ለብዙዎቹ ችግሮቻችን ፍቱን መድኃኒት አድርጌ የምወስደው፣ ጉዳዩን በዘመን ቁመት እና በዓለም ሕዝቦች ታሪክ አግድም መመልከት ነው። ዓለም በበቂ ሁኔታ የምንማርባቸው ስኬቶች እና ውድቀቶች አሏት። ዘውጌኝነት፣ ብሔርተኝነት እና ዜግነት የመሳሰሉትም የብቻችን ጉዳዮች አይደሉም። ዓለም በየፈርጁ የዳከረችበት እና እየዳከረችበት ያለ ችግር ነው። ስለዚህ ጥያቄውን በቅጡ ለማበጃጀትም ይሁን፣ አዋጭ መልስ ለመፈለግ ከሰው ልጆች እንደአንድ የሚያደርገንን ታሪክ የምናውቀውን ያክል ማሰስ ያስፈልጋል። ይህን ከጠቆምኩ በኋላ ወደ የበኩሌን ለመሞከር ወደ አጀንዳዬ እዘልቃለሁ። የዘውግ ብሔርተኝነት ምንድን ነው? የዘውግ ብሔርተኝነት (ethnonationalism) የአንድ ዘውግ (ethnic) ቡድን ነጻ አገር እንዲመሠርት ወይም ከመገንጠል ወዲህ ያለውን የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ለማስቻል የሚደረግ … [Read more...] about “ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]
Opinions
የኔ ሃሳብ
ስለ ሸገር የምለው አለኝ
"ነፍጠኛው ስርዐት ስማቸውን ቀየራቸው ከተባሉት ቦታዎች ውስጥ መርካቶ፣ ፒያሳና ካዛንቺስ ይገኙበታል፤ እነዚህ ጣሊያናዊ ስሞች ናቸው፤ የክሪስፒና የምኒልክ፣ የተፈሪና የሙሶሎኒ ዝምድና ይጣራልን፡፡ * የታሪክ መፅሐፍቱ "Oromo migration movement" ሲሉን ከርመው አይ "Oromo population movement" ነው ብለው አስተካከሉና መዳ ወላቡ ከህዝቡ መስፋፋት በፊት የኦሮሞ ማዕከልና መነሻ መሆኑን ነገሩን፡፡ መስፋፋቱ ደግሞ እ.ኤ.አ ከ1522-1618 ነው እስከዛ ድረስ አዲስ አበባ የማን ነበረች? * ከክርስቲያኑ ግዛተ አፄ እና ከሙስሊሙ የ16ኛው ክ/ዘ አታካችና ረጅም ጦርነት በኋላ የሁለቱም ወገን ጃይንቶች ገላውዲዎስና ኢማም አህመድን ሞት ተከትሎ ተዋጊዎቹ መዳከማቸው ለኦሮሞ ግስጋሴ አይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አፄ ሚናስ የጦራቸውን መሳሳት ተከትሎ የኦሮሞ ተዋጊዎችን … [Read more...] about ስለ ሸገር የምለው አለኝ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የ EDF አቋም መግለጫ
የኢትዮጵያውያን የውይይትና ምክክር መድረክ (ኢውምመ) (EDF) በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የተመሰረተ መድረክ ሲሆን በኢትዮጵያ መሰረታዊ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የፖለቲካዊ ችግሮች ዙሪያ ምርምሮችን እያካሄደ ለተፈላጊ ለውጦች የሚታገል ድርጅት ነው። የዚህ ድርጅት አመራር አባላት በቅርቡ በሚንስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም የሚተነትነውን ረቂቅ አዋጅ በጥልቀት ተወያይቶበታል። ተወያይቶ የሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል በEDF እምነት በመጀመሪያ ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ከብሄር ፖለቲካ የመነጩ አንዳንድ የህገ መንግስቱ አንቀጾች ናቸው። ለዚህ ለአሁኑ የሚንስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ መነሻውም ይሄው ህገ-መንግስቱ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 5 ነው። ህገ-መንግስቱ ከብሄር … [Read more...] about የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የ EDF አቋም መግለጫ
የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት
ራዕይ ለኢትዮጵያ - Vision Ethiopia Vision Ethiopia and ESAT Fourth Conference Second call for papers, July 3, 2017 Conference Theme: Building Democratic Institutions in Ethiopia የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት Vision Ethiopia, an independent network of Ethiopian scholars and professionals, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT), is pleased to announce that the Fourth Conference will be held in Washington D.C. on September 16 and 17, 2017. We thank those who … [Read more...] about የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት
ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ሚያዚያ 27፤2009 የተከበረበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዕለቱ (May 5, 2017) “የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ ለኅትመት አቅርቦ ነበር፡፡ የጽሁፉ ዓላማ በዚህ መልኩ ቀርቦ ነበር፤ “በየዓመቱ ሚያዝያ 27 የሚከበረው የድል ቀን በኢትዮጵያ የቀን መቁጣሪያ (ካሌንደር) ላይ ሥራ ተዘግቶ እንዲከበር ቢደረግም ትውልዱ የቀደሙ እናትና አባቶቹን የተጋድሎ ታሪክ እንዲያወቅ የሚያስችል የበዓል አከባበር አይታይም፡፡ ዕለቱም እንደአንድ ተራ የረፍት ቀን ያልፋል፡፡ በአንጻሩ አንዳች አገራዊ ፋይዳ የሌላቸው የህወሃት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ … የምሥረታ ቀን እየተባለ በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ የሚወጣባቸው ለወራት በዕቅድ ተይዘው የሚደገሱ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ ይደረጋል፡፡ “አዲስ አበባ አራት … [Read more...] about ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የሳውዲ የተራዘመ የምህረት አዋጅ እንዴት እንጠቀምበት?
