ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።
በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣ ስሙ እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤
ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣» (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤ በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦
- ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
- ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
- ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
- ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣
ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።
ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣ አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ እንኳን የሌላቸው ናቸው።
ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤ እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?
አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤ የጨለማዎቹም ሰዎች እንደገና ተነሡ፤ ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤ አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።
የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።
በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤ የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።
ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም፤ ሰኔ 2006 ዓ.ም
Yonas says
Bilih sew ke tanashu yimaral.
Tigist chilo malef kenanetin fikir andinet astemari… Tiru neger enkifat ayatawuw. Teddy yechilema wust birihan… Ewket balew asteway libam ewnetegna sew tewekso ayakim. Bayhon yidenekal enji.
aradaw says
Ewket balew asteway libam ewnetegna sew tewekso ayakim. Bayhon yidenekal enji.
Teddy is a singer and has his followers too. Teddy and his talent, his kindness, truthfulness are not in question here. Teddy as a political person is a question just like any other political person. We have some successful singers than Teddy before and still now. Teddy’s problem started when he picked a song that a lot of people did not like and the song was pure political. He chose and as his choice must handle the criticism, opposition it comes with his choice. I am sure his followers will still cheers him while his opponent will still criticize him. . I do not see why Teddy is an exception. Teddy cannot get free ride for everything he says. That is the norm when one is in public arena and takes a political stand.
ኢትዮጵያ ክብሬ says
የተከበሩ ፕሮፌሰር እጅግ በጣም አመሰግናለሁ የሚናፍቁትን የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያሳይዎት። አሜን እኔ ከ ቴዲ አድናቂዎች አንዱ ነኝ የሚፈጸምበትን በደልና ግፍ ሁሉ ለመቀበል ከጎኑ ሁሌም አለሁኝ ይህም ቴዲ ለምወዳት ሐገሬ እና ለሕዝቧ ካለው ፍቅር እና መልካም አሳቢነት የተቀዳ ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያዊነት እስኪነግስ ወይም ኮካኮላ በይፋ ጥፋቱን አምኖ ቴዲዬን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዬን ይቅርታ እስካልጠየቀ ድረስ ኮካኮላ አለመጠጣት ብቻ ሳይሆን ጎጂ ጎኑን በማጉላት ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ከመስበክ አልቦዝንም እስካሁንም በርካታ ወገኖቼ አምነውበት መጠጣት ከማቆም እስከ ጎጂነቱን ወደመስበክ ተሸጋግረዋል እንቀጥልበታለን በደሌ ቢራንም ዳሽን ቢራንም እንደዚሁ። ትግላችን ይቀጥላል እናሸንፋለን!!
ኢትዮጵያ ጠላትዋ ተወግዶ በክብር ለዘላለም ትኖራለች!!!!!!!
aradaw says
I can not believe this article is written from professor መስፍን ወልደ-ማርያም፤ It is very unlike of him to advocate for an individual. It will be very naive to just separate the current political situation from the act of ቴዲ አፍሮ. I will refrain from the car accident debacle. It is really not important for the question raised by ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም,. Teddy’s artistic talent or his earning potentials are not questions here too. It is very simplistic and not expected from professor Mesfin to say the whole situation with Teddy is “በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ” .Dear Professor knows that the whole affair of Teddy is clear political. Teddy took a clear stand through his songs in the controversial history and particularly Menelik. Dear Professor knows our history, our politics. We are in this odd situation where we do not agree who our heroes and villains are. King Menelik is a hero to some and Teddy has all the free speech right to write, talk and sing about his hero. In same token there are others who look Menelik as a villain. They also have the right to voice their opposition. This is not new in the world politics to voice opposition including boycott, it happened and still happening in the whole world arena and I am really surprised with this article of the professor to be one-sided and misrepresent the deep historical fact. Dear Professor tries a baseless accusation of those who opposed Teddy as ” የጨለማዎቹም ሰዎች”. As he advocates the individual right of Teddy , he forgets the right and voice of the opposition side. Just a reminder, group boycott has helped liberate South Africa. It is a peaceful tool of struggle.
