔ ከራሴ አፍልቄ ፈልስፌና ፈጥሬ ያወራሁት ወይም የጻፍኩት አንድም ነገር የለም፡፡ ማንም የሚያውቀውን ያለውን እውነታ ከታሪክ ማኅደር መዝዠ ከማስነበብ ውጭ ያደረኩት ነገር የለም፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በዚህ የሚያር የሚተክን የሚቃጠል ካለ ልረዳው ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡
ችግሩ የተፈጠረውም እዚህ ላይ ነው አሁን ያለንበት የአሥተዳደር ሥርዓት ዘይቤ እጅግ በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ እውነታን በእውነታነቱ መቀበልን የሚያስተናግድ የሚቀበል አይደለም፡፡ እውነታን አለባብሶ ፈጠራን አንግሦ ሐቅን አድበስብሶ በአንድ አቅጣጫ ብቻ እውር ድንብሱን ሽምጥ የሚጋልብ እንጅ፡፡ ምንም ይሁን እውነታን በእውነታነቱ ተቀብለን ለእውነታ መገዛት ካልቻልንና ይሄንን የመግባቢያ ምኅዳር (code of conduct) መፍጠር ካልቻልን እውነታ እንደ እውነታነቱ ሁሉ በራሱ ጊዜ ሐሰትንና ፈጠራን እየፈነገለ እየገለበጠ በወጣ ቁጥር ሁከት ብጥብጥና ረብሻ አልፎም ሌላ ነገር መከሰቱ የማይቀር ይሆናል፡፡
በዚያ ዩኒቨርስቲም ሆነ በሌሎች የተደረገው ተቋውሞና እረብሻ ከሳሹ እንዳለው በዚያ ጽሑፍ ሳቢያ ከሆነ ይህ ችግር የሥርዓቱ እንጅ ፈጽሞ የእኔ አይደለም፡፡ ሥርዓቱም የዘራውን ለማጨድ በሚገደድበት ወቅት ለምን? እንዴት? የማለት የሞራል (የቅስም) መብት ነጻነትና ብቃት እንደሌለው ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡ ማንም እንክርዳድ ዘርቶ ስንዴን ለማጨድ የሚችል ከቶውንም የለምና፡፡
በዚህች ሀገር እውነት የቡድን ሳይሆን የሀገሪቱና የሕዝቧ ሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ኃላፊነት ያለበት የሚያሳስበው የሚገደው እንደ ፖሊስ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሳሰሉት የሰላምና ደኅንነት ተቋማት ካሉ፤ በዚህ ጽሑፍ ሳቢያ ብጥብጥ ተነሥቷል የተባለው ክስ እውነታነት ካለው፤ ይህ ጉዳይ የጥፋት ኃይሎች በዚህች ሀገርና ሕዝብ ላይ ምን ያህል ስር እንደሰደዱና ከባድና አደገኛ ሥጋት እንደጋረጡ ሊረዱ የሚችሉበት ጥሩ አጋጣሚ ነውና የሚጠብቃቸውን ከባድ የቤት ሥራ በብቃት ለመፈጸም ቢረፍድም ሳይመሽ ነቅተውና በአጭር ታጥቀው የተጋረጠብንን እጅግ ከባድ አደጋ እንዲያመክኑ አበክሬ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይህ ችግር የተከሰተው ሀገር ተረካቢ በሆነው ወጣት ኃይል መሆኑ ብቻ በራሱ የችግሩን እጅግ አሳሳቢነትና ዘለቄታ ሊያስገነዝባቸው ይገባል፡፡ በዚያ ጽሑፍ ሳቢያ ከጥፋት ኃይሎች በግል በኢሜይል ከደረሱኝ መልዕክቶች የተረዳሁት ነገር ቢኖር ይሄንኑ ነው፡፡
እንግዲህ ተፈልገሀል ቅረብ ተብያለሁና እቀርባለሁ፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ የቀረበብኝ ክስ ዋስትና የሚያስከለክል እንዳልሆነ፡፡ የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ ዋስ ያስፈልጋል፡፡ አውቃለሁ በርካታ ቆራጥ ሀገር ወዳድ የመንግሥት ሠራተኞች እንዳላቹህ፡፡ ታዲያ ከዚህ ሁሉ አንድ ለኔ ዋስ ሆኖ የሚያስፈታኝ ጠፍቶ ወህኒ እበሰብሳለሁ ብየ አልገምትም፡፡ እናም አደራ አደራ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
aradaw says
እንደ እውነቱ ከሆነ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኘ ልናገረው የምችለው ያ ጽሑፍ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንን፣ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ተቆርቋሪ የሆነን፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ የማይሸፍጥን፣ ለሀገርና ሕዝቧ ጥፋት የማይመኝን ማንኛውንም ዜጋ ቅንጣት ታክል የሚያስቆጣ፣ የሚያበሳጭ፣ የሚያናድድ፣ የሚያስከፋ አንድም ነገር የለበትም፡
Dear ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
I always wonder when you say “Ethiopia”. I am sure you meant your Ethiopia. My Ethiopia is different than yours. My Ethiopia is a place for all where the histories of oromos and others are respected, not denied. The piece you wrote has a very mixed massage. it seems that it is written against “EPRDF” building monuments but the bigger message with it is absolute unfounded denial of history. You mentioned the history as work of EPRDF. I am very sorry to hear from you which I think a good writer. Now, I do not have to argue with you or any one else for that matter the book is out and I really encourage you to read and comment and if you can refute the content of the book. Dr. Abbas H. Gnamo “conquest and resistance in the Ethiopian Empire 1880-1974”
I am also sorry for the Jimma University action to restrict your right to express your ideas. this is your birth right. I also like to say that when we write something, we must not do it from our emotion. The writing of such a big and controversial issue requires a little bit of critical thinking, compassion about others and reference to available documents. Your writing is very irresponsible and do not help us to come close but instead you dig the pit much deeper. I understand the issue is very brutal and as you mentioned may be divisive , but the question is Is this happened? I will leave the answer for you to find out.