* የተራዘመው የምህረት አዋጅ * የ90 ቀኑ ምህረት አዋጅ አስተምሮቱ .. * አጭሩን ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም .. * የበረራ ፈቃድ እና የአሻራ አሰጣጡ ተጠያቂ ማነው? * በቂ ድጋፍ ለማድረግ የሰው ሃይልን ስለማደራጀት .. * ስራው በማን ነው የሚሰራው? የዲፕሎማቶች? መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ሳውዲን በ90 ቀን ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የተሰጠው ቀነ ገደብ ለ30 ቀናት ተራዝሟል ። በሳውዲው ንጉሳዊ ቤተሰቦች አመራሮች ይሁንታ አግኝቶ በሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ማምሻውን በፖስፖርት የበላይ ዳይሬክተር በሜጀር ጀኔራል ሱሌማን የህያ ይፋ የሆነው መረጃ ይፋ ይፋ ሆኗል። ይፋ የሆነው የምህረት አዋጅ የ90 ቀኑ የምህረት አዋጅ ካለቀበት እአአ ከሰኔ 25 ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ድረስ የሚቆይ እንደሆነው ታውቋል። ፖስፖርት የበላይ ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል … [Read more...] about የሳውዲ የተራዘመ የምህረት አዋጅ እንዴት እንጠቀምበት?
ይድረስ ለአርበኛው ጸሐፊ ዕዝራ ዘለቀ (ዕዝራ አስቻለው ዘለቀ)
በተከታታይ የጻፍካቸውን ሁለት ግሩም መጣጥፎች በፍቅር አነበብኳቸው፡፡ በነዚህ ጽሑፎች እንደተረዳሁት ጥሩ አንባቢ ነህ፤ የብዕር አጣጣልህም ውብ ነው፡፡ ሀገርህንም እንደምትወድ በጽሑፍህ ብቻ ሣይሆን በረሃ መውረድህ ራሱም በቂ ምሥክር ነው፡፡ ማቄን ጨርቄን ሳትል ለአንዲት እናትህ ኢትዮጵያ ስትል እያሳለፍከው ያለኸውን መከራና ስቃይ መረዳት እችላለሁና የእምዬ አምላክ ይከተልህ፡፡ አንተን ብቻም ሣይሆን ለተመሳሳይ በጎ ዓላማ የተሰለፋችሁትን ጓዶችህንም ሁሉ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ፤ ያሰባችሁትንም ያሳካላችሁ፡፡ በረከቱ የሁላችንም ነውና፡፡ እኛም በጸሎት ከጎናችሁ አለን፡፡ ይሁንና በግልጽ መነጋገር ለሁሉም ወገን የሚበጅ እንደመሆኑ ከጽሑፍህ ለመረዳት የሞከርኩትን በግልጽ የተነገሩና ያልተነገሩ አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳት ወደድኩ፡፡ ከብረት ዝገት ከሰው ስህተት እንደመገኘቱ ተሳስቼ የተረዳሁብህ ነገር … [Read more...] about ይድረስ ለአርበኛው ጸሐፊ ዕዝራ ዘለቀ (ዕዝራ አስቻለው ዘለቀ)
“ተዋከበና!”
ለቴዲ አፍሮ ዉበት ያምራል እንዴ? ቁንጅናስ ያምራል? አንዳንድ ጊዜ ሰዎች “I didn’t do nothing” ወይም “I didn’t say nothing” ሲሉ መስማት አዲስ አይደለም። እጅግ በጣም አልፎ አልፎ ቢሆንም፣ እንግሊዝኛ ያፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ሰዎችም ሲሉት ይሰማሉ። በቋንቋው ህግ መሰረት ይህ አ/ነገር ጎደሎ ነው። “double negative” የሚፈጥረው የ“positive” ትርጉም/ፍቺ ግድፈት ይመስለኛል። ሁለት ነጌቲቭ (“didn’t” እና “nothing”) ቃላት/ሃረጎች፣ አንዳንዴ ፖዚቲቭ ትርጉም የሚያስከትሉ መሆኑ ነው። “I didn’t do nothing” ወይም “I didn’t say nothing” በሚሉት ዓ.ነገሮች ውስጥ ለማለት የተፈለገው “ምንም አላደረግሁም”/“ምንም አልተናገርኩም” ሲሆን፣ ትርጉሙ ግን የተገላቢጦሹ ሊሆን እንኳን ባይችልም፣ በጣም ያደናግራል። እናም … [Read more...] about “ተዋከበና!”
አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ አወጣ
የዚህች ጦማር ዋና ዓላማ፡ “ያዲስ አበባው ሲኖዶስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ከቀሩት አኀት አብያተ ክርስቲያናት ተነጥላ ከሀያ በላይ ስህተት ሰርታለችና ትመርመር የሚል ክስና ወቀሳ አቀረበ” ብሎ ሀራ ዘተዋህዶ ባቀረበው ዜና፤ ግራ የተጋባችሁ ክርስቲያኖች፤ “በአኀት አብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያዊ ትውፊት አንጻር እንዴት ትመለከተዋለህ“ ብላችሁ ላቀረባችሁልኝ ጥያቄ ለመመለስ ነው። ይህ የቀረበው ሀሳብ የሀራ ዘተዋህዶ ድረ ገጽ ፈጠራ ከሆነ፡ ”አባት ሆ ይ!እኔ በአንተ አንተ በእኔ እንዳለህ እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ”(ዮሐ 17፡ 21“)በሚለው ክርስቶሳዊ ቃል፤ አንድነታቸውን አጽንተው በኖሩት በአኀት አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየዘመተ ነው ማለት ይቻላል። ምናልባትም ከጥንት ጀምሮ እነዚህን ጥንታውያት አብያተ ክርስቲያናትን ለማጥፋት የሚታገሉት የሰባልዮስ ወይም የአርዮስ ተከታዮች ሊሆን … [Read more...] about አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ አወጣ
የሻለቃ ዳዊት የዋሽንግተን ሲያትል ንግግር በሞረሽ ዕይታ!
ሰዎች መልካም ሢሠሩና ሲናገሩ ማመስገን፣ መጥፎ ሢሠሩና ሲናገሩ ደግሞ መምከርና መገሰጥ ተገቢ ነው። ምንጊዜም ሁሉም ሰው ሕይዎቱን ሙሉ ስሕተት ብቻ እየሠራ አይኖርም። መልካም ነገሮችም ይሠራል። ልዩነት የሚኖረው የትኛው ሥራው ነው የሚያመዝነው? መልካሙ ወይስ መጥፎ የሚለውን መመዘኑ ላይ ነው። በዚህ ረገድ የሻለቃ ዳዊትን ሥራዎች መዝኖ፤ የማሞገሱም ሆነ የመውቀሱ ተግባር፣ እርሳቸውን የሚያውቁ፣ አብረዋቸው የሠሩ፣ የትaምህርትና የሥራ ባልደረቦቻቸው ተግባር ይሆናል። ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ለዐማራ ነገድ ድምፅ ለመሆን የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ያለ ድርጅት ነው። ስለዚህ ሻለቃውን በዚህ ንግግራቸው፣ ላለፉት 5 ዓመታት ሲጮኽባቸው የነበሩ አንኳር ጉዳዮችን እያነሱ፣ ዐማራውን ሲያወግዙ፣ በጠላትነት ፈርጀው የዘር ፍጅት በፈጸሙ ግለሰቦችና ስብስቦች ፊት በኩራት ቆመው በመናገራቸው ከልብ … [Read more...] about የሻለቃ ዳዊት የዋሽንግተን ሲያትል ንግግር በሞረሽ ዕይታ!

![“ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]](https://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2017/07/mc-nat-748174-300x130.jpg)








