• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አህያውን ትቶ ዳውላውን

June 14, 2014 06:31 am by Editor 1 Comment

በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊ የዜና መለዋወጫ መስኮች፤ “ትግሬዎች በዚህ መንግሥት ተጠቅመዋል? ወይንስ አልተጠቀሙም?” የሚለው ጉዳይ ዓይነታ መወያያ ሆኖ፤ መድረኮቹን ሁሉ አጣቦ ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ፤ አንድን ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች ሲያነሱ፤ ከትግሉ ዋና ግብ አንጻር ነው። እንዲያው ለወግ ያህል ወይንም ቁጭትን ለመዘርገፍ የሚደረግ ውይይት፤ የታጋዮችን ቀልብ አይስብም። ይኼ ጉዳይ በትግሉ ሂደት ውስጥ ለኢትዮጵያዊ ታጋዮች ምን ይጠቅማል? ትግሉን ወደፊት ከመግፋትና ከግቡ ከማድረስ አኳያ ምን አስተዋፅዖ አለው? ይኼ ወሳኝ ነው።

ትግል በመርኅ የሚካሄድ እንጂ፤ በየተመቸው የሚነዳ መንፈስ አይደለም። በትግሬዎችና ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ በተነሳው ድርጅት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። በእርግጥ የዚህ ግንባር አባላት በሙሉ ትግሬዎች ናቸው። ይኼ በግልፅ ያለና የማያጠያይቅ ነው። ደጋፊዎቹም በአብዛኛው ከዚሁ ወገን መሆናቸው አያስገርምም። ነገር ግን በአማራው ላይ አማራ ነህ ተብሎ መጠቃቱን እያወገዝኩ፤ አኝዋኩ በአኝዋክነቱ መጠቃቱን እያወገዝኩ፤ ትግሬው በትግሬነቱ እንዲጠቃ ሲዘጋጅ ዝም ብዬ የማይበት ዓይን የለኝም። ትግሬውን እንደ አማራው፣ እንደ ኦሮሞው፣ እንደ አኙዋኩ፣ እንደ ሲዳማው፣ እንደ ኦጋዴኑ ልቆምለት ካልቻልኩ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለቴ ውሸታም ያሰኘኛል።

ይህን የማራምደው ትግሬዎችን ወደ ትግሉ ሠፈር ለማምጣት ካለኝ ምኞት አይደለም። አንድ ትግሬም ሆነ አማራ፤ ኦሮሞም ሆነ አኙዋክ፤ ወደ ትግሉ የሚመጣው፤ የትግሉን መርኅ ስላመነበት እንጂ፤ የግል ጥቅም አገኛለሁ ብሎ አይደለም። እንዲህ ያለው፤ ካለበት ቢቆይ ጥቅሙ የበለጠ ይጠበቅለታል። እኔ ይኼን የማራምደው፤ በትግሬዎች ወገን የሚጠቃ የትግሬ ዘመድ ስላለኝ አይደለም። ይኼን የማራምደው የግል ጥቅም የማገኝበት መንገድ ስላለኝ አይደለም። ይኼን የማራምደው ስለማምንበትና ትክክለኛ መርኄ ሰለሆነ ነው፤ ኢትዮጵያዊነቴ ስለሚያስገድደኝ ነው፤ ታጋይነቴ ስለሚያስገድደኝ ነው።

መረዳት ያለብን፤ ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ለሥልጣን መያዣና አሁንም የሥልጣኑ ማራዘሚያ አድርጎ የያዘው፤ አማራውን በአማራነቱ በማጥቃት ነው። ለአማራው ማጥቂይ አድርጎ ያቀረበው ደግሞ፤ አማራው ተጠቃሚ ነበር፣ አማራው የሥልጣን ባለቤት ነበር፣ አማራው ገዝቶናል፣ በማለት ነው። ይህ ደግሞ መሠረታዊ የሆነውን ኢትዮጵያዊያን ከ፲ ፱ ፻ ፷ዎቹ ተማሪዎች ጀምረው የተነሱለትን በጨቋኝና በተጨቋኝ፤ በገዥዎችና በተገዥዎች መካከል የነበረውን እንቅስቃሴ በመጥለፍ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የአማራው ወገን ሌሎችን በመግዛቱ ነው የሚል የፖለቲካ ስልት በማርቀቅ፤ አነስተኛው ክፍል ብዙኀንን የሚገዛበት ቀመር በማጠንጠን ነው።