Getachew says
I belongs to teddy. God bless you ma bro
gobeze says
Teddy has a great talent but many of his songs favor one group(especially those of Aristocrats. this brings an opposition towards him. as an individual he has the right to sing on behalf of them but he at the same time should realize that his position do not represent the whole of Ethiopia. Teddy’s action is awakening our saddest feelings.
tolcha says
funny! the so called professor, saying the dark age people.
aradaw says
It is really sad to hear this from a person we call Professor a respected senior citizen of “Ethiopia” “የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው”. Our respected professor may have forgotten (may be it is an age thing) nobody talks, cares about ቴዎድሮስ ካሣሁን as an individual. May be the senior citizen professor forgot that Teddy did not start singing yesterday it has been for a while and all this time nobody cared except appreciating his music or singing talent. Listening or not listening his songs, buying his records or not. He was the same like any other አዝማሪ. It would have been a little logical may be smarter to ask “What happened to ቴዎድሮስ ካሣሁን recently and why is he having huge oppositions from one sector of the population and precisely the Oromo population? and also “Why he is getting some support from some special groups? The answer for your question የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው? can be found from this two questions. One also can go further and look deeper from who are the Ethiopian majority who are opposing the most recent song of ቴዎድሮስ ካሳሁን and why. These questions leads us back to our past history. There is no question we have unsolved disagreement in our history, we have disagreement in who are our heroes and villains are. Recently ቴዎድሮስ with his song “ጥቁር ሰው” entered in this dichotomy, he took a stand joined one group discrediting the history and grievances of the others. It is highly irresponsible for our respected Professor to characterize and enter in name calling the opposition as “የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ” (it is surprising to hear such hostility, disrespect and impertinence and a mentality that looks down on others) . I wish our dear Professor as an intellectual and senior citizen took a different unbiased stand to close or shorten the gap that exist now. I am very saddened by his piece here he chose the expression “ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች”. This baseless accusation of trashing the opposition and painting them as የጨለማ ሰዎች will not help us to find a common ground for discourse. Spreading hatred and bigotry deepens & widens the gap. As a former student of the Professor, I am disheartened by his comment of የጨለማ ሰዎች . As a senior citizen with great credential and long term experience, I expect him to guide us with an alternative new vision that leads us to a common ground which eluded us for a
longtime. As his former student I still wish him long life and health and to hear more positive and uplifting things from him.
BALE TEDAR says
“የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው” በትክክል በብዙሀን ስም ግለሰብን የሚያጠቃ ለግለሰብ መብት የማይቆም ስርአት ነው ቴዲን መጽሄቶች የሚፈልጉት የቴዲ ፎቶ ከተለጠፈ ገበያው ሰፊ ነው ሁሉም ህዝብ ይገዛዋል የወያኔ አንዱ የህትመት ጋዜጣም ይሁን መጽሄት ይህንን በህዝብ የመነበብ እድል ስላላገኙ ክፉኛ ይበሽቃሉ ሌላው ቴዲ ከመንግስት ቀድሞ ስለመቻቻል ስለፍቅር ከነሱ በልጦ ስለሰበከ እና ህዝብ ስለወደደው ይንገበገባሉ ሌላው ሀገሪቱ ላይ ያሉ አርቲስቶች የግዜውን መልክ በብእራቸው በድምጻቸው ቀርጸው ለትውልድ መስታወት ሆነው ከአንድ የአርት ሰው የሚጠበቀውን ማድረግ ሳይችሉ በበሉበት የሚጮሁ ሆዳሞች በሆኑባት ሀገር ቴድ ” ባስራሰባት መርፌ በጠቀመው ቁምጣ አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ ” ብሎ ያለውን ስረአት በብእሩ ግዜውን ለትውልድ ቀርጾ ስላሳየ በጠላትነት ተፈርጁዋል ምናልባትም ለዚህ ሁሉ ጥልፍልፍ መነሻው ይሄ ነው ብዬ እገምታለሁ እንግዴህ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በሚፈቅደው ህግ ደሞ ቴዲ መብቱን ተጠቅሙዋል እንደተባለው ” የጨለማ ሰዎች “ራሳቸው ያወጡትን ህግ ራሳቸው ሊያዩት አልፈቀዱም ምክንያቱም ጨለማዎች ስለሆኑ .እናመሰግናለን ፕሮፌሰር !!!!!!!!!!!!!!
aradaw says
ከድጡ ወደ ማጡ
One thing we have to realize. When Teddy says something good and contribute and voice on the side of the people, we all say good job. But we do not have to give him license to say anything and specially that hurt more than half of the Ethiopian people. I am sorry and it is hard for me to agree Teddy is an artist only. Yes, he is a singer and politician. In his song “ባስራሰባት መርፌ በጠቀመው ቁምጣ አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ’. In this song he voiced the voice of the people and we all said ጎሽ ፣ እሰየው and we bought his CDs and attended his concerts above all rewarded him with money he never had in his life and popularity more than he imagined. When Teddy has the car accident thing and was imprisoned all the Ethiopian people including the one you call them “ጨለማዎች” stood with him voicing his release. He is criticized for the song “ጥቁር ሰዉ”. As the history and the deed of the king divided the Ethiopian people so did the song.
As our customary and usual way of handling our disagreement, instead of convincing each other with reason, fact and logic, here we go into baseless accusation, belittling demands and grievances, trashing the other side painting them as ” “ጨለማዎች”. He is an artist and should be criticized for bad deeds that does not respect people and their history. For sure when he does something positive, when he voices the pain of all Ethiopian people he will be rewarded also when he mess up with history and sing the voice of bigotry and hatred and become irresponsible he will be criticized and boycotted. I do not know “BALE TEDAR” knows this, I am sure Teddy clearly knows when he entered in the public arena that he will be criticized or appreciated depending what he does. It would have been civic if your comment does not include name calling as የጨለማ ሰዎች It is unnecessary disheartening and does not help us to have a decent conversation and reduce the gap we have.
በለው ! says
ለሀገር ሉዐላዊነት፣ለህዝብ አንድነት፣ለዳር ድንበር ለነፃነት ለታሪክ የዘፈኑ፣የፃፉ፣የተናገሩ አሸባሪ ይባላሉ በሚሽነሪ ቡችሎች(ሹምባሾ) ጠላት ይደረጋሉ ።
“አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።! ” አንድን አዋቂ ነኝ ባይ ስሙ እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣የሌላውን ባለሙያ ድካምና ጥረት ሥራውን ቢያንቋሽሽ ወይም ቢተች ወይም ግላዊ ሃሳቡን ቢሰጥ ባለሙያ አይባልም፣ ማንነቱንና ምንነቱን አስካፈረበት ድረስ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ጉዳዩ ከዚያው ከምቀኝነትና ከድንቁርና አያልፍም።
**በአንድ ወቅት ቴዎድሮስ ካሳሁን የመንገድ ላይ ተዳዳሪ ወጣት ገጨ ተብሎ እሰከማሰርና ፍርድ ቤት አስከማንገላታት ከፍተኛ ዘመቻ ነበር። በዚህ ጉዳይ አንድ አስቂኝ ጉዳይ የነበረው የክሱ ጭብጥ ከመጠናበሩና ከማጥበርበሩ ማጭበርበሩ በዝቶ …አደጋ ደረሰ የተባለው ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ሆኖ ተጎጂው ዳግማዊ ምንይልክ ሆስፒታል ስምንት ሰዓት ከአሥራ አምስት ደቂቃ ደርሷል።ለመሆኑ አንቡላንሱ ቴዎድሮስ ወጣቱን እንደሚገጨው አውቆ ቆሞ ይጠባበቅ ነበር? አንቡላንሱ ክንፍ አለው? ሌላው በዚያ ፍጥነት ግለሰቡ እንዴት መሐል አስፋልት ላይ ተገኘ? ወይ አስፋልቱ ላይ አንጥፎ ተኝቶ ነበር? ወይንም ሌላ ሰው ገድሎት መሐል ሜዳ አስቀምጦት ሄዷል? ግን ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ!
**ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ሐጢያትና በሁሉም ሃይማኖቶች የተወገዘ ነው። የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ሌላው ነው፤ፖለቲካ ተንታኝ (በታኝ) የጭፍን ፖለቲካ መር! “ቦይ ኮት” የሚሉ ከእርዳታ ሰጪ ሀገራት ከአፍ በወደቀች ቃል ተወስውሰው እንዴት ጠግቦ በማይበላ፣ ሆዱ በአልቅት በተቆዘረ፣ የልጆቹ ፊት በዝንብ በተወረረ፣ ህዝብ ላይ አመፅ ብጥብጥ የአርስበእርስ የሜንጫ መጨፋጨፍን ለድሃው ሕዝብ እየሰበኩ ። እነሱ ሰላምና ምግብ በሞላበት ሀገር ተቀምጠው ሌት ተቀን የድሃውን ልጅ ጭዳ ሊሉ ሲለፋደዱ ይደመጣሉ።
***አሁንም እንደልማዳቸው ከኮካኮላ ኩባንያ ጋር ያለውን ውል ለማፋረስ ምላሳቸውን ሥለው ሜንጫቸውን አንግበው ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤ የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።
>>>”የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?ሲሉ ሊቀ-ጠበብት መስፍን ወልደማርያም ተገርመዋል?
***እንግዲህ የዘርና የቋንቋ ክልል, አንደከብት በአንድ ቦታ መታጎር የሚፈጥረው ብዥታ, የማንነትና የምንነት መሳከር፣ እንደፋሲካ በግ የተገዛ፣ የተሸጠ፣በጥቅም የተለወጠ ለመሆኑ የማንና የየት ክልል ተንቀሳቃሽ ከብት መሆኑ በባንዲራና በብሔር በቀበሌ መታወቂያው በሚናገረው ቋንቋ እየተመረጠ ተቧድኖ የሚንቀሳቀስ ጠባብ አመለካካት የሚፈጥራቸው የትንሽነት ምልክት…የመጥፎ ሀገራት የተረሳና የዘቀጠ ፅንፈኝነትን ኩረጃ…ዘረኝነት…ኋላቀርነት ተደምረው ከሀገር ሉዓላዊነት ይልቅ የክልል ሉዓላዊነት ..ከሕዝብ ይልቅ ጠባብ ጎሰንነት..ከአንድnት ይልቅ መበታተን…ከተጨባጭ ታሪክ ይልቅ ወሬ…አሉባልታን ማናፈስ የሚፈጥራቸው ሽብር በደም ውስጥ የሰረፀ ብልሹ ሥነ-ምግባር በእርግጥ መንግስትና ህግ ቢኖር በወቅቱ ማረምም ከምንጩም ማድረቅ ይቻል ነበር። ሆኖም ያለው መንግስት የራሱን ሥልጣን ዘመን ለማራዘም ታላቁን ሀገር የማጥፋት ተልዕኮ ለማሳካት ተከታዮችን (የጨለማዎቹን ሰዎች) ለአመፅ፣ ትውልድ በማምከንና በማባከን ሥራ ላይ ለ፳፫ዓመት በሚገባ እየሰሩ ከዚህ መንግስት ልዩ ተጠቃሚ ሆነው የአዞ እንባ እያነቡ እንደ ቁራ እየጮሁ ተልዕኮአቸውን በጋራ አሳክተዋል ።አራት ነጥብ። እንግዲህ ሥለ ሀገር ሰላም፣ አንድንት፣ እኩልነት፣ ፍቅር፣ አብሮ መኖር፣ ጀግነት፣ ዳር ድንበርና ሰንደቅ፣ የሚናገርም የሚቆረቆርም አይኖርም! ትውልዱ ወኔውም ሞራሉና ማንነቱ ተሰልቦ በቁሙ የሞተ ሆኗል ወጣቱና ሴቶች ካልነቁ ሀገር በነበር ይቀራል። አዎን! ስለ ሰላም የሚሰብኩ ይከበሩ ዘፈንን ብቻ መውደድ ሳይሆን ለሞተ ደረት መድቃት ባነር መወጠርና በፀሀይ መነፅር ተከልሎ ከመወጠር ከዜጋም ጋር አብሮ መቆም ይልመድብን በለው! በቸር ይግጠመን
aradaw says
This type of talk which has no logic or any historical fact. Full of emotion will not bring us together. Respect, tolerance, straight argument that gets the heart and mind of our people will bring us much closer and help us remove the fascist woyane.
samson says
መስፍን ያረጀና ወደ መቃብርና ወደ ሲዖል እያመራ ያለ ውሻ ነው
ባለሃገሩ፤ says
ባለሃገሩ፤
ቴዲ አፍሮ በቅርቡ በኮካኮላ ድርጅት በኩል የገጠመው ችግር ከዚህ በፊት ሲገጥሙት ከነበሩት የተለየ አይደለም። ጥያቄው ለምን ነው መሆን ያለበት። ባጭሩ ለመናገር አንድነትን፣ ፍቅርን፣ ወዳጅነትን፣ መቻቻልን በህዝቦች መካከል እንዲቀጥል ካለው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ በሚያቀነቅናቸው ዘፈኖች በመግለፁ ነው። በዚህም ስኬታማ ሆኖ በሃገሩ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ስላገኘ ነው።
ልዩነትን የሚደግፉ ጥላቻን የሚያስፋፉ በጠላትነት ጎራ ለይተው ግጭቶችን የሚናፍቁ ጥቂት ወገኖች እንዳሉ ማመን አለብን። የሃገራችን ጠላቶች በፊት ለፊት ማግኘት ያልቻሉትን ድል ዘዴያቸውን ቀይረው በራሳችን ወገኖች ሊያጠቁን እንደሚሞክሩ ግልጽ ነው። ለግል ጥቅም ማንነታቸውንና ሀገራቸውን ለመሸጥ የሚደራደሩ ዜጎች አሉ ወደፊትም ይኖራሉ።
ያለፉት የኢትዮጵያ መሪዮች በቴዲ ዘፈኖች የተወደሱትና የተሞገሱት በ አንድና አንድ ምክንያት ነው። ነጻነታችንን አስከብረው ለዛሬው ትውልድ በማስተላለፋቸው ነው።