እዚህ ላይ እጅግ የሚገርመው ነገር ሕወሓት ኢሕአዴጎች ዐፄ ምኒልክ ከአሳዳጊያቸውና ከአስተማሪያቸው ከዐፄ ቴዎድሮስ የተቀበሉትን የተቻላቸውን ያህል ኢትዮጵያን እንደገና መልሶ አንድ የማድረግ ዓላማ አንግበው ሲዘምቱ ጡትና እጆቻቸውን ቆርጠውባቸዋል የሚሏቸውን ወገኖች ያቅጣት ሊደርስቦቸው የቻለው አንዋሐድም፣ የኢትዮጵያ ግዛት አካል አንሆንም፣ ለመንግሥት አንገብርም በማለታቸው እንደነበር ሳያፍሩ ይናገራሉ፡፡ ይባስ ብለውም መሥዋዕትነት የከፈሉ ወገኖች ሲሉ ይገልጿቸዋል፡፡ ይታያቹህ ኢትዮጵያ አንድ እንዳትሆን ሲታገሉ ተገቢ እርምጃ የተወሰደባቸው የሀገር ጠላቶች የአንድነት እንቅፋቶች ሆነው እያለ መሥዋዕትነት የከፈሉ ይሏቸዋል፡፡ አዬ ወያኔ! ይህ ምን ማለት ነው?
Having disagreement with EPRDF is something, but this inhumane and malice statement of yours is very hurtful to any human with flesh and blood. I am very disheartened by your comment. This type of statement and attitude drives away most of us rather than come close. To come close and work for common goals we have to break this old attitude and thought and have a human thought of of sharing pains, such as “when injustice against one is taken as injustice against us all.” Hate and bigotry are not the way to solve our problems. It is compassion for others and see others as us not them.
Abreham says
መሠረታዊ የታሪክና የማንነት ልቀት እንዳለህ የምታስብ ከሆነ፤ አሁንም ደግመህ ማሰብ ያለብህ ይመስለኛል፡፡ በወቅቱም ለጽሁፍህ ተገቢ ነው ብዬ ያመንኩትን ምላሽ በዚሁ ድረ-ገጽ ላይ https://www.goolgule.com/no-more-silence/ ሠጥቼህ ነበር፡፡ ምላሽ ብለህ በሰጠኸውም ላይ ቢሆን፤ እኔ ምላሽ ቢሆን ያልኩት በወቅቱ ውይይቱ ማለቁ ተገልጾልኝ ቢቆምም፡፡ በእራሴ ብሎግ ላይና በፌስቡክ ገጼ ላይ አስፍሬልህ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን http://www.zconcern.blogspot.com/2014/04/blog-post.html ይህ ሁሉ ቢሆንም ቅሉ፤ አሁንም ስለኢትዮጵያዊነት እንደሚዘምር ሰው ሆነህ ትቀርባለህ፡፡ አንተ ለመበታተን የምታስባትን ኢትዮጵያ፤ ሌሎች ሊበትኑት ነው ትላለህ፡፡ ካንተ በላይ በዚህ ግብር የሠራ ማን አለ? ከዚህ ባሻገርም እርግጠኛ ባልሆንም፤ ሠዓሊ ትሆን ይሆናል፤ ጋዜጠኛ ግን መሆን ሌላ ነገር ነው፡፡ ሀሣብን በነጻነት መግለጽ መብት ሊሆን ይችላል፡፡ ህዝብን ባጥላላት ግን ሌላ ነው፡፡ ለስዕልህ የፈለግከውን ቀለም መጠቀም ትችል ይሆናል፡፡ ጽሑፍ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ መጻፍ የቻልክ መስሎህ ሊሆን ይችላል፡፡ ጋዜጠኝነትና ገለልተኝነት ግን ሌላ ነው፡፡ ከጀርባ የምትከራከርለትና የምትወግንለትን ማንነት ይዘህ፤ ስታበቃ ሌሎችን ማሳነስ በእራሱ ጥፋትም ነው፡፡
aradaw says
Dear Abraham:
I have not seen your piece before. I read both you wrote and I want to say thank you for your critical and very thoughtful piece. I was really shocked that there are this type of cruel and senseless people to throw truck load of garbage, bigotry in the name of unity. The most surprising is the second article “ክስ”. I am not surprised that it created a revolt in Jimma Universality. Of course this type of hateful massage will create grievance and revolt any where in the world. I enjoyed your articles and will follow your twitter.