እየገዛን ያለው ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ነው። ትግሬዎች ተጠቃሚ ናቸው፣ ትግሬዎች ገዙን፤ የሚለው እምነት፤ ጠንከኛ ነው። የዚህን መንግሥት የፖለቲካ ተግባር ትክክል አይደለም የሚል የረጋ አእምሮ ያለው ሰው፤ ዛሬ በተገላቢጦሽ፤ ትግሬዎችን በአማራዎች ተክቶ በትግሬዎች ላይ ዘመቻ ማድረግ፤ አንድም የዚህን ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ እንዲቀጥል ማራገብ ነው፤ ከዚህ ወዲያ ደግሞ እንደዚሁ ወገንተኛ ወራሪ ግንባር የራስን ወገን ለማሰባሰብ የተወረወረ ዘዴ ነው። በሁለቱም በኩል አፍራሽና የኢትዮጵያዊነት ጠር ነው። ይህ ማለት ለዚሁ መንግሥት ያደሩ አልተጠቀሙም ማለት አይደለም። ሆዳቸውን ያመለኩ ግለሰቦች፤ ለዚህ መንግሥት ስግደው ያደሩ ተጠቅመዋል። ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች አቧራቸውን ተሸካሚም ሆነውም ለዚህ የትራፊ ለቃሚዎች አሉ። እኒህም ተጠቃሚዎች ናቸው። ከነዚህ ሆድ አደሮች የትግሬነት ደም ጠብታ በሰውነታቸው ቢፈለግ አይገኝም። ስለዚህ፤ የስርዓቱ ደጋፊና ስርዓቱን የሚቃወሙ በሚል ብቻ ነው፤ ኢትዮጵያዊያንን ታጋዮች ኅብረተሰቡን የሚከፋፍሉ፤ ድሮም ሆነ ዛሬ። እዚህ ላይ ተጋዮች የሚለውን አሰምርበታለሁ።

የፖለቲካ አመለካከትንና ተግባርን በዘር ላይ የተመሠረ አድርጎ መመልከት ዘረኝነት ነው። በገዥው ክፍልም ሆነ በታጋዩ ክፍል፤ የፖለቲካ አመለካከትን ከግለሰብ አውጥቶ ከአንድ የኅብረተሰብ ክፍል ጋር ማቆራኘት ስህተት ነው። ይህ አጥር የሌለበት ጉዳይ ነው። ለዚህኛው ይሠራል ለዚያኛው አይሠራም ልንል አንችልም። የወደፊቷ ኢትዮጵያ የሁላችን ኢትዮጵያዊያን እንጂ፤ አንዱን ክፍል የሚጠቅም ወይንም የሚጎዳ መሆን የለበትም። ዛሬ በአማራዋ ላይ እየተፈጸመ ያለው ነገ በትግሬዋ ላይ እንዲደገም አንፈልግም። እናም መላ ኢትዮጵያዊያን፤ ትግሬዎችን ሆኑ ሌሎቹ በዚህ መንግሥት ላይ በአንድነት መነሳት አለብን። የፖለቲካ አመለካከታችን በግለሰብ እንጂ የትውልድ ሐረግ በመምዘዝ መሆን የለበትም።

የኢትዮጵያዊያን ጠላት ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት እንጂ፤ ተጠቀመም አልተጠቀመም፤ የትግራይ ወገናችን አይደለም። ኢትዮጵያ ስንል በወርድና ስፋቷ የሚኖረውን ህዝብ በሙሉ እንጂ፤ አንዱን ክልል ለይተን ነው አይደለም ልንል አንችልም። የፖለቲካ ቁማር መጫወት ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ባህርይ እንጂ፤ የታጋዮች ባህርይ አይደለም። አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ዛሬ ትግሬዎችን ራሱን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብሎ የሚጠራው መንግሥት ሙሉ ደጋፊ ናቸው ወይንም በዚህ መንግሥት ምክንያት ተጠቃሚ ናቸው ብሎ እንደ አጀንዳ ማራገብ፤ የዚሁ መንግሥት መጠቀሚያ ከመሆን አያልፍም። ከዚያ ካለፈ ደግሞ፤ የራስን ወገን ለይቶ ነፃ አውጪ ግንባር ለማቋቋም መንገድ የማዘጋጃ ሩጫ ነው። ይህ መንግሥት ሊወድቅ የሚችለው ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተን፤ ኢትዮጵያዊያን ነን ብለን ስንቆም ነው። ከዚህ የተለዬ መንገድ፤ የዚህ መንግሥት መጠቀሚያ መሆን ነው።

አንዱ ዓለም ተፈራ፤ የእስከመቼ አዘጋጅ፤

eske.meche@yahoo.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. RESOM says

    June 30, 2014 11:17 am at 11:17 am

    በእዉነት ከሆነ በዉስታችን ያለዉ ተንኮል ትተን መትፎነት ትተን በመልካምነት ብንመለከት ያለዉ ገዢዉ{መንግስት}ትግሬ ብቻ እንዳልሆነ ልቦናች ያዉቃል ኢትዬ በሙሉ ደማችን በመርዝ አንመርዘዉ አፋችን በቆሻሻ አንሙላዉ እግራችን ወደ ሲሆል አንምራዉ ከመልካም እትፍ ደስታ ከተኮል ደሞ እትፍ…………………….ይገናል ስለዚህ ወገኔ አንሳሳት አንቾክል ከመወሰናችን በፊት እናስብ እ/ር ሆይ የሚያስተዉል አይምሮ ስተን አሜን አሜን አሜን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule