
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሶስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡
መልስ
በፊት የታወቁ – ገነው በስራቸው
ዛሬ ሚታወሱ – በቴዲ ልጃቸው
ስምህ ይጠራልህ – ብትሞትም ያላቸው
ካሳሁን ገርማሞ – ማለት እኚህ ናቸው
ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፬” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡
ቃልም አልተነፍስ – ፍንጭም አልናገር
ታሪክ ስለሆነ – የሳቸው ምስክር
እኚህ የሚታዩት – መልከ መልካም ኩሩ
ማነው የሚባሉት በሉ ተናገሩ
*******************
“እኔም አልናገር !
ሥምና መልክ ሆኖ እያለኝ ድንግርግር
የሩቁን አቅርቦ ፎቶ ብቻ ይናገር
“ለካርልስ፣ ማርክስ፣ ሌሊን “አዝነን ስንማረር
አቤት የእኛ ነገር!
ትልልቅ ሰው አልፏል የተማረ ያስተምር
ዕድሜ አይሳብ ላስቲክ አደል አይመዘዝ ክር
ያልተማረ ይማር አቤት የልጅ ነገር!!
**በ*****ለ*****ው !